Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 07th
Home arrow Sections arrow ኃይሌ ሆራ ሐይቅ ላይ ባለ አምስት...
ኃይሌ ሆራ ሐይቅ ላይ ባለ አምስት... Print E-mail
Wednesday, 23 April 2008
Image
ኃይሌ ገብረ ሥላሴ
ኃይሌ ሆራ ሐይቅ ላይ ባለ አምስት ኮከብ ተጨማሪ ሆቴል ሊገነባ ነው

ግንባታው እስከ 150 ሚሊዮን ብር ይፈጃል


ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ሆራ ሐይቅ ላይ ባለ አምስት የኮከብ ደረጃ ያለው ዘመናዊ ሆቴል ለማስገንባት እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታወቀ፡፡ ሆቴሉ አዋሳ ላይ እየተገነባ ካለው ሆቴል ጋር በዲዛይንም ሆነ በበጀት ተመሳሳይ ነው፡፡

ቢሾፍቱ ለሆቴል ቱሪዝም ተመራጭ አካባቢ እንደሆነች የገለፀው ኃይሌ፤ ሆራ ሐይቅ ላይ ዘመናዊ ሆቴል መገንባት ጠቀሜታው ከፍተኛ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ሆቴሉን ለመስራት እየተካሄደ ያለው ጥናት መጠናቀቁን የገለፀው ኃይሌ፣ በአካባቢው የሚሰጠውን መሬት አጥሮ እንደማያስቀምጥና በቀጥታ ወደ ተግባር በመግባት ለአልሚ ባለሃብቶች አርአያ የሚሆን ሥራ ለመስራት ማቀዱን ተናግሯል፡፡

ወደፊት በተለያየ ኢንቨስትመንት መስኮች በተግባር የሚታይ ሥራ እንደሚሰራ ያስታወቀው ኃይሌ፤ በቀጣይ በኢንቨስትመንት የሚሳተፍባቸው መስኮች ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ በሆራ ሐይቅ ዳርቻ የሚሰራው ሆቴሌ ከ120 እስከ 150 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደሚያወጣ ከኃይሌ ገለፃ ለመረዳት ተችሏል፡፡

በተመሳሳይ ከዓመት በፊት በደቡብ ብ/ብ/ህ/ክልላዊ መንግሥት ፈቃድ ተሰጥቶት በአዋሳ ሐይቅ ላይ እየገነባ ያለው ሆቴል ሲጀመር 5ሺ ካሬ ሜትር ቦታ ነበር፡፡ የክልሉ መንግሥት በተግባር እየተሰራ ያለውን ግንባታ ተመልክቶ በሂደት መሬት በመጨመር 35ሺ ካሬ ሜትር እንዳደረገለት ኃይሌ ገልጿል፡፡

ሆቴሉ በአንድ ጊዜ እስከ አንድ ሺ ተሰብሳቢ የሚይዝ አዳራሽ፣ አራት ሬስቶራንት፣ 250 የመኝታ ክፍሎች፣ የባንክ አገልግሎትን ጨምሮ የተለያዩ የንግድ ቢሮዎች ያካተተ መሆኑንና የሆቴሉ ግንባታ በአንድ ዓመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ኃይሌ ገልጿል፡፡

ዋናው አማካሪው ድርጅት ገሬታ ኮንሰልታንት ሲሆን የውስጣዊ (ኢንቴሪየር) ዲዛይን ተቆጣጣሪ የደቡብ አፍሪካ ኩባንያ ሆቴሉ ሲጠናቀቅ ከማንኪያ ጀምሮ ያለው የሆቴሉን እቃ ሙሉ በሙሉ በማስገባት ሆቴሉን አገልግሎት የማስጀመር ውል ቀደም ሲል መከናወኑን ኃይሌ በተለይ ለሪፖርተር አስታውቋል፡፡

ኃይሌ የክልሉ መንግሥት ቦታ ከመስጠት ጀምሮ ግንባታውን ቀን በቀን በመከታተል ልዩ ማበረታቻ  ተናግሯል፡፡   

በአሰግድ ተፈራ
 
< Prev   Next >