| በ5 ሚሊዮን ብር ወጪ... |
|
|
| Wednesday, 23 April 2008 | |
|
በ5 ሚሊዮን ብር ወጪ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ይከበራል
በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ “የሰንደቅ ዓላማ ቀን” ግንቦት 30 ቀን 2000 ዓ.ም ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እንደሚከበር ታወቀ፡፡ የፌዴሬሽንና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሉን አስመልክቶ የህግ ማዕቀፍ ያወጣሉ፡፡ በአዲስ አበባ ሚሌኒየም ጽ/ቤት የአጠቃላይ ዝግጅቶች ውድድሮችና ትርኢቶች መምሪያ ኃላፊ የሆኑት አቶ ተፈሪ የማነ ባቀረቡት ሀሳብና የፕሮጀክት ሰነድ መነሻነት የሰንደቅ ዓላማ ቀኑ ዘንድሮ ግንቦት 30 እንደሚከበር ታውቋል፡፡ ይህንኑ አስመልክቶ ሚያዚያ 4 ቀን 2000 ዓ.ም አበባ አስተዳደር አዳራሽ በተካሄደው ውይይት የፕሮጀክቱ ተግባራዊነት ተወስኗል፡፡ በውይይቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ስዩም መስፍን፣ የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ ብርሃነ ሀይሉ፣ የቱሪዝምና ባህል ሚኒስትር አምባሳደር መሀመድ ድሪር፣ የፌዴራልና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተወካዮች፣ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ እንዲሁም የብሔራዊና የአዲስ አበባ ሚሌኒየም ጽ/ቤት ሠራተኞች ተገኝተዋል፡፡ በዕለቱ ስብሰባ ላይም በአሉ ግንቦት እንዲከበር ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ የበዓሉ ዓላማ በዴሞክራሲ ግንባታ፣ በልማትና በመልካም አስተዳደር አጀንዳዎች ላይ ህብረተሰቡ ብሔራዊ መግባባት ላይ እንዲደርስ የታለመ መሆኑን አቶ ተፈሪ በተለይ ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልፀዋል፡፡ በህብረተሰቡ ዘንድ የሰንደቅ ክብርና ግንዛቤ እንዲሰርፅ የማድረግ ዓላማ እንዳለ አቶ ተፈሪ አስታውቀዋል፡፡ የበዓሉ አከባበርን አስመልክቶ የብሔራዊና የአዲስ አበባ ሚሌኒየም ጽ/ቤቶች በኃላፊነት እንደሚይዙት ተገል"ል፡፡ ለክብረ በዓሉ ማከናወኛ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚደረግና ወጪውንም የአያት አክሲዮን ማህበር ባለቤት አቶ አያሌው ተሰማ እንደሚሸፍኑ አቶ ተፈሪ ገልፀዋል፡፡ ለበዓሉ ማክበሪያ የሚያስፈልጉ .4 ሚሊዮን ባንዲራዎችን ከኢትዮ ጃፓን ጨርቃጨርቅ ኩባንያ ጋር የግዥ ውል መከናወኑ ተገል"ል፡፡ በዓሉ ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ በብሔራዊ በዓልነት እንዲከበር ውስን የበዓሉ ማክበሪያ ቀንና አጠቃላይ የበዓሉን ሁኔታ አስመልክቶ የፌዴራል ምክር ቤት እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጋራ የሕግ ማዕቀፍ እንደሚያወጡለት አቶ ተፈሪ ገልፀዋል፡፡ በተሾመ ንቁ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |