Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow የምንዛሪ ዋጋ አሁንም እያደገ ነው
የምንዛሪ ዋጋ አሁንም እያደገ ነው Print E-mail
Wednesday, 23 April 2008
የዩሮ ምንዛሪ በአንድ አመት ውስጥ ከ3 ብር በላይ ጨመረ

የውጭ ገንዘቦች የምንዛሪ ዋጋ አሁንም በመጨመር ላይ ሲሆን አማካይ በባንኮች የአንድ ዶላር ዋጋ ዋጋ ወደ አስር ብር፣ የፓውንድ ደግሞ ወደ ሃያ ብር በመጠጋት ሲሆን የዩሮ ምንዛሪ ደግሞ አንድ አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ3 ብር በላይ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

የሰሞኑ የባንኮች የውጭ ምንዛሪ ዋጋ እንደሚያመለክተው የአንድ ፓውንድ መሸጫ 18.84 ብር፣ መግዣ ደግሞ 19.22 ብር ደርሷል፡፡ ተመሳሳይ በሆነ መልኩም የአንድ ዶላር ዋጋ ምንዛሪ ወደ አስር ብር እየተጠጋ ነው፡፡ በሰሞኑ የባንኮች ምንዛሪ የአንድ ዶላር መሸጫ 9.518 ብር መግዣ ደግሞ 9.708 ብር ደርሷል፡፡ ይህም የውጭ ገንዘቦች የምንዛሪ ዋጋ እድገት ሳያቋርጥ እየቀጠለ መሆኑን ያሳያል፡፡

የባንኮች የምንዛሪ ዋጋ ሰንጠረዥ እንደሚያሳየው በሰኔ 1999 ዓ.ም የአንድ ዶላር የመግዣ ዋጋ 9.02 ብር፣ መሸጫ ደግሞ 9.20 ብር የነበረ  በዚህ ወቅት የአንድ ፓውንድ መግዣ ዋጋ 17.91 ብር መሸጫ 18.26 ብር፣ ዩሮ ደግሞ መግዣ 12.11 ብር፣ መሸጫ 12.42 ብር ነበር፡፡

በአሁኑ ወቅት አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ዶላር ከ50 ሣንቲም በላይ ፓውንድ ከ90 ሣንቲም በላይ፣ ዩሮ ከ3 ብር በላይ ጭማሪ አሳይተዋል፡፡

የውጭ ገንዘቦች የምንዛሪ ዋጋ በዚህ ፍጥነት የሚቀጥሉ ከሆነም በወራት ውስጥ ዶላር አስር ብር ፓውንድ 20 ብር፣ ዩሮ ደግሞ ከ16 ብር በላይ ሊመነዘሩ እንደሚችሉ ተገምቷል፡፡

ከሦስቱ ዋና ዋና ገንዘቦች ውስጥ ከዶላር እና ከፓውንድ የበለጠ ፈጣን የምንዛሪ ጭማሪ ያሳየው ዩሮ እንደሆነም ለማወቅ የተቻለ ሲሆንዩሮ ከሌሎች በተለየ የምንዛሪው እያደገ የመጣው ከዶላር  ከፍተኛ የግብይት እየተካሄደበት በመሆኑ እንደሆነ ያነጋገርናቸው የባንክ ባለሙያ ጠቁመዋል፡፡

በዳዊት ታዬ
 
< Prev   Next >