Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪዎች...
የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪዎች... Print E-mail
Sunday, 20 April 2008
የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪዎች ስሙን ለመቀየር ተገደደ

የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪዎች ማህበር ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በተደረገበት ጫና ስሙን ለመቀየር መገደዱን ምንጮች አመለከቱ፡፡

በንግድና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ 314/95 ማህበሩ እንደገና መደራጀት አለበት በሚል የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጫና  ባለኢንዱስትሪዎች ደግሞ በፈለጉት ቅርፅ ለመደራጀት ሕገመንግሥቱ የሚደግፋቸው በመሆኑ እስከዛሬ ሲታገሉ መቆየታቸውን ምንጮቹ አስረድተዋል፡፡

ሚኒስቴሩ ከማህበሩ ጋር ተባብረው ለሚሠሩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጭምር ማኅበሩ ሕጋዊ አለመሆኑን በመግለፅ ደብዳቤ ሲፅፍ መቆየቱን ጠቁሟል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተው ፍትህ ሚኒስቴር ስያሜውን ቀይራችሁ ቅረቡ በማለቱ አባላቱ ተነጋግረው የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱትሪዎች ማህበር የሚለው ስም “ብሄራዊ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪዎች ማህበር” በሚል እንዲተካ ተስማምተው ይኸው ስያሜ ለምዝገባ በቅርቡ ለፍትህ ሚ/ር ቀርቦ ምላሽ እየተጠበቀ ነው ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ስለተቋቋመ የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪዎች ማህበር በዚያ ውስጥ ተካቷል፣ ራሱን ችሎ ሁለተኛ ማህበር መሆን አያስፈልግም የሚል መከራከሪያ በንግድና ኢንዱስትሪ ሚ/ር በኩል መነሳቱን ሆኖም ማኅበሩ ልክ እንደሌሎች ማህበራት በፍትህ ሚ/ር የተመዘገበ በመሆኑ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ም/ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ እንደማይመለከተው ሲያስረዳ መቆየቱን ምንጮቹ ገልፀዋል፡፡

ምንጮቹ አያይዘውም አንድ ባለኢንዱስትሪ በአንድ ወይም ከአንድ በላይ ማህበራት መታቀፍ  የሚከለክለው ምንድነው በማለት ከጠየቁ በኋላ ሚኒስቴሩ በእኛ መልክ የተቋቋሙ ተመሣሣይ ማህበራትን ሳይጠይቅ የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪዎች ማኅበር ላይ ብቻ ትኩረት ማድረግ የፈለገበት ምክንያት ግልፅ አልሆነልንም ብለዋል፡፡

ማኅበሩ በ1984 ዓ.ም የኢትዮጵያ የግል ኢንዱስትሪዎች ማኅበር ተብሎ የተቋቋመ መሆኑን በኋላም ከአዲስ አበባ የግል ኢንዱስትሪዎች ማኅበር ጋር ተዋህዶ የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪዎች ማኅበር በሚል እንደገና መደራጀቱ ተጠቁሟል፡፡ ማኅበሩ  በላይ አባላት እንዳሉትም ታውቋል፡፡

በጋዜጣው ሪፖርተር
 
< Prev   Next >