Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow የማዳበሪያ ዋጋ አርሶ አደሮችን...
የማዳበሪያ ዋጋ አርሶ አደሮችን... Print E-mail
Wednesday, 23 April 2008
የማዳበሪያ ዋጋ አርሶ አደሮችን እንዳይጎዳ የተለየ ድጎማ የለም

የማዳበሪያ ዋጋ በአለም ገበያ እየጨመረ ቢመጣም ለአርሶ አደሮች ድጎማ የመስጠት የተለየ ፕሮግራም የለም፡፡ የአርሶ አደሩ የመግዛት አቅም ስላደገም ባለው የገበያ ዋጋ መግዛት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

በሌላ  የግብርና ምርትንና ምርታማነትን ለማሻሻል፣ የምርት መጠንን በብዛትና በጥራት ለመጨመር እንዲሁም አርሶ አደሩ በገበያ እየተመራ የሚያመርትበትን ሂደት ለመፍጠር ድጋፍ መስጠት አስፈላጊ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር ከሚያዚያ 24 እስከ 26 ቀን 2000 ዓ.ም  አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል የሚከበረውን የሚሌኒየምና መሥሪያ ቤቱ የተቋቋመበትን 100ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በተሰጠው ትናንት ሚያዚያ 14 ቀን 2000 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ጽጌ እንደገለፁት፣ እየጨመረ ለመጣው የማዳበሪያ ዋጋ አርሶ አደሮች እንዳይጎዱ የተለየ የድጎማ ፕሮግራም እንደሌለ አመልክተዋል፡፡

የተቀናጀ የእርሻ መሳሪያ ቴክኖሎጂ ምርታማነትን ለማሳደግ ወሳኝ ቢሆንም በምርምር ተቋማት ያሉትን መሣሪያዎች ወደ አርሶ አደሩ ለማስፋፋት የአቅም ውሱንነት እንዳለም ገልፀዋል፡፡

በተወሰኑ አካባቢዎች አርሶ አደሮች ያገኙዋቸውን መልካም ልምዶች ወደ ሌሎች አካባቢዎችና አርሶ አደሮች ለማስፋፋት የምርት ግብይት ሥርዓት የተቀላጠፈ እንዲሆን የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ አስፈላጊ መሆኑን ያመለከቱት ኃላፊው የግብአት፣ የብድር አቅርቦት እንዲኖርና የምርጥ ዘርና የማዳበሪያ አጠቃቀም በትክክለኛው አስተያየት እንዲሆን በመሰልጠን ላይ ያሉት የግብርና ባለሙያዎች አስተዋጽኦ ጉልህ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ከ6 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚ አርሶ አደሮች መኖራቸውንና 50"000 የግብርና ልማት ባለሙያዎች መሰልጠናቸውን የገለፁት አቶ ታረቀኝ በ1999 ዓ.ም ከተገኘው የወጪ ንግድ ገቢ 90 በመቶ የሚሆነው ከግብርና ምርቶች የተገኘ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የአርሶ አደሮች በዓል በየክልሉ ይካሄድ የነበረበትን ሁኔታ አስታውሰው በዚህ ዓመት በአዲስ አበባ መካሄዱ ከሁሉም ክልሎች የሚገኙ አርሶ አደሮችን ልምድ ለከተማው ኅብረተሰብ ለማሳየት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በኤግዚቢሽን ለመሳተፍ ፍቃደኛ የሆኑ አርሶ አደሮች መሳተፍ ሲችሉ ኅብረተሰቡም በነፃ በመግባት ጉብኝት ማድረግ እንደሚችል ገልፀዋል፡፡

 በኤግዚቢሽኑ የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር ተጠሪ መሥሪያ ቤቶች፣ ኅብረት ሥራ ማኅበራት፣ የምርጥ ዘር ድርጅቶች፣ አርሶ አደሮች፣ ዩኒየኖችና የግል ድርጅቶች እንደሚሳተፉ ሲጠበቅ ግብርና ትናንት ዜና ነገ በሚል ርዕስ የፓናል ውይይት እንደሚካሄድም ተገልጿል፡፡

በቤዛዊት ሥዩም
 
< Prev   Next >