Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 07th
Home arrow Sections arrow ዲያስፖራው ተስፋ
ዲያስፖራው ተስፋ Print E-mail
Wednesday, 23 April 2008
ዲያስፖራው በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ ሁኔታዎች ተመቻችተዋል፡፡ የዲያስፖራን ጉዳይ የሚከታተል ጽህፈት ቤት መቋቋሙ ጥሩ ነው፡፡ ፅህፈት ቤቱ በመቋቋሙ ብቻ ችግሮች ወይም አስፈላጊ ያልሆኑ ውጣ ውረዶች ይወገዳሉ ማለት አይቻልም፡፡ ጠንክሮ መሥራትን ይጠይቃል፡፡ ዲያስፖራውም የድርሻውን ይጠበቅበታል፡፡ ቢሮክራሲው አላንቀሳቅስ አለኝ ብሎ ያቀዳቸውን ከዳር ሳያደርስ መቅረት የለበትም፡፡

በሪፖርተር ጋዜጣ ሚያዚያ 12 ቀን 2ዐዐዐ እትም “ዲያስፖራው ከቀድሞው በተሻለ መልኩ እየተስተናገደ ነው” በሚል ርዕስ ከቀረበው ፅሁፍ ለመገንዘብ እንደተቻለው “ዲያስፖራው ችግር ብሎ የሚያነሳው የተቀላጠፈ መስተንግዶ አለመኖር ነው”፡፡

አብዛኛው ዲያስፖራ የጀመረው እቅድ የማይሳካለት እየመሰለው የሚፈራበት አጋጣሚ አለ፡፡ በአንፃሩም የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ተቋቁመው ወደ ሥራ የገቡት በሥራቸውም ውጤታማ የሆኑ እንዳሉ ግልፅ ነው፡፡ የአብዛኛው ዲያስፖራ  ለመኖሪያ ቤት መሥሪያ የሚውል ቦታ በማግኘት ላይ ያተኰረ ነው፡፡ ቦታ የማግኘት ፍላጎት እንዳለ ሁሉ ለዚህ ሲባል የወጡትን ደንቦችና መስፈርቶችን ማሟላት የግድ ነው፡፡ አብዛኛው ዲያስፖራ ግን ይህንኑ የማሟላት አቅምና ፍላጎት የለውም፡፡

ዲያስፖራ በመሆኑ ብቻ የሚፈልገውን ሁሉ አልጋ በአልጋ እንዲሆንለት ያስባል፡፡ ቦታ ተፈልጎ እስከሚሰጠው ድረስ በመካከሉ ያሉት አሰራሮች ምን ያህል ውስብስብ እንደሆኑ ያለመረዳት ችግር ስላለ ዲያስፖራው ተስፋ መቁረጥ የለበትም፡፡

(ከበደ አሰፋ፣ ከፒያሳ)
 
< Prev   Next >