Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow ከፍተኛ ትምህርቱንና ባለሀብቱን...
ከፍተኛ ትምህርቱንና ባለሀብቱን... Print E-mail
Sunday, 20 April 2008

Image
ፕሮፌሰር ወንድወሰን ታምራት
ከፍተኛ ትምህርቱንና ባለሀብቱን የሚያገናኝ ስትራቴጂ የለም


 ትምህርትና በንግድ ማህበረሰቡ መካከል ጥብቅ ትስስርና በአገር ደረጃ የሚገናኙበት የጋራ መስሪያ ማዕቀፍ ለመፍጠር የሚያስችል ግልፅ  ብሔራዊ ፖሊሲና ስትራቴጂ እንደሌለ ተገለፀ፡፡

በብሪቲሽ ካውንስል ሪጂናል ማኔጅመንት ፕሮግራም "ከፍተኛ ትምህርትና የቢዝነስ ልማት በእውቀት ኢኮኖሚ" በሚል ርዕስ ባካሄዱት ፎረም ላይ የቅድስተ ማሪያም ኮሌጅ ፕሬዚዳንት ተባባሪ ፕሮፌሰር ወንድወሰን ታምራት እንደገለጹት በከፍተኛ  ንግዱ ማህበረሰብ መካከል ያለው ትስስር ደካማ ነው፡፡

በሁለቱ ወገኖች በኩል ያለውን የተቀራራቢነት ሚና ለማስተዋወቅ ያለው እድል አናሳ ሲሆን በአገር ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የንግዱ ማህበረሰብና ኢንዱስትሪዎች የሚገናኙበትን የጋራ መስሪያ ማዕቀፍ በመንግሥት ደረጃ ቀርፆ ያለመንቀሳቀስ ችግር እንዳለ ገልፀዋል፡፡

ጀማሪ ሰልጣኞች ወደ ሥራ እንዲገቡ የሚያስችላቸውን እውቀት እንዲማሩ አጫጭር ኮርሶች በሥርዓተ ትምህርት ውስጥ እንዲካተት ጥያቄ የማቅረብ፣ ተቋሞቹ የንግዱ ማህበረሰብ የሚፈልገውን በማጥናትና በመካከላቸው ያለውን ትብብር ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በከፍተኛ ትምህርትና በንግድ ማህበረሰቡ መካከል አንዱ የሌላውን አስፈላጊነት ያለመገንዘብ ግንኙነታቸውን ቀዝቃዛና ውሱን እንዲሆን ማድረጉን ጠቅሰዋል፡፡

ካለው የኢኮኖሚ አቅም አንፃር ከፍተኛ የሆኑ የንግድ ድርጅቶች፣ የመሥሪያ ቤቶች፣ የኢንዱስትሪ የግብርናና  የሚፈልጉትን የእውቀት፣ የክህሎትና የተግባቢነት ብቃት እንዲያገኙ፤ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም ገበያ ላይ የሚፈለገውን ሰልጣኝ በማሰልጠን በኩል ውጤታማ እንዲሆኑ የንግዱ ማህበረሰብን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተሳሰረ ግንኙነት መመስረት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አብዛኛው ትኩረት በስልጠና ላይ በመሆኑ ለአዳዲስ ፈጠራዎች የሚያግዙ የምርምር ሥራዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ ሆኖም ለምርምር  ገንዘብና ጊዜ አናሳ ነው፡፡

ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን 25 በመቶ የሚሆነውን ጊዜያቸውን ለምርምር ሥራ እንዲውል የሚያስገድድ ሕግ ቢኖርም ከምርምር ጋር በተያያዘ የማበረታቻ ውሱንነት የገንዘብና የጊዜ ችግር እንዳለ ጠቁመዋል፡፡

በአገራችን የኢንዱስትሪ፣ የምርትና የአገልግሎት ዘርፍ ድርሻ  በመሆኑ የእነዚህ ዘርፎች እድገት ሰልጣኞችን የመቀበል አቅም ለማሳደግ እንደሚያስችልም ተናግረዋል፡፡

በሰልጣኞችና  የሰው ሃይል መካከል ክፍተት መኖሩን የጠቆሙት ተባባሪ ፕሮፌሰር ወንድወሰን ገበያ የሚፈልገውንና ተቋማት የሚሰለጥኑበትን ዘርፍ የሚከታተልና የሰራተኞችን ፍላጎት የሚያመላክት ተቋም በሌሎች አገሮች እንዳለና ይህንንም በአገራችን ተግባራዊ  አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አነስተኛ የኢኮኖሚ አቅም ባላቸው አገሮች የሚወጡ ተማሪዎች 60 በመቶ የሳይንስ 40 በመቶ የሶሻል ሳይንስ ክህሎት እንዲኖራቸው ቢጠበቅም ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መቋቋም  የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች እድገት በመኖሩ በአቅርቦትና ፍላጎት መካከል ክፍተት መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡

ሰልጣኝ ተማሪዎች ገበያውን በማጥናት ተጨማሪ የሥራ እድል ያላቸውን በምርጫው ማካተት፣ ተቀጣሪ ሠራተኛ ከመሆን በዘለለ በስራ ፈጠራ ማሳተፉ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀው ለዚህ አጋዥ የሆነ የፈጠራ ሥራ ፈንድ ማቋቋም ወሳኝ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

35 ሚሊዮን የሚሆነው ሕዝብ አነስተኛ ክህሎትና ትምህርት በሚጠይቅ ዘርፍ ላይ መሰማራቱንና በከተማ 10 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ብቻ ከሁለተኛ ደረጃ የዘለለ ትምህርት እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡

ከ45 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝብ አነስተኛ እውቀትና ክህሎትን በሚጠይቁ የንግድ የአገልግሎቶችና አነስተኛ ሥራዎች ላይ ተሳታፊ መሆናቸውን የገለፁት ተባባሪ ፕሮፌሰር ወንድወሰን በአገራችን ካለው የሥራ ዕድል  82.1 በመቶ፣ በጅምላና በችርቻሮ ንግድ 7.6 በመቶ፣ በምርት 3.61 በመቶ፣ በአገልግሎት 5.4 በመቶ እንደሆነና የወጣት ሥራ አጦች ቁጥር በማደግ ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አነስተኛና መካከለኛ የንግድ ዘርፎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሰለጠኑ ተማሪዎችን የመቀበል ፍላጎታቸውም አነስተኛ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በቤዛዊት ሥዩም
 
< Prev   Next >