Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Thursday
Nov 20th
Home arrow Sections arrow ቢዮንሴ ረታች
ቢዮንሴ ረታች E-mail
Wednesday, 09 January 2008
ቤቢ ቦይ የተሰኘው ዘፈኗን ጄኒፈር አርሙር ከእኔ የተወሰደ ሥራ ነው በማለቷ ቀርቦባት የነበረውን የኮፒ ራይት ክስ ቢዮንሴ መርታቷን የቢቢሲ ዘገባ አመልክቷል፡፡

ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ የክስ ክርክሩ የቆየ ሲሆን፣ ቢዮንሴ ..በሥራው ላይ ለተሳተፉት ሁሉ ውሳኔው ተስፋ ሰጭ ነው.. ብላለች፡፡

አርሙር ..አይ ጐት ኤ ሊትል ቢት ኦፍ ላቭ ፎር ዩ.. የሚለውን ዘፈን ለቢዮንሴ ማናጀር በ1995 ዓ.ም ሪከርድ እንዲያደርግላት ሰጥታው እንደነበረ፣ በዚያ ወቅትም ኮፒ እንደተደረገባት የተናገረች ቢሆንም በሂዩስተን የዋለው የቴክሳስ ችሎት የቢዮንሴ ..ቤቢ ቦይ.. ከዚያ በፊት የተሠራ ነው በማለት ውድቅ አድርጐባታል፡፡

 

የአና ፍራንክ ዲያሪ በሙዚቃ ሊቀርብ ነው

በናዚ የማጎሪያ (የኮንሰንትሬሽን) ካምፕ በ1945 አካባቢ የሞተችው አና ያሰፈረችው ዲያሪ (የዕለት ውሎ ማስታወሻ) በስፓኒሽ ሙዚቃ ሊቀርብ ነው፡፡
 
ቢቢሲ እንደዘገበው በየካቲት ወር በ13 ዓመቷ ታዳጊ በሚመራና 22 አባላት ባሉት የሙዚቃ ቡድን ማድሪድ ካልዴሮን ቲያትር ቤት ትርዒቱ ይቀርባል፡፡

የትርዒቱ ዳይሬክተር ራፋኤል አልቬሮ በመድረኩ ዝግጅት ወቅት ከስሜታዊነት የዘለለ የትራጂክ ኦፔራ እንደሚቀርብ ተናግሯል፡፡

የአና ዲያሪ በእሷና በቤተሰቦቿ ውስጥ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ናዚ በአምስተርዳም ያደረሰውን ሰቆቃ የሚገልፅ ሲሆን፣ በዓለም ላይ በሚሊዮኖች እንደተነበበ ይታወሳል፡፡ ..የአና ማስታወሻ.. በሚል በአማርኛ መተርጐሙም ይታወቃል፡፡

 
< Prev   Next >