Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow አፍሪካውያን አርቲስቶች የጥበብ ሥራቸውን አቀረቡ
አፍሪካውያን አርቲስቶች የጥበብ ሥራቸውን አቀረቡ Print E-mail
Sunday, 20 April 2008
ከርቀት ሲታይ፣ ነጩ መኝታ (አልጋ) በአበባ አሸብርቆ ሲታይ ለተመልካቹ ሳቢ ነው፡፡ ቀረብ ብለው ሲያዩት ደቡብ አፍሪካዊው ሥነ ጠቢብ ኢሎና አንደርሰን የትራሱ ልብስ ጥልፍ ጠበንጃና አበባ ያለበት ጥይት የበሳው ቀዳዳ የሚመስል አለበት እንደ ጆዲ ፋይንበርግ አዘጋገብ፡፡

 

በየዕለታዊ ሕይወት የሚከሰተው የማይፈለገው ሁከትና ጭብጡ አድርጎ የተነሳው በኒው ኢንግላንድ የተዘጋጀው የሥነ ጥበብ ሥራዎች ዐውደ ርዕይ አምስት የዘመኑ አፍሪካውያን ሥነ ጠበብት ለማኅበራዊ ኢፍትሐዊነት የሰጡት ምላሽ ነው፡፡

ዐውደ ርእዩ እስከ ግንቦት 3 ቀን 2000 ዓ.ም ድረስ በሳውዝ ሾሬ በኮሃሴት የጥበብ ማዕከል ይቀርባል፡፡

ትርዒቱ ሥዕሎች፣ ኢንስታሌሽን አርት፣ ግራፊክ ዲዛይንና ቪዲዮን ሲያካትት አቅራቢዎቹ ከሱዳን ካሊድ ኮዲ፣ ከዚምባብዌ ቻዝ ማቪያኔ-ዳቪዝ፣ ከኢትዮጵያ ሳሌም መኩሪያና እዝራ ውቤ ናቸው፡፡

በእያንዳንዱ የጥበብ ሥራ፣ ጥነ ጠበብቱ ስለ ረሃብ፣ ስለመፈናቀል፣ ፖለቲካዊ ተጽዕኖ፣ ጦርነት፣ ደፈራ (መድፈር"፣ የሕዝብ ጅምላ እልቂት (ጄኖ ሳይድ) ተንፀባርቋል፡፡

"አስጨናቂና አስደንጋጭ ታሪኮች ሰምተናል፡፡ ግን በሐሳብ ደረጃ የተረዳነው ነው፡፡ ሥነ ጥበቡን ስትመለከት ግን ድርጊቱ ከተፈጸመበት ሁነኛ ሥፍራ ጋር የሚያቆራኝህ ገጠመኝ ታገኛለህ" በማለት አርቲስቱ ካንዲስ ኮርቢ ገልጿል፡፡

ሁለንተናዊ ቁሶችን እንደ አልጋ (መኝታ"ና ልብስ በመጠቀም አርቲስቶቹ በተመልካቹና በሰለባዎች መካከል ግንኙነት እንዲኖር አጽንኦት ሰጥቶበታል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ያለው ሱዳናዊው ካሊድ ኮዲ በነተቡና ባደፉ አልባሳት በአገሩ ሰዎች ላይ የደረሰውን ቶርቸርና ግድያ አመልክቷል፡፡

የኢንስታሌሽን ሥራው በዳርፉር በጃንዳዊድ ስድስት ልጆቿ ለተፈጁባት እናት መታሰቢያ ሆኗል፡፡

ኢትዮጵያዊው ሠዓሊ እዝራ ውቤ "ኤክሶደስ" በተሰኘው ሥራው ብዙኃኑን ሕዝብ ደኅንነቱ ፍለጋ በተለያየ አቅጣጫ ሲንቀሳቀስ የሚያሳይ ነው፡፡ በሥራው ውስጥ የቀለም አጠቃቀሙ ደማቅ ቀይ፣ ብርቱካናማና ወርቃማ ሆኖ በቀውስ ውስጥ ያለውን ብርታትና ውበት ገልጾበታል፡፡ እዝራ ከኢትዮጵያ የተጓዘ ሲሆን በማስ የአርት ኮሌጅ ከፍተኛ ትምህርቱን እየተከታተለ ነው፡፡

የፊልም ደራሲዋ የፕሮፌሰር ሳሌም መኩሪያ "ረፕቸርስ፡ ኤ ሜኒ ሳይድድ ስቶሪ" የድሮ ምስሎችና በቅርብ ጊዜ የተቀረጹ ምስሎች በሦስት ስክሪኖች ቀርበዋል፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሐይማኖት መነሻን የያዘ ሲሆን የኢትዮጵያ ውስብስብና በርካታ የታሪክ ክፍሎችና ማኅበረሰብ ይገልጻል፡፡

አገሪቱ ከቅኝ ገዢዎች ከተጠበቀችበት ጊዜ በኋላ ኢትዮጵያ ዘውዳዊ ሥርዓቷን ማስወገዷ፣ ረሃብ፣ የማርክሲስት-ሌኒኒስት መንግሥት ቀንበር ሆኖ እንደተጫነባት፣ እንዲሁም ከተገንጣይ እንቅስቃሴዎች ጋር ጦርነት ማካሄዷ ታይቷል፡፡

"ማለቂያ የሌለው ልዩ ልዩ ጭብጦችን ይዟል" ያለው በቦስተን የአፍሮ አሜሪካ አርቲስቶች ሙዚያም ብሔራዊ ማዕከል ዳይሬክተር ጋይተር ነው፡፡ ሙዚየሙ ዐውደ ርዕዩን ከግንቦት 24 እስከ ሐምሌ 20 ለማሳየት እቅድ አለው፡፡

ከፕሮፌሰር ሳሌም ምስሎች ውስጥ ሴቶች በጅምላ መቃብር አካባቢ ነጠላቸውን አዘቅዝቀው ሲላቀሱ፣ የተወዳጅ ወገኖቻቸውን መጥፋት፣ አንዷ ፊቷን ከካሜራ ከልላ ስለ አስከፊው የኤድስ በሽታ ስታወጋ፣ ሌላዋ ሴት ስለ ተረሸነው ልጇ ስትናገር ያሳያል፡፡

"ረፕቸርስ" የተሰኘው ሥራዋ የሰውን መልካም ተዛምዶና ጤናማ ያልሆነ ክስተት ገጽታን ያሳያል፡፡

በዌሌስሊ ኮሌጅ የሥነ ጥበብ ፕሮፌሰር ሳሌም መኩሪያ በርካታ ፌሎውሺፕስና ሽልማቶችን ያገኙ ሲሆን፣ በዓመት ሁለት ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የኢትዮጵያውያን ዐውደ ሕይወት የመሰነድ (ዶክመንታሪ የመሥራት) ሥራቸውን ይቀጥላሉ፡፡

ፕሮፌሰሯ "ምስሎችን ማቅረብና እነርሱው እንዲገልጹ ማድረግ እንጂ ሰዎች ምን እንደሚያስቡ ለመናገር አልሻም፡፡" ብለዋል፡፡

ፕሮፌሰር ሳሌም በቅርቡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም "ኢሜጂንግ ኢትዮጵያ" በሚል ርእስ ጥናታዊ ፊልም ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡
በጋዜጣው ሪፖርተር

 
< Prev   Next >