Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow አደንዛዥ ዕፅ ሲያዘዋውሩ...
አደንዛዥ ዕፅ ሲያዘዋውሩ... Print E-mail
Sunday, 20 April 2008
አደንዛዥ ዕፅ ሲያዘዋውሩ የተገኙ ተጠርጣሪዎች ተያዙ

የሽሬ እንደሥላሴ ከተማ ፖሊስ አደንዛዥ ዕፅ ሲያዘዋውሩ ደረስኩባቸው ያላቸውን አንድ የውጭ አገር ዜጋና ሁለት ኢትዮጵያዊያን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የከተማው ፖሊስ አስታወቀ፡፡

 

የናይጄሪያን ዜና ጨምሮ ኢትዮጵያውያኑ በቁጥጥር ሥር የዋሉት፣ ከጐንደር ወደ አክሱም ለማለፍ በሽሬ እንደሥላሴ ከተማ ቆይታ ባደረጉበት ወቅት ለፖሊስ በሕዝብ በደረሰው ጥቆማ ነው፡፡ ግለሰቦቹ በተያዙበት ወቅት 5ዐ ግራም ማሪዋና የተባለ አደንዛዥ ዕፅ በኘላስቲክ ጠቅልለው በካልሲያቸው ውስጥ ደብቀው መገኘታቸውን ገልጿል፡፡

ኢዚአ

*                             *                        *

ጽላት የሰረቁ በጽኑ እስራት ተቀጡ

በሰሜን ጐንደር ዞን ዓባት ወረዳ ውስጥ ፅላት የሰረቁና በድርጊቱ የተባበሩ አምስት ግለሰቦች እስከ ዘጠኝ ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ የተፈረደባቸው መሆኑን የወረዳው ማስታወቂያ ፅህፈት ቤት ገለፀ፡፡

በግለሰቦቹ ላይ እስራቱ የተወሰነው በወረዳው ገወጣ ቀበሌ ካለው የጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን መጋቢት 9 ቀን 2ዐዐዐ ጽላቱን መስረቃቸው በማስረጃ በመረጋገጡ መሆኑን፣ እንዲሁም ጽላቱን በመቀበል ዳባት ከተማ ደብቀው የተገኙ ሁለት ግለሰቦች እያንዳንዳቸው በአምስት ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣታቸውን አስታውቋል፡፡

አዲስ ዘመን፣ ሚያዚያ 9 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም.

*                             *                        *

የዘጠኝ ቢሊዮን ብር ኘሮጀክቶች መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች እየተካሄዱ ናቸው

በኢትዮጵያ በአሁኑ ዘጠኝ ቢሊዮን ብር የሚያወጡ ኘሮጀክቶች ከሁለት ሺ በላይ በሚሆኑ ዓለም አቀፍና ሀገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆኑ የልማትና የዕርዳታ እንዲሁም የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች እየተካሄዱ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የድርጅቶቹ ቁጥር ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመር በተለይ የሀገር በቀል የልማትና ዕርዳታ ድርጅቶች ቁጥር በሦስት እጥፍ ማደጉን፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ የልማት አጋሮች በኢትዮጵያ በስፋት ከሚንቀሳቀሱባቸው ክልሎች መካከል ኦሮሚያ፣ አዲስ አበባ፣ አማራ፣ ደቡብ ሕዝቦችና ትግራይ ከፍተኛውን ድርሻ መያዛቸው ተጠቁሟል፡፡

አዲስ ዘመን፣ ሚያዚያ 10 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም.
*                             *                        *

ከኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት ጋር በተያያዘ የስልክ አገልግሎት እየተቋረጠ ነው

የኢትዮጵያ ቴሌኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን 24 ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል በሚያስፈልጋቸው የኔትወርክ ማሰራጫና ማከፋፈያ መሳሪያዎቹ ላይ እያጋጠመ ባለው የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት የተነሳ በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች የስልክ አገልግሎት በከፊል የመቋረጥ ችግር እየተፈጠረ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት ያጋጠማቸው የኮርፖሬሽኑ መሳሪያዎች በማዞሪያዎችና በደንበኞች መካከል የሚገኙ የኦኘቲካል ፋይበር የኬብል ማከፋፈያ ሳጥኖች መሆናቸውን ገልፆ፣ ኃይል ሲቋረጥ በተጠባባቂነት የሚያገለግል ባትሪ እንዳላቸውና፣ ባትሪዎቹ አገልግሎት መስጠት የሚችሉት ለተወሰኑ ሰዓታት ብቻ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ኢዜአ

*                             *                        *

በቅጣት አወሳሰን ላይ በሚፈጠር ሰፊ ልዩነት ሕብረተሰቡ በፍትሕ አስተዳደሩ ላይ አመኔታ ያጣል

ተመሳሳይ በሆኑ የወንጀል ጉዳዮች በተከሰሱ ተጠርጣሪዎች የቅጣት አወሳሰን ላይ ሰፊ ልዩነት መፈጠሩ ሕብረተሰቡ በፍትሕ አስተዳደሩ ላይ ያለውን አመኔታ እንደሚጐዳው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ኘሬዚዳንት አስታወቁ፡፡

ህብረተሰቡ ተመሳሳይ በሆኑ የወንጀል ጉዳዮች በተከሰሱ ተጠርጣሪዎች የቅጣት አወሳሰን ላይ እየታየ ባለው ሰፊ ልዩነት የተነሳ በወንጀል የተጠረጠረ ሰው ምን ሊጠብቀው እንደሚችል መገመት የማይችሉበት ሁኔታ መድረሱን አብራርተዋል፡፡

ኢዜአ

 
< Prev   Next >