Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 06th
Home arrow Sections arrow የሚሌኒየሙ ሐውልቶችና...
የሚሌኒየሙ ሐውልቶችና... Print E-mail
Sunday, 20 April 2008
Imageየሚሌኒየሙ ሐውልቶችና መዘክር ዲዛይን ሥራ ተጠናቀቀ

የኢትዮጵያ ሚሌኒየም በዓል አከባባር ብሔራዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት የሴቶች፣ የብሔር ብሔረሰቦችና የአፍሪካ ሕዝብ መታሰቢያ ሐውልቶችን ለማቆምና የቡና መዘክርና የአትሌቲክስ ሙዚየሞችን ለማሰራት የሚያስችል እንቅስቃሴ በማከናወን ላይ ነው፡፡ እስካሁንም በተካሄደው እንቅስቃሴ የሐውልቶቹና የመዘክሩ የዲዛይን ሥራ ተጠናቋል፡፡ በኢትዮጵያ የሜክሲኮ አምባሳደር የአትሌቲክስ ሙዚየሙን የዲዛይን ሥራ ለማከናወን ቃል መግባታቸውን አቶ ሥዩም በረደድ የጽ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አስታወቁ፡፡

 

የአፍሪካ ሕዝብ መታሰቢያ ሐውልትን ለማቆም የታሰበው ከእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያ ከፍ ብሎ የሌኒን ሐውልት ቆሞበት ከነበረው ፊት ለፊት ባለው ደሴት ላይ ሲሆን የሴቶች ሐውልት የሚሰራው ደግሞ ቦሌ መድሃኔዓለም ቤተክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው አደባባይ ላይ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አመልክተዋል፡፡ ከዚህም ሌላ የብሔር ብሔረሰቦቹ መታሰቢያ ሐውልትን መስቀል አደባባይ ወይም ጽሕፈት ቤት አጠገብ ከሚገኘው ደሴት ላይ እንዲሁም መዘክሩን በቦንጋ፣ ሙዚየሙን ደግሞ ቦቆጂ ላይ የማሰራት ሀሳብ መኖሩንና ሙዚየሙ በቆጂ ላይ እንዲሰራ የታሰበው ሥፍራው የበርካታ አትሌቶች መፍለቂያ በመሆኑ ነው ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

አቶ ሥዩም እንዳብራሩት የብሔር ብሔረሰቦችን ሐውልት የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን፣ የአፍሪካ ኅብረትን ሐውልት የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ፣ የሴቶችን ሐውልት የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የቡናውን መዘክር በቡና ንግድ የተሰማሩ ባለሃብቶችና ሙዚየሙን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወጪውን ችለው እንደሚሰሩት አስረድተዋል፡፡

ከሙዚየሙ በስተቀር የሐውልቶቹና የመዘክሩ ሕንፃ ዲዛይን የተከናወነው የጨረታ ውድድር ተካሂዶና በዚህም ውድድር ላይ ተጫራቾች አስፈላጊውን የፋይናንስና የዲዛይን ሥራቸውን አስገብተው ነው፡፡ ከዚህም ሌላ በአሁኑ ወቅት መስቀል አደባባይ ላይ የቆመውና ከአፄ ቴዎድሮስ እስከ ፕሬዚዳንት ግርማ ድረስ ያሉት የአገር መሪዎችን በያዘው ቢል ቦርድ ላይ የነገሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ምስል አለመኖሩን በተመለከተ ተጠይቀው አቶ ሥዩም ሲመልሱ "ቢል ቦርዱ የጽሕፈት ቤቱ ሳይሆን የአንድ ግለሰብ ነው፡፡ ከጽሕፈት ቤቱ ጋር የተገናኘ አይደለም፡፡ አንዳንድ አከራካሪ ነገሮችም አስነስቷል" ብለዋል፡፡

ከአቶ ሥዩም ማብራሪያ ለመረዳት እንደተቻለው ግንቦት 28 ቀን 2000 ሁለተኛው የዛፍ ተከላ ፕሮክራም ይካሄዳል፡፡ ተከላውም የሚከናወነው "ሦስት ዛፍ ለሦስት ሺህ" በሚል መሪ መፈክር ነው፡፡ በዚህም ዘመቻ ያለፈው ዓመት የችግኝ ተከላ ሁኔታ ይገመገማል፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄደውንም በተጠናከረ መልኩ ለማከናወንና በተለይም ወጣቱ ላይ ያተኮረ እንቅስቃሴ እንዲሆን ለማድረግ ታቋዷል፡፡

ግንቦት 28 ቀን 1999 ከዋለው የዓለም አከባበር ቀን ጋር ተያይዞ በተከናወነው የችግኝ ተከላ ዘመቻ ላይ ከ700 ሚሊዮን የሚበልጡ ልዩ ልዩ አይነት የአገር ውስጥ የዛፍ ችግኞች በመላ ኢትዮጵያ ተተክለዋል፡፡ ቀደም ሲል መሠረት በተጣለባቸውና የሚሌኒየም ፓርክ ተብለው በተመረጡ ቦታዎች ከተተከሉት ችግኞች መካከል 50 በመቶ ያህል መጽደቃቸውን ዳይሬክተሩ ጠቁመው "ሁለት ዛፍ ለሁለት ሺህ" በሚል ፕሮጀክት የተተከሉት እነዚሁ ችግኞች የአደጉ አገሮች የሚለቁትን ካርቦንዳይኦክሳይድ በማስመጥ ረገድ ጥሩ አጋጣሚ እንደሚሆኑና አገሪቱም "የካርቦን ክሬዲት" እንዳልጠየቀች አስረድተዋል፡፡

ተከላው የተከናወነው የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር በአምስት ዓመት እቅዱ ውስጥ በብዘት ያፈላቸው ችግኞችን በመውሰድ ነው፡፡ ይህም ጽሕፈት ቤቱን ከወጪ አድኖታል፡፡ ከዚህም ሌላ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በብሔራዊ ደረጃ በየዓመቱ ለማክበር ታቅዷል፡፡ በዚህም ቀኑን ብቻ አክብሮ መዋል ሳይሆን የሰንደቅ ዓላማውን አያያዝ፣ ሥርዓትና አክብሮትን መማር ያስችላል፡፡ የሰንደቅ ዓላማው ቀለሞች አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ጥራትና ደረጃ ሊወጣለትም ይገባል፡፡

"የጽሕፈት ቤቱ የመቆያ ጊዜው በሕግ የተወሰነ ነው" ያሉት አቶ ሥዩም ይህም መስከረም 1 ቀን 2001 ጽ/ቤቱ ሲዘጋ፣ ጅምር ሥራዎቹን ተረክበው የሚያስፈጽሙ ተቋማት እንዳሉ አስረድተዋል፡፡ ስለሆነም የችግኞቹን ተከላ ጉዳይ የግብርናና ገጠር ልማት፣ የሐውልቶቹን፣ የሙዚየሙና የመዘክሩ ጉዳይ የባህልና ቱሪዝም፣ የወጣቶች ማዕከልን ሥራ የወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ሚኒስትሮች ይረከባሉ፡፡

ከአቶ ሥዩም ማብራሪያ ለመረዳት እንደተቻለው የቱሪስት አማራጮች መፈጠር አለባቸው፡፡ ሁልጊዜ ታሪካዊ እያልን አንድ ቦታ ላይ ብቻ ማተኮር የለብንም፡፡ ቱሪስቶች ከየትም መጥተው እንደየስሜታቸው እንዲሄዱ ማድረግ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ የተፈጥሮ ቡና ወይም ቡና በስፋት የሚገኙባቸውን ቦታዎች እንዲጎበኙና ገንዘባቸውንም እንዲያወጡ ማድረግ ይቻላል፡፡  
በታደሰ ገብረማርያም

 
< Prev   Next >