| የአፍሪካ ልማት ባንክ ለፋይበር ኦፕቲክ... |
|
|
| Wednesday, 09 January 2008 | |
|
የአፍሪካ ልማት ባንክ ለፋይበር ኦፕቲክ ዝርጋታ 14 ሚሊዮን ዶላር ፈቀደ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ21 በላይ የሚሆኑ የአፍሪካ አገራትን በፋይበር ኦፕቲክስ ለማገናኘት ለተጀመረው ፕሮጀክት የአፍሪካ ልማት ባንክ 14.5 ሚሊዮን ዶላር ብድር መፍቀዱ ተገለፀ፡፡ ባንኩ የብድሩን መፈቀድ አስመልክቶ ከትናንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ ብድሩን የፈቀደው ከሌሎች ብድር ከሚሰጡ ተቋማት ጋር በመተባበር ነው፡፡ ገንዘቡ በምሥራቅ አፍሪካ ባህር ዳርቻ ውስጥ ለውስጥ የስልክ ኬብል ለመዘርጋት ለተጀመረው ፕሮጀክት ሥራ ይውላል፡፡ የፋይበር ኦፕቲክስ መስመር ዝርጋታው ፕሮጀክት በጠቅላላው በባህር ዳርቻና ወደብ አልባ የሆኑ 22 አገሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የከፍተኛ ደረጃ ያለው የኢንተርኔት አገልግሎትና ዓለም አቀፍ የመገናኛ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል፡፡ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በአካባቢው ለሚኖሩ 250 ሚሊዮን ሕዝቦችን የመገናኛ አገልግሎት መስጠት የሚቻል ሲሆን የደንበኞችና የተጠቃሚዎች የአገልግሎት ታሪፍ እንደሚቀንስም ይጠበቃል፡፡ ከአፍሪካ ልማት ባንክ የወጣው መረጃ እንደሚጠቁመው፣ የፕሮጀክቱ በለቤቶች በባህር ውስጥ ለውስጥ የሚዘረጋ የፋይበር ኦፕቲክ ዝርጋታ የሚሆን ግንባታ የሚገነቡ ሲሆን የደቡብ አፍሪካ የባህር ደርቻን ይዞ እስከ አፍሪካ ቀንድ ድረስ 10 ሺህ ኪሎ ሜትር ይሸፍናል፡፡ አገሮቹም ደቡብ አፍሪካ፣ ሞዛምቢክ፣ ማዳጋስካር፣ ታንዛኒያ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ጅቡቲና ሱዳን በባህር ዳርቻ በሚገኙ አገሮች የሚያልፍ ነው፡፡ ከዚሁ የፋይበር ኦፕቲክ ፕሮጀክት ሲስተም ጋር መስመራቸውን የሚያገናኙ ሌሎች የባህር በር ከሌላቸው 13 አገሮች መካከል ቦትስዋና፣ ቡሩንዲ፣ መካከለኛው የአፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ቻድ፣ ኢትዮጵያ፣ ሌሴቶ፣ ማላዊ፣ ሩዋንዳ፣ ስዋዚላንድ፣ ኡጋንዳ፣ ዛምቢያ እና ዚምባቡዌ ይገኙበታል፡፡ ይህ ፕሮጀክት የመላው አፍሪካ ዙሪያን በጠቅላላ ያካለለ የፕሮጀክት አካል ስለሚኖረው ከፍተኛ ደረጃ ያለው የፋይበር ኦፕቲክስ ኔትወርክን ይፈጥራል፡፡ የፋይበር ኦፕቲክስ ኬብሉ ዝርጋታ የአካባቢውን የቴሌኮሙኒኬሽን መስክ የሚቀይር ነው፡፡ የአፍሪካ ልማት ባንክ ለፕሮጀክቱ የሚያቀርበው ገንዘብ በዌስት አንዲያየን ኦሺን ኬብል ካምፓኒ በኩል 14.54 ሚሊዮን ዶላር በመጀመሪያ በጥር ወር የተፈቀደ ነው፡፡ የፕሮጀክቱ ግንባታ ባለፈው ወር የተጀመረ ሲሆን ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ በሥራ ላይ የሚውለው እ.ኤ.አ በ2010 ደቡብ አፍሪካ ውሰጥ በሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ወቅት ነው፡፡ የአፍሪካ ልማት ባንክ፣ የፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ፣ የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ፣ የጀርመን ልማት ባንክ፣ የአለም ባንክ ግሩፕ የሆነው ኢንተርናሽናል ፋይናንስ ኮርፖሬሽን በጋራ 70.7 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የሚሸፍኑ ሲሆን የአፍሪካ ልማት ባንክ የመጀመሪያውን 14.5 ሚሊዮን ዶላር ብር ሰጥቷል፡፡ የፕሮጀክቱ ጠቅላላ ወጪ 225 ማሊዮን ዶላር ነው፡፡ በጠቅላላው 25 የግል የቴሌኮም ኩባንያዎችም በሚዘረጋው የኬብል ዝርጋታ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡ ፕሮጀክቱ አገሮች በተናጠል ለቴሌኮም የሚያወጡት የኢንቨስትመንት ወጪ የሚያስቀሩና በአነስተኛ ደረጃ በቴሌኮም ቢዝነስ ውስጥ ለሚሳተፉ ኢንቨስተሮች አመቺ ነው፡፡ የኬብል ዝርጋታው የኢንተርኔት የትራፊክ መጨናነቅን በመቀነስ ለግንኙነት አመቺ ከመሆኑም በላይ አፍሪካ ከተቀረው ዓለም ጋር በቀላሉ በቴሌኮም እንድትገናኝ የሚያደርግም ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን በመላ አገሪቱ የፋይበር ኦፕቴክስ ኬብልን ለመዘርጋት እየተንቀሳቀሰ ሲሆን ከአዲስ አበባ በስድስት አቅጣጫ ዝርጋታ መጀመሩም ይታወቃል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |