| አየር መንገድ በቀጣይ ሦስት ዓመታት... |
|
| Wednesday, 09 January 2008 | |
|
አየር መንገድ በቀጣይ ሦስት ዓመታት የመንገዶቹን ቁጥር ወደ 3 ሚሊዮን ለማሳደግ አቀደ የአገሪቱን የአየር ትራንስፖርት ለማጠናከር የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተለያዩ የአቅም ግንባታዎችን እንደሚያከናውንና በቀጣይ ሦስት ዓመታት ውስጥም አሁን ያሉትን የበረራ መስመሮች ወደ 60 በማሳደግ የሚያጓጉዛቸውን የደንበኞች ቁጥር ወደ 3 ሚሊዮን ለማሳደግ መታቀዱ ተገለፀ፡፡ አዲስ የአቭየሽን አካዳሚ ይገነባል፡፡ የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴር የአገሪቱን ወቅታዊ የትራንስፖርት የሥራ እንቅስቃሴና በቀጣይ 3 ዓመታት ሊገነቡ የታቀዱትን ሥራዎች በማስመልከት ባሰራጨው ሪፖርት ላይ እንዳመለከተው፣ በተለይ የአየር ትራንስፖርቱ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰራበት መሆኑን ያሳያል፡፡ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እቅድ መሰረት በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ግንባታቸው የተጀመሩትን የሰባት ኤርፖርቶች የማጠናቀቅና የአራት አዳዲስ ኤርፖርቶች ሥራ ይጀምራል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጪዎቹ ሦስት አመታት በእቅድ ከያዛቸው ተግባራት መካከል አየር መንገዱ የሚሰጠው የካርጎ ትራንስፖርት አገልግሎት ማስፋፋትና አየር መንገዱ ከገዛቸው ቦይንግ 787 አውሮፕላኖች አብዛኛዎቹን በሁለት ዓመታት ውስጥ የማስገባት ሥራ ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 የአለም አቀፍ በረራ መስመሮቹን ቁጥር ወደ 60 ለማሳደግናየአገር ውስጥ በረራ አገልግሎትም በአዳዲስ አውሮፕላኖች ለመተካት አቅዷል፡፡ በተለይ በምዕራብና ደቡብ አፍሪካ ያለውን የበረራ መስመር በማስፋፋትና በአካባቢዎቹ የበረራ ማዕከል በመክፈት ተፎካካሪነቱን ለማጠናከር የሚያስችለው አሰራር እንደሚከተል ስትራቴጂካል እቅዱ ያሳያል፡፡ እያደገ የመጣውን የነዳጅና የሌሎች የኦፕሬሽን ወጭዎች ለመቋቋም ፊዩል ሄጂንግ፣ኢንተረስት ሄጂንግ እና ሌሎች ወጭ ቀናሽ አሰራሮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚንቀሳቀስ መረጃው አመልክቷል፡፡ ወጪ ሊቀንስባቸውና ተጨማሪ ገቢ ያገኝባቸዋል ተብለው ከታመኑት ሥራዎች መካከል ለማስገንባት በዝግጅት ላይ ያለውና እስከ 500 ሚሊዮን ብር ሊፈጅ ይችላል ተብሎ የታመነበት ባለ አራት ኮከብ ሆቴል አንዱ ነው፡፡ ከዚህ ጎን ለጎንም የአቭየሽን አካዳሚ በቀጣዩ ሁለት ዓመት ውስጥ ገንብቶ በማጠናቀቅ የአየር ትራንስፖርቱን ሊያሳድግ ይችላል ተብሎ የታመነበት ሥራ ይሰራል፡፡ ከዚህም ሌላ የ ካርጎ ተርሚናል የ ሜይንቴናንስ ሃንገር ግንባታና .. 737 እና ..-575 አውሮፕላኖች የምስለ በረራነ (ሲሙሌተር) ግዥና ግንባታ ፕሮጀክት መጠናቀቁንም አመልክቷል፡፡ የድርጅቱን የአየር ትራንስፖርት አቅርቦትና ያጓጓዘውን ትራፊክ መጠን በማሳደጉ ረገድም ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ለገበያ ያቀረበው የመንገደኛ አቅርቦት (አቬይላብል ሲል) በአማካይ 25 በመቶ ሲያድግ የጭነት አቅርቦቱን (አቬይላብል ቶን ኪሎሜትርስ) ደግሞ በ21 በመቶ አሳድጓል፡፡ ያጓጓዘው የደንበኞች ቁጥር በአማካይ 16 በመቶ ማደጉንና የተጓጓዘው የጭነት መጠን ደግሞ በ14 በመቶ አድጓል፡፡ ወደፊት አቅርቦት ለማሳደግ ይረዳው ዘንድም ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ የአስር ቦይንግ 787 አውሮፕላኖች የግዥ ስምምነት ከቦይንግ ኩባንያ ጋር መፈራረሙን፣ እንዲሁም አስር የፓይለት ማሰልጠኛ አውሮፕላኖች ግዥ መጠናቀቁን ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |