Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ላንጋኖ ያለው ያኮና ቱሪንግ ንብረት...
ላንጋኖ ያለው ያኮና ቱሪንግ ንብረት... Print E-mail
Wednesday, 23 April 2008
ላንጋኖ ያለው ያኮና ቱሪንግ ንብረት በጨረታ ሊሸጥ ነው

ያኮና ቱሪንግ ኃ/የተ.የግ.ማህበር ከኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ተከራይቶት የነበረውን የላንጋኖ መዝናኛ ውዝፍ ኪራይ ባለመክፈሉ በተመሰረተበት ክስ በመዝናኛ ሥፍራው ያለው የድርጅቱ ንብረት በሃራጅ ሊሸጥ ነው፡፡

በሁለቱ ወገኖች መካከል በፍ/ቤት የተያዘው ጉዳይ ከሁለት አመት በላይ  ሲሆን ቀደም ብሎ በተሰጠ ውሳኔ ያኮና ቱሪንግ የመዝናኛ ማዕከሉን እንዲለቅና ኮንፌዴሬሽኑ እንዲረከበው ተደርጓል፡፡

ኮንፌዴሬሽኑ ያኮና ያለበትን እዳ ሊከፍለው ባለመቻሉ በመዝናኛ ማዕከሉ ያሉ የያኮና ንብረቶች እንዲታገዱና በኋላም ተሸጠው ክፍያውን ለመውሰድ ባመለከተው መሠረት የከፍተኛ ፍርድ ቤት መጋቢት 1 ቀን 2000 ዓ.ም ወስኗል፡፡

ሰሞኑን ይፋ የሆነው የፌደራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም መምሪያ የሃራጅ ማስታወቂያ እንዳመለከተው፣ በኮንፌዴሬሽኑና በፍርድ ባለ እዳ ያኮና ቱሪንግ ኃ/የተ.የግ.ማኅበር መካከል ስላለው የፍርድ አፈፃፀም ጉዳይ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በመዝናኛ ሥፍራው የሚገኙ የባለእዳው ንብረቶች ግምታቸው 734 ሺህ 403 ከአርባ ሳንቲም ሆነው በሐራጅ እንደሚሸጡ ያመለክታል፡፡ ጨረታውም ግንቦት 5 ቀን 2000 እንደሚካሄድ አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል ግን በመዝናኛ ሥፍራው የሚገኘው ንብረት ኮንፌዴሬሽኑ ከሚፈልገው ገንዘብ በታች እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ኮንፌዴሬሽኑ በፍርድ ቤት ይህ ውሳኔ ከመወሰኑ በፊት ያኮና ቱንግ የተከራየውን መዝናኛ ሥፍራ እንዲለቅ ተደርጎ ባለፈው አመት ይህንኑ መዝናኛ ለማከራየት ባወጣው ጨረታ በአመት 1.2 ሚሊዮን ብር ለመክፈል ላቀረበ ተጫራች ማዕከሉን  ይታወሳል፡፡ ኮንፌዴሬሽኑ በገቢ ምንጭነት ከሚጠቀምባቸው ከአምስት የሚበልጡ የመዝናኛ ማዕከላትና ሆቴሎች ውስጥ ከፍተኛው ገቢ የሚያገኘውም ከዚሁ ከላንጋኖ መዝናኛ ነው፡፡


በዳዊት ታዬ
 
< Prev   Next >