| ለፌደራል መንግሥት ተጨማሪ በጀት ተጠየቀ |
|
|
| Wednesday, 23 April 2008 | |
|
ካልተዘጉ 229 የባንክ ሂሳቦች 160.6 ሚሊዮን ብር ተገኝቷል
በደመወዝ ጭማሪ ምክንያት ላጋጠመ የገንዘብ እጥረትና በዓመቱ እቅድ ለተያዘላቸው ሥራዎች ተጨማሪ የ1 ቢሊዮን 16 ሚሊዮን ብር የበጀት ማሟያ ተጠየቀ፡፡ ካልተዘጉ 229 የባንክ ሂሳቦች 160.6 ሚሊዮን ብር ተገኝቷል፡፡ ትናንት ሚያዚያ 14 ቀን 2000 ዓ.ም በተወካዮች ምክር ቤት በተካሄደው መደበኛ ስብሰባ ላይ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ እንደሚያመለክተው በደመወዝ ጭማሪ ምክንያት ካጋጠሙ የገንዘብ እጥረቶች በተጨማሪ የጥናት ጊዜያቸው አልቆ ወደ ግንባታ ለመግባት የቅድመ ክፍያ በጀት የተያዘላቸው ሥራዎች ከተያዘላቸው በጀት በላይ የሆኑ ክፍያዎች የተጠየቀባቸው በመሆኑ ተጨማሪ በጀት ሊጠየቅባቸው ችሏል፡፡ በዚህም መሰረት ለካፒታል ወጪ አንድ ቢሊዮን ብር ተጠይቋል፡፡ ለተጨማሪ በጀት ዓመት የሚውለው ወጪም ከተዘጉ የመንግሥት የባንክ ሂሳቦች፣ የመንግሥት ሌተር ኦፍ ክሬዲት ሂሳቦች፣ ወደ አገር ውስጥ በሚገቡ ዕቃዎች ላይ ከተጣለ ሱር ታክስ፣ ከፕራይቬታይዜሽን ገቢ እና መሥሪያ ቤቶች ከሚሰበስቡት የውስጥ ገቢ እንደሚሸፍን ተገልጿል፡፡ አካውንት የከፈቱ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ጊዜ ሳይንቀሳቀሱ ሲቆዩ፣ አንዳንድ መሥሪያ ቤቶች ደግሞ ከሌላ መሥሪያ ቤት ሲዋሃዱ ወይም ሲፈርሱ በተገቢው መንገድ የባንክ ሂሳባቸውን እንደማይዘጉ ለተወካዮች ምክር ቤት አባላት የገለፁት የመንግሥት ተወካይ ለረጅም አመታት በቆዩት የባንክ ሂሳቦች ላይ ጥናት ተደርጎ ካልተዘጉ 229 የባንክ ሂሳቦች 160.6 ሚሊዮን ቀሪ የመንግሥት ገንዘብ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡ አዋጁ ላይ እንደተገለጸው ከተዘጉ የመንግሥት ሌተር ኦፍ ክሬዲት ሂሳቦች 84.5 ሚሊዮን ብር ተጨማሪ ገቢ ተገኝቷል፡፡ በዕቃ ዋጋ መጨመር፣ በስምምነት መፍረስ ግዥው ሳይከናወን በመቅረቱ፣ ወይም ዋጋ በመቀነሱ ገንዘብ በትርፍነት በመኖሩ ገንዘቡ ሳይንቀሳቀስ ዓመታት መቆየቱ በረቂቅ አዋጁ ላይ ተገልጾ ጊዜያቸው ያለፈባቸው የሌተር ኦፍ ክሬዲት ሂሳቦች ተዘግተው እንደተጨማሪ ገቢ እንዲወሰዱ አመልክቷል፡፡ ወደ አገር በሚገቡ እቃዎች ላይ የተጣለን ሱር ታክስ በተመለከተም የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለሥልጣን ከሚያዚያ እስከ ሰኔ 1999 ዓ.ም ድረስ 492.0 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡ ተጠቁሞ ይኸው ብር ለ2000 በጀት ዓመት እንደተጨማሪ ገቢ መያዙ ተገልጿል፡፡ ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች የሽያጭ ገቢ ብር 263.9 ሚሊዮን ብር ገቢ መገኘቱ ተጠቁሞ ይህ ገንዘብ እንደተጨማሪ ገቢ እንደሚወሰድ በረቂቅ አዋጁ ላይ ተብራርቷል፡፡ የኢትዮጵያ ደረጃዎች ባለሥልጣን ከደረጃዎች ምደባ ክፍያ ከሚሰበስበው የውስጥ ገቢ ብር 0.625 ሚሊዮን፣ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ከህዝብ መገናኛ ዘዴዎች ክፍያ ከሚሰበስበው ገቢ ብር 3.955 ሚሊዮን እንዲሁም የትራንስፖርት ባለስልጣን ከመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት ክፍያ ከሚሰበስበው ገቢ ብር 11.447 ሚሊዮን በጠቅላላ ብር 16.026 ሚሊዮን ለ2000 በጀት ዓመት ከታወጀው በጀት በላይ መሥሪያ ቤቶች ይሰበስባሉ ተብሎ ከሚገመተው ገቢ የተያዘ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ የተጨማሪ በጀቱን ረቂቅ አዋጅ አስመልክተው አስተያየታቸውን የሰጡት አቶ ተመስገን ዘውዴ አንድ የመንግሥት ሂሳብ ሲከፈት እና ሲዘጋ የራሱ የሆነ አካሄድ እንዳለው ጠቁመው ካልተዘጉ የባንከ ሂሳቦች ተገኘ የተባለው 160 ሚሊዮን ብር እንዴት ሊገኝ እንደቻለ መጣራት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡ ከሌተር ኦፍ ክሬዲት ተገኘ የተባለው 84 ብርም በአሰራሩ ላይ ሙስና አለበት የሚል ጥርጣሬ ሊያስነሳ እንደሚችል አመልክተዋል፡፡ የኢዴአፓ መድህን ተወካይ አቶ ደረጀ መንግሥቱ በበኩላቸው አዲስ በወጣው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ላይ መንግሥት ለፖለቲካ ፓርቲዎች ድጎማ እንደሚሰጥ የተገለጸ መሆኑን ጠቁመው በተጨማሪ በጀቱ ላይ ለፓርቲዎች የሚሰጥ ድጎማ የታቀደ መሆንና አለመሆኑን ጠይቀዋል፡፡ ረቂቅ አዋጁ ለበጀትና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴዎች በኃይሌ ሙሉ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |