Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ካረጡ በኋላ የሚጠጡ...
ካረጡ በኋላ የሚጠጡ... Print E-mail
Sunday, 20 April 2008
ካረጡ በኋላ የሚጠጡ ሴቶች ለጡት ካንሰር ቅርብ ናቸው

ካረጡ በኋል አልኮል የሚጠጡ ሴቶች ለጡት ካንሰር የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ እንደሆነ አንድ ጥናት ጠቆመ፡፡

 

በአለም ላይ ሴቶች በከፍተኛ ሁኔታ ከሚሞቱባቸው ምክንያቶች መካከል የጡት ካንሰር አንዱና ዋናው ነው፡፡ ከቅርብ አመታት ወዲህ ሴቶች ጡት ማጥባትን ልማድ በማድረጋቸው የተመጣጣነ ምግብ በመመገባቸው በጡት ካንሰር የሚያዙት ቁጥር ዝቅተኛ እየሆነ ቢሄድም አልኮል መጠጦችን መጠጣት እስካላቆሙ ድረስ በጡት ካንሰር የመያዝ እድላቸው አሁንም ከፍ ያለ እንደሆነ ነው የሆባን ሪፖርት ድረ ገጽ የዘገበው፡፡

አጥኚዎቹ በጥናታቸው ያገኙትን ውጤት እማኝ አድርገው እንደሚያስረዱት አልኮል መጠጦችን መውሰድ አንድ አይነት የሆነ የጡት ካንሰር ያስከትላል፡፡

የጥናት አድራጊዎቹ ዋና አስተበባሪ ጃስሚን ሊው እንደሚሉት ሴቶች የሚጠጡት የአልኮል መጠንና ለካንሰር የመጋለጥ እድላቸው ምን ያህል ግንኙነት እንዳለው ጥናት ተደርጓል፡፡ በጥናቱ መሰረትም የሚጠጡት የአልኮል መጠን በጨመረ ቁጥር ለካንሰር የመጋለጥ እድላቸውም ይጨምራል፡፡ በተለይም ሴቶች ካረጡ በኋላ የተወሰነ አይነት የጡት ካንሰር የማስከተል ባህሪ አለው፡፡

ኤስትሮጅን እና ፕሮጀስትሮን ሁለቱም በሴቶች ሰውነት ውስጥ የሚመነጩ ሆርሞኖች ናቸው፡፡ ሴቶች የማረጥ እድሜ ደረጃ ላይ ሲደርሱ የሚመነጨው የእነዚህ ሆርሞኖች መጠን ይቀንሳል፡፡ በዚህ ወቅትም የእነዚህ ሆርሞኖች አነቃቂ የሆኑ ሴሎች ወደ ካንሰርነት የመቀየር እድል ይኖራቸዋል፡፡ በተለይ ሴቶች በዚህ ጊዜ አልኮል መጠጣትን ካዘወተሩ ሴሎቹ ወደ ካንሰርነት የመቀየር እድላቸው ከፍ ይላል፡፡ ከማረጥ በኋላ በቀን አንዴ የሚጠጡ ሴቶች በጡት ካንሰር የመያዝ እድላቸው ሰባት በመቶ ሲሆን በቀን ሦስቴ የሚጠጡ ደግሞ በካንሰር የመያዝ እድላቸው 51 በመቶ ይሆናል፡፡

ሊው የተሰኙት አጥኚ "አንዲት ያረጠች ሴት አልኮል ጠጣች ማለት ወዲያውኑ ለካንሰር ትጋለጣለች ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን በየቀኑ የአመጋገብ ስርዓቷ አልኮል መጨመሯ በህይወት ዘመኗ አንድ ቀን በካንሰር የመያዝ እድል እንዲኖራት ያደርጋል" ብለዋል፡፡

 
< Prev   Next >