| ውጥረትን መቀነስ |
|
| Wednesday, 09 January 2008 | |
|
እያንዳንዱ ሰው በገዛ እግሩ መቆምና የገዛ ራሱን ችግሮች ራሱ መፍታት ካለበት በመጀመሪያ ደረጃ ውጥረትን መቀነስ መቻል አለበት፡፡ በውጥረት ራሱን ያደከመ ሰው፣ ጭንቀት ይሰፍንበታል፡፡
በምንም ዓይነት መልኩ ስኬታማ ህይወት ሊኖረው አይችልም፡፡ ስኬታማ ለመሆን፣ አእምሮ ሰከን ያለ አስተሳሰብ ሊኖረው ይገባል፡፡ ውጥረት የሌለበት የተረጋጋ አእምሮ ደግሞ፤ ያለውን ክህሎትና ዕውቀት በተገቢው ብቃት ሊጠቀምበት ይችላል፡፡ ሰውና ሕግ የዱር እንስሳት በመካከላቸው ሕግና አዋጅ አልተቋቋመም፡፡ ያለ ሕግ፣ ያለ ዐዋጅ ያለ ደንብና ያለ ሥራት ሊኖሩ ችለዋል፡፡ ሰዎች ግን ያለ ሕግና ያለ ዐዋጅ ያለ ደንብ ሊኖሩ አይችሉም፡፡ በመካከላቸው ያለው ሕግ የፈረሰ እንደሆነ እርስ በርሳቸው ይተላለቃሉ፡፡ ዘራቸው ጨርሶ እንዳይጠፋ ኃይለኛ የሆነ ሰው ተነሥቶ የፈረሰውን ሕግና ዐዋጅ መልሶ በቶሎ እንዲያቋቁምላቸው ያስፈልጋል፡፡ ይህን በሰው ውስጥ ያለውን ያውሬነት ጠባይ አግዶ የሚይዘው ዋና ልጓም ሃይማኖት ነው፡፡ ሂንዱኢስም የተባለው የህንዶች ሃይማኖት ምኞት የኃጢአት ሁሉ ምንጭ መሆኑን ሲያስብ ጽድቅን ለማግኘት ከሁሉ አስቀድሞ ሰው ምኞትን ከልቡ ውስጥ አስወግዶ ሊያጠፋው እንደሚያስፈልገው ያስተምራል፡፡ (ከበደ ሚካኤል፣ የሥልጣኔ አየር፣ 2000) ውበትሽ የኔ ነው.. ውበትሽ የኔ ነው ከልቤ ውስጥ ያለ በነፍሳችን መራመድ ብዙ ጥያቄዎች ትጠይቃላችሁ፡፡ ምሁራን የተባሉትም ፅሁፎቻቸው የሚጀምረው ያለውን ሥርዓት በመርገም፣ ሕጎችን በመጠርጠር፣ ግለኝነትን በሚናፍቁ ቃላት በመታጀብ ነው፡፡ ፀሐፍት እንድትባሉ የግድ ሥርዓቱን መንቀፍ አለባችሁ፡፡ ታላላቆቻችሁ የፈፀሟቸው ተግባራትና የመረጧቸው ጎዳናዎች ካሉ እናንተም ያንኑ ማድረግ አለባችሁ? የምታደርጉትስ ግዴታ ስለሆነ ወይስ ስላመናችሁበት? ሮክፌለር በንግድ ሥራ ብዙ ሀብት ከሰበሰቡ ስማቸው በዓለም ላይ ከታወቀ ባለፀጎች ሁሉ የበለጠ ሆኖ የተገኘው ዦን ዴቪሰን ሮክፌለር የሚባለው ሰው ነው፡፡ እሱም እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ1855 ዓ.ም በአሜሪካ ሔዊት ከሚባል ልዩ ልዩ የምግብ ዕቃ በጅምላ ከሚሸጥ ነጋዴ ዘንድ ተቀጥሮ ሥራ ጀመረ፡፡ ሲቀጠርም መጀመሪያ የተቆረጠለት ቀለብ በወር አምስት ያሜሪካ ዶላር ነው፡፡ በልጅነቱ ያስተምረው የነበረው መምህር ላባቱ ሁልጊዜ እንደዚህ እያለ ይነግረው ነበር ይባላል፡፡ ..ልጅህ መልካም ልጅ ነው ነገር ግን አሳቡ ሰፊ አይደለም፡፡ ስለዚህ የገልባጭነት ሥራ እንዲማር ብታደርገው የሂሳብ ሰራተኛ ረዳት ሆኖ የሚጠቅም አገልግሎት ሊሰጥ ይችላል.. ስለ ተማሪዎቻቸው ጠባይና ወደ ፊትም ሊሆኑ ስለሚችሉት በሚናገሩት ትንቢት የሮክፌለር መምህር ብቻ ሳይሆን የብዙ ትልልቅ ሰዎች አስተማሪዎች ተሳስተው ተገኝተዋል፡፡ ይህም የሚሆንበት ምክንያት ሲያድጉ ትልቅ ሥራ የፈጸሙ ሰዎች አብዛኞቹ በልጅነታቸው ከጓደኞቻቸው የተለየ ብልህነት ያላቸው ሆነው ስለማይታዩ ነው፡፡ የማርቲን ሉተር ኪንግ ፍላጎት ከእናንተ ውስጥ ማናችሁም ቀኔ ደርሶ ሕይወቴ ስታልፍ የተገኛችሁ እንደ ሆነ የቀብሬ ሥነ ሥርዐት ረጅም እንዳይሆን መፈለጌን እንድታውቁልኝ፣ ስለ ሕይወት ታሪኬ የሚናገር ሰው ካገኛችሁ አጠር እንዲያደርገው ንገሩት፡፡ የኖቤልን ሽልማት ስለ ማግኘቴ እንዳይናገሩ ንገሯቸው፡፡ እስከዚህም አስፈላጊ አይደለም፡፡ ሦስት መቶና አራት መቶ የሚሆኑ ልዩ ልዩ ሽልማቶችም እንዳሉኝ መጥቀስ አያስፈልግም፡፡ ቁም ነገር አይደሉምና፡፡ የት የት እንደተማርኩም እንዳይናገሩ ንገሯቸው፡፡ ከመካከላችሁ አንዱ ማርቲን ሉተርኪንግ ጁኒየር ሌሎችን ለማገልገል ሕይወቱን የሰጠበትን ቀን ትውስ እና ትዝ እንዲለው እሻለሁ፡፡ ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር ማንንም ለማፍቀርና ለመውደድ ይጥር የነበረበትን ቀን ከመካከላችሁ አንዱ እንዲያስታውሳት እወዳለሁ፡፡ ስለ ጦርነቱ ባለኝ እምነት ትክክለኛነቱን በማስታወስ የተናገርኩበት ቀን ትውስ ቢላችሁ ደስ ይለኛል፡፡ የተራቡትን ለማብላት የሞከርሁበትን ቀን እንድታስታውሱ ከመመኘቴም በላይ እስር ቤት የሚገኙትን ለማጽናናት የጠየቅሁበትን ቀን እንድታስታውሱ እፈልጋለሁ፡፡ የሰውን ልጅ የሚወድና ሰውን ለማገልገል የተፈጠረ ነው እንድትሉ እሻለሁ፡፡ የማጎ ብሔራዊ ፓርክ ማጎ ብሔራዊ ፓርክ የሚገኘው ከኦሞ ወንዝ በስተምሥራቅ ነው፡፡ የፓርኩ ስፋት 2162 ስኩየር ኪሎ ሜትር 835 ስኩየር ማይል ይሸፍናል፡፡ ከባሕር ወለል በላይ ከፍታው በ450 እና በ2528 ሜት (በ1476 እና 8292 ጫማ) መካከል የሚገኝ ሲሆን ከፍተኛው ቦታ የማጎ ተራራ ነው፡፡ የአየር ሙቀቱ ከ14 እና 41 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ 57-106 ዲግሪ ፋራናይት መካከል ነው፡፡ የዝናብ ወራቶች ከመጋቢት እስከ ግንቦትና ከጥቅምት እስከ ታህሳስ ነው፡፡ የዝናብ መጠኑም በአማካኝ 480 ሚሊ ሜትር 10 ኢንች ይደርሳል፡፡ ጎብኝዎች ብዙ ጊዜ ማየትና ፎቶግራፍ ማንሳት የሚፈልጉት ከንፈራቸውን ለጥጠው በመካከሉ ትልቅ የሸክላ ክብ በማስገባት፣ እንደውበት ምልክትና እንደ ባል ማግኛ ዘዴ የሚቆጥሩትን የሙርሲን ሴቶች ነው፡፡ ይህ ባህል ግን ምን ያህል በአካል ላይ ጉዳትና ስቃይ የሚያስከትል እንደሆነና ጥቅሙንና ጉዳቱን ከጎሣ ተጠሪዎችና ከሚመለከታቸው ባለሙያዎች ጋር በመምከርና ጥናት በማድረግ ጎጅነቱ የሚያመዝን ከሆነ መፍትሄ ሊፈለግለት የሚገባ ነው፡፡ (ጌታቸው ደስታ፣ ቱሪዝም በኢትዮጵያ) አዝማሪዋና የጣሊያኑ ጄኔራል በኢጣሊያ ወረራ ወቅት አዝማሪዎችና አልቃሾች በሚያዩትና በሚያጋጥማቸው ላይ ይገጥማሉ፡፡ ጣሊያኖችን በመልካቸው በልብሳቸው በአመጋገባቸው እየተቹ ይዘፍኑባቸዋል፡፡ ዋና መቀመጫውን ደብረ ብርሃን አድርጎ አማራን በሚያስተዳድረው ጄኔራል ትራኪያ ሥር ..ጎሪ.. የተባለ የመቶ አለቃ ነበር፡፡ ፈሰሴ የምትባል አዝማሪ ጎሪን በቅርብ ታውቀው ኖሯል፡፡ ስለዚህ እንዲህ ብላ ገጠመችለት፡፡ አዝማሪ ፈሰሴ በአርበኞች ጎን ቆማ የምታነቃቃ እንደነበረች ተፅፏል፡፡ ገራገር በፍች የተጨናነቀው ቀን የገና እለት ከማንኛውም ቀን በበለጠ የፍች ማመልከቻ ተፅፎበታል፡፡ ..ኢንሳይድ ድቮርስ.. የተሰኘ የእንግሊዝ ድርጅት 100 የሚደርሱ ለሕግ ጥብቅና የሚሰሩ ድርጅቶችን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ 2..000 ሰዎች ፍች ፈፅመዋል፡፡ ዘ ሰን ጉዳዩን ሲዘግብ ከ5 ትዳሮች በገና እለት አንዱ ተነቃንቋል፡፡ የቤተሰብ ሕግ ባለሙያ የሆነችው ሱዛን ኪንግስተን ..አብረው ጊዜያቸውን የሚያሳልፉ ጥንዶች የመነጋገር እድል ስለሌላቸው ጉዳዮቹ ይሸፋፈናሉ፡፡ ነገር ግን በገና እለት ረጅም ጊዜያትን አብረው ስለሚያሳልፉ ችግሮቹ ግልፅ ይሆናሉ፡፡ እርግጥ ነው የቤተሰብ ጣልቃ ገብነትና የገንዘብ ጭቅጭቆች ተፅዕኖ ይፈጥራሉ፡፡ የሆነ ሁኖ በገና እለት ጥንዶች ለችግሮቹ መፍትሄ ለመስጠትና አዲስ ህይወት ለመጀመር ይነሳሳሉ.. በማለት የፍችውን ምክንያት ለማስረዳት ሞክራለች፡፡ ወጣቷ የአፍላ ወጣቶች መግባቢያ አዘጋጀች አንዲት የት/ቤት ወጣት የአፍላ ወጣቶችን መግባቢያ መመሪያ በፅሁፍ አዘጋጀች፡፡ ለዚህ ያነሳሳትም ቤተሰቦቿ ጋር መግባባት ባለመቻሏ ነው፡፡ የ13 ዓመቷ ሉሲ አመሮንገን የአፍላ ወጣቶች መግባቢያ መመሪያ ከኤ እስከ ዜድ በሚል ርዕስ ያወጣች ሲሆን እንደ ዘ ሰን ዘገባ መመሪያው 300 ቃላትን አካቷል፡፡ ወጣቷ ..መመሪያው ግራ መጋባትን እንደሚያስወግድ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ቤተሰቦች አፍላ ወጣቶችን የተለየ ቃል እንዳይጠቀሙ ተፅዕኖ ያደርጋል፡፡ ይሄ ግን ስህተት ነው፡፡ በየቀኑ ቀለል ያሉ ብዙ ቃላት ይፈጠራሉ፡፡ ፈጣሪዎቹን ልናመሰግን እንጅ ልንኮንን አይገባም.. ብላለች፡፡ ሱሴክስ አሳታሚ መጽሐፏን ያሳተመው ሲሆን አባቷ ቪክተር መመሪያውን ካዬ በኋላ ..አሁን በተሻለ ሁኔታ ከልጄ ጋር መግባባት እችላለሁ.. ብሏል፡፡ መጽሐፉ እስከአሁን 3000 ኪፒ ተሽጧል፡፡ ሉሲ የተሻሻለውን ቅፅ ድጋሜ ለማሳተም በዝግጅት ላይ ነች፡፡ ለሽማግሌዎችና አሮጊት መከላከያ ከዘራ ተሰራ የማርሻል አርት ባለሙያ የሆነው ኬቪን ጋርውድ ለጡረተኛ ሽማግሌዎችና አሮጊት የሰራው ከዘራ ራስን ለመከላከል እንደሚጠቅም ተናግሯል፡፡ ኬቪን እንዴት ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ስልጠና ሰጥቷቸዋል፡፡ እንደ ዴይሊ ሜይል ዘገባ አንዲት አሮጊት አዲሱን ከዘራ በመጠቀም ሌቦችን በመግታቷ ትምህርቱ ወደ ተግባር እየተለወጠ ነው ብሏል፡፡ ጋርውድ በሳምንት ሦስት ቀን ስልጠናውን ይሰጣል፡፡ ስልጠናው ሰውነት በማሟሟቅ ተጀምሮ የእጅ እንቅስቃሴን፣ የወገብ መተጣጠፍንና የአጠቃላይ ሰውነትን እንቅስቃሴ አቅጣጫ በፍጥነት መለወጥን በመከወን የከዘራውን ትብብር በማግኘት እንዴት ባለጋራን መዋጋት እንደሚችል በማስተማር ይደመደማል፡፡ ኬቪን ..የተወሳሰበ ቴክኒክ የለውም፡፡ መሰረታዊ ትምህርት ብቻ የምንሰጥ ሲሆን በቀላሉ የምታስታውሰው ነው.. ብሏል፡፡ እጩ ወታደሯ በአርቴፊሻል ጡት የተነሳ ተባረረች አንዲት ሴት እጩ ወታደር ከጀርመን ወታደራዊ ማሰልጠኛ በአርቴፊሻል ጡት የተነሳ በመባረሯ ይግባኝ ብላለች፡፡ የ23 ዓመቷ አሌሲጃ ዶርፍማን ..በጣም ተበሳጭቻለሁ፡፡ ወታደር መሆን የዘወትር ህልሜ ነው፡፡ ጡቴን በኦፕሬሽን በማተለቄ ስራዬን ማጣቴ ይገርማል.... ብላለች፡፡ በማከልም ..ከስራዬ እንደተባረርኩ ሲነግሩኝ እንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም፡፡ የወታደሩ የሕክምና ቡድን አባል መሆንና ነፍስ ማዳን እፈልግ ነበር.. ብላለች፡፡ ይግባኙን የተቀበለው የወታደሮች አለቃ ጉዳዩ በድጋሚ እንደሚታይ ግልጽ አድርጓል፡፡ የጦሩ ቃል አቀባይ ሄራልድ ካመርባወር ..ሕጉ የወጣው እየጨመረ የነበረውን የጉዳት አደጋ ለመከላከል ነው ከ10 ዓመት በፊት የወጣ ሕግ በመሆኑና አሁን ጉዳዩ ያን ያህል አንገብጋቢ ባለመሆኑ ልዩ ሁኔታዎችን ለመመልከት እየተዘጋጀን ነው.. ብለዋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |