| ደርባ ሲሚንቶ ከዓለም ዐቀፍ ተቋሞች ብድር አገኘ |
|
|
| Wednesday, 23 April 2008 | |
![]() አቶ ነብዩ ሳሙኤል የሼህ መሐመድ አል አሙዲ ከፍተኛ አማካሪና ልዩ ረዳት የአለም አቀፍ አበዳሪ የገንዘብ ተቋሞች፣ በኢትዮጵያ የግል ሴክተር የመጀመሪያ የሚባለውን ብድር ለደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ ለመስጠት ተስማሙ፡፡ የደጀን ሲሚንቶ ፕሮጀክት ከሳምንታት በኋላ ስርጭት ይጀምራል፡፡ ደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ ብድሩን የሚያገኘው፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክ (ADB)፣ ከአለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) እና ከአውሮፓውያን ኢንቨስትመንት ባንክ (EIB) ሲሆን ከሃገር ውስጥ ከአፍሪካ ልማት ባንክ እንደሚገኝበት አቶ ነብዩ ሳሙኤል የፕሮጀክቱ ባለቤት የሼህ መሐመድ አል አሙዲ ከፍተኛ አማካሪና ልዩ ረዳት ገልፀዋል፡፡ ለደርባው ፕሮጀክት፣ የአፍሪካ ልማት ባንክና፣ የአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን፣ 110 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር የብድር ስምምነት ባለፈው ሳምንት ማፅደቃቸውንና በሚቀጥለው ወር ለፊርማ እንደሚቀርብ አቶ ነብዩ ገልፀዋል፡፡ የአውሮፓውያን ኢንቨስትመንት ባንክም ጋር 45 ዶላር ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ 450 ሚሊዮን ብር ብድር ለማግኘት እንደታሰበም ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ የግሉ ኢንቨስትመንት እስካሁን የውጭ ብድር ተገኝቶ የማያውቅ ሲሆን አሁን ግን በደርባ ሲሚንቶ መጀመሩ ወደፊት የሰፋ እድል እንዲኖር እንደሚያደርገው ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡ “አበዳሪ ተቋሞቹም ከሼህ መሐመድ ጋር መስራት እንደ አንድ ሃብት አይተውታል".” ይላሉ አቶ ነብዩ፡፡ ብድሩ ሊፈቀድ የቻለው የደርባው የሚድሮክ ሲሚንቶ ፕሮጀክት ስራ አዋጭነት፣ የባለሃብቱ ተዓማኒነት፣ አስፈላጊነቱ ሁሉ ታይቶና ተቋሞቹ የጠለቀ ክትትል ካደረጉ በኋላ በደረሱበት ድምዳሜ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ለደርባ ሲሚንቶ የተፈቀደው ገንዘብ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን ለአፍሪካ ልማት ባንክ በተጨማሪ በሲሚንቶ ኢንቨስትመንት ላይ ሲሳተፍ የመጀመሪያው መሆኑን አቶ ነብዩ ተናግረዋል፡፡ “ባለሃብቱ ሺህ መሐመድ፣ የብድሩን መፈቀድ አስፈላጊ አድርገው የሚያዩት ለኢትዮጵያውያን ኢንቨስትመንትና የውጭ ለማግኘት አዲስ በር የሚከፍት በመሆኑ ነው".” ይላሉ አቶ ነብዩ፡፡ በሌላ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት ለደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ የማዕድን ፈቃድ መስጠቱን አቶ ነብዩ ገልፀዋል፡፡ የደርባ ሜድሮክ ሲሚንቶ ከመንግሥት ከተሰሩትና ከሼህ መሐመድ ከተዘረጉት ኢንቨስትመንቶች ጭምር፣ በታላቅነቱ ቀዳሚው መሆኑን አቶ ነብዩ አስታውሰው፣ ፕሮጀክቱ 300 ሚሊዮን ዶላር እንደሚፈጅ ጠቅሰዋል፡፡ የደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ፣ ባለፈው ዓመት ጥር ወር፣ ትልቅ ከሚባለው የቻይና ብሔራዊ ግንባታ ዕቃዎች ጋር ተዋውሎ ሥራውን ሳያቋርጥ ከአንድ ዓመት በላይ ግንባታው መከናወኑን በቀሪዎቹ ጊዜያቶች በእቅዱ መሠረት ተጠናቆ በሚቀጥለው ዓመት ሥራ ይጀምራል፤ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል፡፡ ሥራው ሲጠናቀቅ በዓመት 25 ሚሊየን ኩንታል፣ እንደሚያመርት የሚጠበቀው ደርባ ፒቢሲ (70 በመቶ) ኦፒሲ (30 በመቶ) በመባል የሚታወቁትን ሲሚንቶዎች ያቀርባል፡፡ በተጓዳኝ በደርባው ፕሮጀክት ሥር ያሉ ሁለት የሲሚንቶ ፕሮጀክቶች እየተጠናቀቁ መሆናቸውን አቶ ነቢዩ አስታውቀዋል፡፡ አቶ ነብዩ እንደሚሉት አንደኛውና በቀን 4,000 ኩንታል እንደሚያመርት የታቀደው የደጀን ከሦስት ሳምንት በኋላ ሥራውን ይጀምራል፡፡ ሁለተኛው እዚያው ደርባ የተሰራውና በቀን 4000 ኩንታል እንዲያመርት የሚጠበቀው ፕሮጀክት፣ በቀጣይነት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርና ለዋናው ለሲሚንቶ ፋብሪካው ሥራ እንደሚረዳ አቶ ተናግረዋል፡፡ ከፕሮጀክቱ ጋር ተያይዞ፣ የ500 ሠራተኞች መኖሪያ የተሟላ ሕክምና ሆስፒታል፣ ትምህርት ቤትና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ መሥሪያ ቤቶች ተሟልተው የሚሰሩበት ግንባታ እንደሚካሄድ የ50 ኪ.ሜትር መንገድም ሥራ እንደሚከናወን አቶ ነቢዩ ገልፀዋል፡፡ የደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ ሥራው ሲጠናቀቅ አሁን በከፍተኛ ግስጋሴ ላይ ያለውን የሲሚንቶ ዋጋ ሕብረሰሰቡ ሊሸከመው በሚችለው ሁኔታ ሊያስታግሰው እንደሚችልና በከፍተኛ ደረጃ ዝቅ ሊያደርገው ይችላል ተብሎ በእርግጠኝነት እንደሚገመት አቶ ነብዩ ጠቁመዋል፡፡ “በገበያው ዋጋ ፍላጎት፣ ሳይሆን ሼህ መሀመድ ፍላጎት፣ ዋጋው ሕብረተሰቡ ሊሸከመው በሚችለው መንገድ ልማቱን ማፋጠን በሚችልበት ዋጋ በዝቅተኛ እንደሚሸጥ ነው፤ ለእኛ የተሰጠን መመሪያ” ለ500 ቋሚ ሠራተኞች የሥራ እድል የሚፈጥረው ደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ 1000 ለሚሆን ተጓዳኝ ሥራዎችን ለሚሰሩና በየአካባቢው የስርጭቱን ተግባር የሚያከናውኑ 10,000 በላይ ዜጎች የሥራ እድል እንደሚከፍት ዋና አማካሪው ተናግረዋል፡፡ መንግሥት ከኮርፖሬት ታክስ፣ ከቫት ከፍተኛ ገቢ እንደሚያገኝ ሲጠቅሱ ከአዲስ አበባ ቀጥሎ ከፍተኛ መብራት ከሚጠቀመው ደርባ፣ 50 ሜጋ ዋት ስለሚጠቀም የኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን 150 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ እንደሚያገኝ በጥቅሉ ከግማሽ ቢሊየን በላይ ገቢ እንደሚያገኝ ተናግረዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የድንጋይ ከሰል ለማምረት ንግግርና ጥናት እየደረገ መሆኑን አቶ ነቢዩ ሳሙኤል ገልፀዋል፡፡ ከጋዜጣው ሪፖርተር |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |