|
Sunday, 20 April 2008 |
|
ሥርግው ገላው
በሪፖርተር ጋዜጣ ኪንና ባህል ገጽ "ጥቂት ነጥቦች ስለክብረ ነገሥትና"". በሚል ርእስ ረቡዕ ሚያዚያ 1 ቀን 2000 ዓ.ም የወጣውን ወዳጄ ራንሐኮህን ከቴላቪቭ በድረ ገጽ ልኮልኝ ተመለከትኩት፡፡
ሔኖክ በክብረ ነገሥት ሥራዬ መስተካከል ያለባቸውን ሁለት ነገሮች አመላክተዋል፡፡ ሁለቱም ተገቢ አስተያየቶች ናቸው፡፡
1. "የአማርኛው የፊደል አጠቃቀም በ1973 ዓ.ም የቀድሞው የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አካዳሚ በረቂቅ ደረጃ በወሰነው የፊደል ገበታ መሠረት የተሠራ፣ ሕጋዊ የአካዳሚ ውሳኔ ባልተሰጠበት ፊደላቱን የቀናነሰ በመሆኑ፣ በተለይም የመጽሐፉ ርእስ በኩሩን ግእዝ ያከበረ ሳይሆን፣ ባልተጻፈበት ፊደል የተጻፈ በመሆኑ ብዙዎችን አላስደሰተም፡፡" የሚለው አስተያየት ነው፡፡
ይህ ጉዳይ በየጊዜውና በየቦታው በተደጋጋሚ ተነስቷል፡፡ እኔ ራሴም በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የተቋም ጉዳይ ሆኖብኝ እንጅ በፊደላቱ መቀነስ ደስተኛ አለመሆኔን ደጋግሜ ገልጫለሁ፡፡ ከማእከሉ ጋር በመመካከር በሁለተኛው እትም ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ይሆናል፡፡
2. ቅሬታቸው ክብረ ነገሥቱ "በዐረብኛውም መጽሐፍ ከወንጌላዊውና የሁላችንም መምህር ከሆነው ከማርቆስ መንበር በ409 ዓመተ ምሕረት የቅጽል ስሙ ላሊበላ በሆነው በንጉሥ ገብረ መስቀል ዘመንና በቸሩ ጳጳሳችን በአባ ጊዮርጊስ ዘመን ከቅብጢ ቋንቋ ወደ ዐረብኛ ቋንቋ ተረጎምናት """ የሚለውን ሳብራራ "409 ዓ.ም የሚለው ከላሊበላ ዘመነ መንግሥት ጋር አይቀራረብም፡፡ ይልቁንስ ዓመተ ሒጅራ ይመስላል፡፡ ሒጅራ የሚጀምረው በ622 ዓ.ም ነው፡፡ 622ቲ409 " 1031 ይሆናል፡፡" ያልኩት እንዲስተካከል የሰነዘሩት አስተያየት ነው፡፡
ሔኖክ "በኢትዮጵያ ባሕረ ሐሳብ ዓመተ ምሕረት በሚል መጠሪያ የሚታወቅ ከዐቢይ ቀመር (532 ዓመት) ጋር የሚዛመድ አቆጣጠር አለ፡፡ ዘመነ ላሊበላ ወደ ዓመተ ዓለም ለውጦና ለ532 አካፍሎ የሚገኘው ዓመተ ምሕረት" ይባላል በማለት የሰጡት አስተያየት የጽሑፋቸው ዋና ጭብጥ ነው፡፡
ጉዳዩን ግልጽ ለማድረግ እኛ ዛሬ "ዓመተ ምሕረት" የምንለው የግእዝ ሥነ ጽሑፎች "ዓመተ ሥጋዌ" የሚሉትን ነው፡፡ ይህም ማለት ዓመተ ምሕረት ሲሉ ከዛሬው የእኛ ዓመተ ምሕረት የተለየ አቆጣጠር ነው የሚሰጡት፡፡ የግእዝ ሥነ ጽሑፎች ዓመተ ምሕረት በየጊዜው ስለሚለዋወጥ አጥኝዎችን ሁሉ ግራ ሲያጋባ ቆይቷል፡፡ በምሳሌ ላስረዳ፡፡
ሔኖክ መጽሐፉ እንደታተመ ክብረ ነገሥት ከናዝሬት ይስሐቅ እስከ አዲስ አበባ ሥርግው በሚል ርእስ "ክብረ ነገሥት በዘመነ ማርቆስ ወንጌላዊ፣ በ46 ዓ.ም በፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ዘመንና በፓትሪያርካችን በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ጳውሎስ ዘመን ከግእዝ ቋንቋ ጋር በትይዩ አማርኛውን ተርጉመው እንዲታተም በማድረግዎ፣ እንኳን በአማርኛ የግእዙን ንባብ ለማግኘት በሚያስቸግርበት ሁሉን ማሟላትዎ አምኃ ይገባዎታል፡፡ """". በማለት እንኳን ደስ አለህ ካሉኝ ሰዎች ውስጥ ናቸው፡፡ ምሳሌ ያልኩት ሔኖክ የእኛን 1994 ዓ.ምን "46" ዓ.ም ማለታቸውን ነው፡፡ ይህ ከፍ ሲል የተጠቆመውን የዐቢይ ቀመር ስሌት ለማያውቅ ግራ ማጋባቱ ግልጽ ነው፡፡ ይኸውም በዛሬው ጽሑፋቸው "በኢትዮጵያ ባሕረ ሐሳብ ዓመተ ምሕረት በሚል መጠሪያ የሚታወቅ ከዐቢይ ቀመር (532 ዓመት) ጋር የሚዛመድ አቆጣጠር አለ፡፡ ዘመነ ላሊበላ ወደ ዓመተ ዓለም ለውጦና ለ532 አካፍሎ የሚገኘው ዓመተ ምሕረት ይባላል" በማለት የገለጹት ስሌት መሆኑ ነው፡፡ አባባላቸውን የበለጠ ግልጽ ለማድረግ ዓመተ ምሕረት መሠረት የሚያደርገው ዓመተ ዓለምን ነው፡፡ ከሁሉ አስቀድሞ ዓመተ ዓለም"5500 ቅ.ል.ክቲ """.ድ.ል.ክ. መሆኑን ማስታወስ ይጠቅማል፡፡ ዓመተ ዓለምን ለዐቢይ ቀመር ማለትም 532 ዓመት ማካፈል ሲባል ዓመተ ምሕረት በየ532 አንድ"1) እያለ የሚጀምር አቆጣጠር ማለት ነው፡፡ ይህንን ቀመር ተከትዬ የክብረ ነገሥትን ዓመተ ምሕረት ሳሰላው የክብረ ነገሥት ሥራ የተጠናቀቀው በ1293 ዓ.ም ይሆናል፡ ምክንያቱም 532ቦ12ቲ409"6792-5500" 1293 ስለሚሰጥ ነው፡፡ ይህንን ስሌት ከተቀበልን የሚገርመኝ ተአምረኛው ክብረ ነገሥት ወደ አማርኛ ተተርጉሞ የታተመው ሳይጎድል ሳያተርፍ የመጀመሪያው ሥራ በተጠናቀቀ ልክ በ700 ዓመቱ መሆኑ ነው፡፡ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ከታተመበት 1994 የመጀመሪያ ሥራው የተጠናቀቀበት 1293 ሲቀነስ 700 ይሰጣልና፡፡
ይሁንና ይህ ስሌትም ቢሆን ሙሉ በሙሉ የቀመሩን ችግር ፈቶታል ማለት አይቻልም፡፡ ከሁሉ አስቀድሞ ጸሐፊው ሥራው ተጠናቀቀ የሚለን በላሊበላ ዘመነ መንግሥት ነው፡፡ ላሊበላ ደግሞ እንደነበረ የሚገመተው በ1112 ገደማ ነው፡፡ ስለዚህ 1293 ለላሊበላ ሩቅ ነው፡፡ ቢያንስ 150 ዓመታት ያህል ልዩነት ያሳያል፡፡ 1293 የሚቀርበው ከ1297-1327 ለነገሠው ለዓምደ ጽዮን ነው፡፡
ክብረ ነገሥት የተጻፈው በዓምደ ጽዮን መሆኑን ሁሉም የታሪክ ሰዎች ቢስማሙም ጸሐፊው በዘመነ ዓምደ ጽዮን በማለት ፋንታ ስለ ምን በላሊበላ ዘመን አለ? የላሊበላና የዓምደ ጽዮን የንግሥ ስም ተመሳሳይ (ገብረ መስቀል) ቢሆንም ጸሐፊው ጠንቅቆ ላሊበላ ማለቱ ያለምክንያት አይመስለኝም፡፡ ለእኔ እንደሚመስለኝ በላሊበላ ዘመን የተከናወነው ከቅብጥ ወደ አረብኛ የመተርጎሙ ሥራ ሲሆን በ1293 የተከናወነው ደግሞ አረብኛውን ወደ ግእዝ የመተርጎሙና መጽሐፉን የማስፋፋቱ ሥራ ነው፡፡ መጽሐፉ በአረብኛው ምንባብ ያገኘውን ቀንና የመጨረሻው የግእዙ ሥራ የተጠናቀቀበትን ቀን ቀላቅሎት ይሆን? በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ስሌት ክብረ ነገሥት ዓምደ ጽዮን ከመንገሡ ጥቂት ዓመታት ቀደም ብሎ መጠናቀቁን ያመለክታል፡፡ ይህም የሚያሳየው ክብረ ነገሥትን ያጻፈው ዓምደ ጽዮን ሳይሆን ያዕቢከ እግዚእ የተባለው መስፍን መሆኑን ነው፡፡ ያዕቢከ እግዚእ አክሱማዊና ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት ይገባኛል ባይ ይመስላል፡፡ ምክንያቱም የመጽሐፉ ዋና ትኩረት የሰጠው ከሁሉ አስቀድሞ ለጽዮን (አክሱም"ና ለሰሎሞን ዘርነት ነውና፡፡ ያእቢከ እግዚእ መጽሐፉ በዚህ መልኩ እንዲዘጋጅ ቢጥርም አልተሳካለትም፡፡ ይልቁንም ዓምደ ጽዮን ስሙን ከጽዮን ጋር አስተሳስሮ ዋናው ጽዮናዊና የሰሎሞን እሱ ሆኖ ብቅ ያለ ነው የሚመስለው፡፡ በኋላም ያእቢከ እግዚእ በዓምደ ጽዮን መገደሉን ከሌሎች ምንጮች እናገኛለን፡፡ በመጨረሻ ምሁራን በስሌቶቹና በልዩነቶቹ ላይ አስተያየት ቢሰጡበት ለ2ኛው እትም ዝግጅት የሚያግዘኝ ይሆናል፡፡ ችግሩ አሁንም ሙሉ በሙሉ አልተፈታምና፡፡ |