Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow የኢትዮጵያ አየር መንገድ...
የኢትዮጵያ አየር መንገድ... Print E-mail
Sunday, 20 April 2008
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመንግሥት ጋር እየተደራደረ ነው

በአውሮፕላን የነዳጅ ምርት ላይ የተጣለውን 30 በመቶ ኤክሳይዝ ታክስ ትክክል አለመሆኑን በመግለጽ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ታክሱ እንዲነሳለት ከመንግሥት ጋር እየተደራደረ መሆኑን አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የአየር መንገዱ ከፍተኛ ኃላፊ ለሪፖርተር ጋዜጣ ገለፁ፡፡

በአየር መንገዱ ላይ የተጣለው ታክስ ለከፍተኛ ኪሳራ የሚዳርገው መሆኑን የጠቆሙት እኚህ ኃላፊ  አንድ እርምጃ ካልወሰደ በስተቀር በዘርፉ ተፎካካሪ ሆኖ መቀጠል እንደሚያስቸግር ተናግረዋል፡፡

ኤክሳይስ ታክስ ባልተጣለበት ጊዜ እንኳን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአበባ ምርቶችን ወደ ውጭ ሲያጓጉዝ የቆየው በኪሳራ እንደነበር የጠቆሙት ኃላፊው አሁን የተጣለው የኤክሳይዝ ታክስ ደግሞ ለበለጠ ኪሳራ እንደሚዳርገው አስረድተዋል፡፡

በቅርቡ በወጣው የኤክሳይዝ ታክስ ማሻሻያ አዋጅ ላይ በአውሮፕላን የነዳጅ ምርቶች ላይ በተጣለው 30 በመቶ ታክስ ምክንያት አየር መንገዱ ለኪሳራ እንዳይጋለጥ ለማድረግ መንግሥት አንዳንድ ሁኔታዎችን ለማስተካከል እንደሚሞከር ቢገለጽም ተቃዋሚዎች ግን መንግሥት በነፃ ገበያ እንቅስቃሴ ጣልቃ መግባት የለበትም በማለት ሀሳቡን ተቃውመውታል፡፡ አየር መንገድን በተመለከተ መንግሥት በቀጣይ ሊወስደው ሰላሰበው እርምጃ በግልጽ የተባለ ነገር የለም፡፡

ለረጅም አመታት በአገር ውስጥ ሲያካሂድ በነበረው በረራ በአመት 20 ሚሊዮን ብር ይከስር የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በወሰደው የዋጋ ማስተካከልና በተሳፋሪዎች ቁጥር መጨመር ምክንያት እ.ኤ.አ ከ2006 ጀምሮ ትርፋማ እየሆነ መጥቷል፡፡ ይሁን እንጂ በዓለም የነዳጅ ዋጋ መጨመር ምክንያት አየር መንገዱ ከአለም አቀፉ በረራ ሲያገኘው የነበረው ገቢ በ60 በመቶ መቀነሱ ታውቋል፡፡ ያለፉትን ሁለት ዓመታት አየር መንገዱ ያገኘው የተጣራ ትርፍ 130 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው፡፡ በአመት 300 ሚሊዮን ብር ያህል ለነዳጅ ግዥ ያውላል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 307/95 ባሻሻለበት ወቅት በአውሮፕላን ነዳጅ ላይ 30 በመቶ ታክስ መጣሉ ይታወሳል፡፡      

በኃይሌ ሙሉ
 
< Prev   Next >