| የምርጫ ቦርድ በቀበሌ 13/14 ላይ... |
|
|
| Sunday, 20 April 2008 | |
|
የምርጫ ቦርድ በቀበሌ 13/14 ላይ የምርጫ ስህተት መፈጠሩን አመነ
- ምርጫው ዛሬ ይደገማል የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት በአዲስ አበባ በቀበሌ 13/14 በቀድሞ ቀበሌ 10 የምርጫ ጣቢያ 2-ሀ ላይ ያለፈው እሁድ በተደረገው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምርጫ አሰጣጥ ሂደት ላይ ስህተት መፈጠሩን አመነ፡፡ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለወረዳ 12/13 የምርጫ ክልል ጽ/ቤት እንዲሁም በግልባጭ ለተወዳዳሪ ፓርቲዎች ሚያዚያ 09 ቀን 2000 ዓ.ም በአ 64-01/ክ/14/244/19 በፃፈው ደብዳቤ፤ በወረዳ 12/13 የምርጫ ክልል በቀበሌ 13/14 የምርጫ ጣቢያ 2-ሀ በተደረገው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ላይ ስህተት ተከስቷል፡፡ በደብዳቤው መሰረት በምርጫ ጣቢያ 2-ሀ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምርጫ፤ የድምጽ መስጫ ወረቀት የሌላ የምርጫ ክልል ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ይህም ስህተት የድምጽ አሰጣጡ ሂደት ሲጀመር ሳይታወቅ የምርጫ ጣቢያው መራጭ ድምጽ የሰጠበትና ቆጠራም ተካሂዶ ካለቀ በኋላ መታወቁን የቦርዱ ጽ/ቤት ማመኑን ደብዳቤው ያመለክታል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ የምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት ከቦርዱ ኃላፊዎች ጋር ባደረገው ውይይት የተፈጠረው ስህተት መታረም እንዳለበት ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡ በዚህም መሠረት የመራጩ ህዝብ የመምረጥ ህገ መንግስታዊ መብቱን ከማስጠበቅ አኳያ የምርጫ ሂደቱ እንዲደገም ተወስኗል፡፡ በደብዳቤው መሠረት በምርጫ ጣቢያው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማሟያ ምርጫ ዛሬ ይካሄዳል፡፡ የአዲስ አበባ የምርጫ ቦርድ አስተባባሪ አቶ ደስታ ኃይለሚካኤል በበኩላቸው በጣቢያው የሚገኙ ኃላፊዎች ሳይቆጣጠሩ፣ በስህተት ከወረዳ 24 የመጣ የድምጽ መስጫ ወረቀት የእጩዎች ፖስተር፣ የድምጽ መስጫ ባሎት በወረዳ 12/13 ቀበሌ 13/14 የምርጫ ጣቢያ ሀ ላይ ጥቅም ላይ መዋሉን አስታውቀዋል፡፡ በዚህም ምክንያት “ባልሆነ የድምጽ መስጫ ወረቀት ድምጽ ስለተሰጠ፤ ምርጫው ትክክል አይደለም፡፡ ስለዚህ ምርጫው ይደገማል” ሲሉ አቶ ደስታ ገልፀዋል፡፡ በተሾመ ንቁ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |