| በቢፒአር ምክንያት የሚፈናቀሉ... |
|
|
| Wednesday, 23 April 2008 | |
|
በቢፒአር ምክንያት የሚፈናቀሉ ደመወዛቸው አይቋረጥም
በቢፒአር (በመሠረታዊ የአሰራር ሥርዓት ጥናት) ምክንያት ከሥራቸው የሚፈናቀሉ ሠራተኞች ደመወዛቸውን እንደማያጡ የአቅም ግንባታ ሚኒስቴር አቶ ተፈራ ዋልዋ ገለፁ፡፡ የመሥሪያ ቤታቸውን የዘጠኝ ወር ሪፖርት ትናንት በተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት ሚኒስትሩ እንደገለፁት በመሰረታዊ የአሰራር ለውጥ ምክንያት ከሥራቸው የሚፈናቀሉ ሰዎች የተለያዩ ስልጠናዎች ተሰጥቷቸው ሌላ ሥራ እስከሚያገኙ ድረስ ደመወዛቸው እንደማይቋረጥባቸው አስታውቀዋል፡፡ የአሰራር ለውጡ አገርን የሚጠቅም ቢሆንም የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራምን በሚገባ ባለመገንዘብ ለውጡን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሚፃረሩ ዝንባሌዎች በአንዳንድ ተቋማት ላይ መታየቱንም ሚኒስትሩ አክለው ገልፀዋል፡፡ አቶ ተፈራ እንዳሉት የአሰራር ለውጡን መሰረታዊና ፖለቲካዊ መሆኑን በሚገባ ባለመገንዘብ በአንዳንድ ተቋሞች ላይ ተፃራሪ ዝንባሌዎች ታይተዋል፡፡ ለውጡን የማስቀጠል ሚና የሚጫወቱ የትምህርት፣ የምርምር፣ የስልጠናና የማማከር ሥራ ተቋማትም ወደ ለውጡ ፕሮግራም ሳይገቡ ወደ ኋላ መቅረትም ዋነኞቹ ፈተናዎች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የክልሎችን አፈፃፀም በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት ሚኒስትሩ አሁን ያለው የፖለቲካ አመራር ካልተዛባ በስተቀር የኦሮሚያ ክልል በዚህ ዓመት ሰፋ ባሉ ተቋማቱ ለውጥ ማምጣት በሚችልበት አካሄድ ላይ መሆኑን በሪፖርታቸው ገልጸዋል፡፡ የአማራ ክልልም በፖለቲካ አመራሩ አካሄድ ላይ ለውጥ ካልመጣ በስተቀር እንደ ኦሮሚያው አበረታች አፈጻጸም ላይ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ ትግራይ ከቀደሙት ክልሎች ልምድ ወስዶ በሰፊውና በጠንካራ ግፊት በመሥራት ላይ መሆኑንና እስከ ሰኔ ባለው ጊዜ ውስጥ የሙከራ ትግበራ ሊጀመር እንደሚችል ሚኒስትሩ በሀረሪና በድሬዳዋ ግን የፖለቲካ አመራሩ ያዝ ለቀቅ የሚል አካሄድ ስለሚታይ አካሄዱ ካልተለወጠ በስተቀር መሰረታዊ ለውጡን ማምጣት ይችላሉ ብሎ እንደማያስደፍር ገልጸዋል፡፡ የታዳጊ ክልሎችን በሚመለከት ያለውን ሥራ ሊሰራ የሚችል ምርጥ የሰው ተልኮ በፌደራል ደረጃ በመሰልጠን ላይ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሩ በዕቅዱ መሰረት የተንቀሳቀሰውን አበረታች እድገት ያሳየው የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ብቻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የጋምቤላ እና የአፋር ክልሎች ለስልጠና የላኳቸው የሰው ኃይሎች የማይመጥኑ በመሆናቸው ተመልሰው መላካቸውን፣ ከሶማሌ ክልል ግን ስልጠናውን በተመለከተ ምንም አይነት ምላሽ አለመገኘቱን ገልጸዋል፡፡ በኃይሌ ሙሉ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |