Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow “ለወደፊቱም የዓለም አቀፍ...
“ለወደፊቱም የዓለም አቀፍ... Print E-mail
Sunday, 20 April 2008
ImageImage“ለወደፊቱም የዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በሌሉበት ምርጫ አንወዳደርም” አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

“አብዛኛዎቹ አስፈፃሚዎች የኢህአዴግ አባላት ናቸው” ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ

የኦፌዴን ሊቀመንበር አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ለወደፊቱም ፓርቲያቸው ዓለም አቀፍ ታዛቢ በሌለበት ምርጫ እንደማይወዳደር አሳውቀው፣ በምርጫ አቋርጦ  ህጋዊና የተለመደ መሆኑን ለሪፖርተር ገለፁ፡፡ የህብረት ሊቀመንበር ፕ/ር በየነ በበኩላቸው አብዛኛዎቹ አስፈፃሚዎች የኢሕአዴግ አባላት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ባለፈው አሁድ የተካሄደው የክልል አስተዳደር ምክር ቤትና የፓርላማ ማሟያ ምርጫ ተሳትፎ በዛሬው ቀን በሚካሄደው የአካባቢ ምርጫ ላለመወዳደር በመወሰን ራሱን ያገለለው ኦፌዴን፣ ይህንን እርምጃው ተከትሎ ምርጫ ቦርድ በጉዳዩ ላይ የሰጠው “ህጋዊ አይደለም” የሚለውን መግለጫ ተቃውመዋል፡፡

ምርጫ  በፊት ቀደም ብሎ በምርጫ ቦርድ አስፈፃሚዎችና በኢሕአዴግ ካድሬዎች በድርጅታቸው አባላትና ዕጩ ተወዳዳሪዎች ላይ ከፍተኛ ወከባና እንግልት እየተፈፀመበት እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲገልፅ የቆየው ኦፌዴን፣ ባለፈው እሁድ በተካሄደው የመጀመሪያ የምርጫ ፕሮግራም ከተሳተፈ በኋላ “ሁኔታው ተባብሶ ቀጥሏል” በማለት በዛሬው ቀን ከሚካሄደው የአካባቢ ምርጫ ራሱን ማግለሉን ባለፈው ሮቡዕ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ አድርጓል፡፡ በመግለጫው “ዜጎች ያለመሸማቀቅ በአገራቸው የፈለጉትን የፖለቲካ ድርጅት የመደገፍ፣ የመምረጥና አባል የመሆን መብታቸው ተጠብቆ ስልጣን በነፃና በፍትሃዊ ምርጫ እንዲገኝ” የሚል የፓርቲው ዋና ዓላማ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

መግለጫው ምርጫ እየተቃረበ ሲመጣ በአባሎቻቸው ላይ የሚደርሱት ወከባዎችና እንግልቶች ከመቼውም ጊዜ በላይ ተባብሶ መቀጠሉን ያትታል፡፡ በመግለጫው ፓርቲው ተፈፅሞብኛል ያላቸውን ወከባዎች በዝርዝር ያስቀመጠ ሲሆን ከእነዚህ መካከል የሚወዳደሩ  ወዳልታወቀ ቦታ ተወስደው ኢሰብዓዊ ድርጊት የተፈፀመባቸው እንደሆነ፣ ወኪሎቻቸውና ዕጩ ተወዳዳሪዎቻቸው በወረዳ አስተዳዳሪዎች መታሰራቸው፣ ኦፌዴን ይመርጣሉ ተብለው የተገመቱ ግለሰቦች እንዳይመዘገቡ መዳረጋቸው፣ አባሎቻቸው በፈጠራ ወንጀል ተከሰው ለእስር መዳረጋቸው፣ ዕጩ ተወዳዳሪዎቻቸው በማስፈራራት፣  መሬት በመስጠት ከምርጫ ውጪ እንዲሆኑ መደረጋቸው ይገኙባቸዋል፡፡

እነዚህ ሁሉ ህገ ወጥ ድርጊቶች  ለዴሞክራሲና ለመልካም አስተዳደር መስፈን ባላቸው ፍላጎት እስከ መጨረሻ የምርጫ ዕለት በሂደቱ ለመቆየት መወሰናቸው በመግለጫቸው አካትተዋል፡፡

ሆኖም በሚያዚያ 5 በተካሄደው ምርጫ ካለፉት ችግሮች በእጅጉ ተባብሰው መቀጠላቸው የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ለገዢው ፓርቲና የምርጫ አስፈፃሚዎችን ኮንነዋል፡፡ በዛሬው  ራሳቸውን  እንዲወስኑ ካስገደዱዋቸው ህገወጥ ድርጊቶች መካከል በርካታ የዕጩ ወኪሎቻቸው እንዳይታዘቡ መታገዳቸው፣ የኢህአዴግ ካድሬዎችና ዕጩ ተወዳደሪዎች በምርጫው ዕለት ቅስቀሳ ሲያካሂዱ መዋላቸው፣ የምርጫ ሳጥኖች ያለ ቁልፍ አስቀምጠው (የጣት አሻራ ቀለም ባለመኖሩ) የገዢው ፓርቲ መራጮች በድጋሚ እንዲመርጡ መደረጉ፣ የወረዳና የቀበሌ አስተዳዳሪዎች በምርጫው ጣቢያ ተቀምጠው መራጮች ኢሕአዴግን እንዲመርጡ ሲያሳስቱ መዋላቸውና በመጨረሻ የድምፅ ቆጠራ ላይ ድምፅ የሰጠ የሕዝብ ቁጥር ከተመዘገበው በላይ ሆኖ መገኘቱን አስረድተዋል፡፡    

ፓርቲያቸው የተወዳደረው ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ ይካሄዳል የሚል እምነት ስላለው ሳይሆን በአገሪቱ የስልጣን ሽግግር በምርጫ እንዲሆን ባለው ፅኑ ፍላጎትና የዴሞክራሲ ጭላንጭል እንዳይጠፋ በማለት መሆኑን ሊቀመንበሩ አክለው ገልፀዋል፡፡ እንደ እሳቸው  ይህንን ተስፋቸውንና እምነታቸውን ሁሉ በገዢው ፓርቲና በምርጫ አስፈፃሚዎች ህገወጥ ድርጊት በመጨናገፉ ከዛሬው ምርጫ ፓርቲያቸው ራሱን ማግለሉን አሳውቀዋል፡፡

ይህንን የኦፌዴን እርምጃ ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው መግለጫ፣ ፓርቲው ከምርጫው ራሱን ማግለሉ ህጋዊና ተገቢ አለመሆኑን ገልጿል፡፡

ንቅናቄው ለአካባቢና ለማሟያ ምርጫ በጠቅላላ አገሪቱ 180  ለአዲስ አበባ ምክር ቤት 16  ማቅረቡን ጠቁሞ፣ በምርጫው ዕለት  በደጋፊዎቹና አባላቱ ላይ ደርሶብናል ያላቸውን ችግሮች በማስረጃ አስደግፎ ማቅረብ አለመቻሉን ጠቅሷል፡፡

ቦርዱ ባወጣው መግለጫ፣ ፓርቲው ቀደም ሲል በወንጀል የታሰሩ ሰዎች አባሎቻችን ናቸው ማለቱ፣ ለዕጩነት ብቁ  ሰዎችን ዕጩ ሆነው እንዲመዘግቡለት መጠየቁና የምርጫ ህጉና መመሪያው ከሚያዘው ውጪ ዕጩዎቹን በቀበሌ ደረጃ ማስመዝገብ ሲገባው ወረዳ ላይ እንዲመዘገቡለት መጠየቁ ተገቢ ያልሆኑ ድርጊቶች መፈፀሙን አስታውሷል፡፡

ከህብረት በጋራ የዕጩዎች የምዝገባ ቀን እንዲራዘም በጠየቁት መሠረት ተግባራዊ መሆኑ የገለፀው የቦርዱ መግለጫ፣  እሁድ የተካሄደው ምርጫ ውጤት ከገመገመ በኋላ የምርጫ ውጤት አዝማሚያ አይቶ ራሱን ማግለሉ አሳውቀዋል፡፡ በመሆኑም በምርጫ ሂደት መካከል እንዲህ ዓይነት እርምጃ ጤናማ አካሄድ እንዳልሆነ በመውቀስ፣ ጉዳዩን አስመልክቶ ከተወያየ በኋላ ለወደፊቱ አቋም እንደሚወስድበት አስገንዝበዋል፡፡

የፓርቲው እርምጃ ህጋዊነት አስመልክተን ላቀረብንላቸው ጥያቄ አቶ ቡልቻ መልስ ሲሰጡ፣ “የተለመደ አካሄድ ነው፣ ምርጫ ቦርድም ፣ህጋዊ ላይሆን ይችላል፣ እንጂ ህጋዊ አይደለም አላለም” ብለዋል፡፡

ትግል ነው፣ ተቋቁማችሁ  አትችሉም ነበር ወይ  ጥያቄ አቅርበንላቸው “እስከ አሁን ችግሩን ተቋቁመን ልንቀጥል ችለናል፡፡ አሁን ግን የማይቻል ችግር ሲደርስበት ማን ይወዳደራል” በማለት ምርጫው የኢሕአዴግ ታዛቢዎች ብቻ ባሉበት ምርጫ ሊሆን ስለማይችል ከሂደቱ ጥለው ለመውጣት መገደዳቸውን አቶ ቡልቻ ተናግረዋል፡፡

“ችግሩ ከዓቅማችን በላይ በመሆኑ መቋቋም አልቻልንም፣ መታገልም አልቻልንም፣ መቀጠል አቃተን”፡፡

ሂደቱን ማቋረጥና ችግሩን ተቋቁሞ ከመቀጠል ለሂደቱ የትኛው ይሻላል? ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱ “መቀጠል ይሻል ነበር፡፡ ይሁን እንጂ አንድ ምርጫ ያለታዛቢ ማካሄድ አይቻልም” ብለዋል፡፡ “ታዛቢዎቻችን ተባረዋል፣ ታስረዋል፣ ተደብድበዋል መታዘብ አልቻሉም፡፡ ታዛቢ የሌለው ምርጫ ሊኖር አይችልም” ያሉት አቶ ቡልቻ ውጤት አይታችሁ አዝማሚያውን ካወቃችሁ በኋላ መሸሽ አይመስልም ወይ ለ..ለው ጥያቄ “መሸሽ ሊሆን አይችልም፡፡ በምርጫው ከቀጠልን ግን ኢሕአዴግ ተወዳድሬ አሸንፌያለሁ ከሚል ብቻውን ተወዳድሮ እንዲያሸንፍ ብለን ነው ከሂደቱ የወጣነው” ብለዋል፡፡

ለወደፊቱስ ምን ሊሆን ይችላል? ለሁለት ተከታታይ ጊዜያት በምርጫ ካልተሳተፋችሁ ምርጫ ቦርድ ሊያግዳችሁ እንደሚችል ይታወቃል፣ ተብለው፣ “ሲጀመር መቼ ምርጫ ተካሄደና? ኢሕአዴግ ብቻውን ተወዳድሮ ራሱ ቆጥሮ ለሚገኝ ውጤት ምርጫ ተብሎ አይጠራም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ለወደፊቱ ፓርቲያቸው ምን እንዳሰበ ጠይቀናቸው፣ ዓለም ዓቀፍና የአገር ውስጥ ታዛቢዎች በሌሉበት  መቼም ቢሆን በምርጫ እንደማይሳተፉ ገልፀዋል፡፡

“በሌሎች አገሮች ሁሉ እንደሚደረግ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች መኖር አለባቸው፡፡ ኢትዮጵያ ታዛቢዎች አልቀበልም የምትልበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ አልተጋበዙም አገር ውስጥ ያሉትም ተከልክለዋል፡፡”

አንድ ምርጫ የምርጫ ደረጃ የሚኖረው ታዛቢ ባለበት ከተካሄደ ብቻ መሆኑ ጠቅሰው፣ “ለወደፊቱም ዓለም አቀፍና የአገር ውስጥ ታዛቢዎች በሌሉበት በሚካሄድ ምርጫ አንወዳደርም” ብለዋል፡፡

አቶ ቡልቻ እርምጃቸው “የዴሞክራሲ ትግሉን የሚያጠናክር እንጂ የሚጎዳ ነው” የሚል እምነት እንደሌላቸው አስረድተዋል፡፡ ይሄም ራሱን የቻለ የትግል መንገድ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ከምርጫው  ብሎ ከሂደቱ ራሱን ያገለለው የኢትዮጵያ ዴሞክራሲዊ ኃይሎች ህብረት በበኩሉ የምርጫ አስፈፃሚዎች  የኢሕአዴግ አባላት መሆናቸውን ለሪፖርተር ገልጿል፡፡ የሕብረቱ ሊቀመንበር ኘ/ር በየነ  “በደቡብ ክልል በሚገኘው በምሥራቅ ባዶዋቹ ዞን 237 ረበ97 ምርጫሪ የኢሕአዴግ አሸናፊ ተብለው የቀበሌ  አባል ሆነው የቆዩ ምርጫ አስፈፃሚ ተብለው ተመርጠዋል” ብለዋል፡፡ በማከልም ፕሮፌሰር በየነ ባለፈው ምርጫ አስፈፃሚ ሆነው አጥፍተው ምርጫ ቦርድ ያባረራቸው በአሁኑ ወቅት አስፈፃሚ ሆነው የሚሰሩ በርካታ ቁጥር ያላቸው ግለሰቦች እንዳሉ ጠቁመዋል፡፡

ዕጩዎቻቸው በተለያዩ ሰበቦች ሆን ተብሎ እንዳይመዘገቡ መደረጋቸው የሚገልፁት ፕ/ር በየነ፣ በአንድ ወቅት በመመዝገቢያ ሰዓት ዕጩዎች ለማስመዝገብ ሄደው 6 ቀበሌዎች ተዘግተው እንደነበር ለምርጫ ቦርድ ቢያመለክቱም ማስከፈት አልተቻለም ብለዋል፡፡

በአባሎቻቸውና ዕጩ ተወዳዳሪዎቻቸው ላይ በተፈፀመባቸው ህገ ወጥ ድርጊትና ወከባ ሳቢያ ከሂደቱ እንዲወጡ መገደዳቸውን ገልፀዋል፡፡

በየማነ ናግሽ
 
< Prev   Next >