Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ለሺሕ ዓመቱ ስኬት
ለሺሕ ዓመቱ ስኬት Print E-mail
Wednesday, 23 April 2008
Image
የጽ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሥዩም በረደድ
የኢትዮጵያ ሺሕ ዓመት (ሚሌኒየም) ለአፍሪካ ክብር በሚሰጥ ሁኔታ በተለያዩ የአፍሪካ አገሮችና በአዲስ አበባ በቅርቡ እንደሚከበር የኢትዮጵያ ሚሌኒየም በዓል አከባበር ብሔራዊ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

የጽ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሥዩም በረደድ ለሪፖርተር  እንደገለጹት፣ በተባባሪ ድርጅቶች በተለይም በዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል አማካይነት የተዘጋጀው በዓል በአራት የአፍሪካ አገሮች፣ በደቡብ አፍሪካና በናይጄሪያ፣ በሱዳንና በጅቡቲ ከሚያዚያ 16 ቀን ጀምሮ ይከበራል፡፡ በ8ኛው የአፍሪካ ኅብረት መሪዎች ጉባኤ የኢትዮጵያ ሺሕ ዓመት የአፍሪካም ሆኖ እንዲከበር መወሰኑን ያስታወሱት ዳይሬክተሩ፣ በአዲስ አበባ በግንቦት ወር የአፍሪካ የባህል ሣምንት በሚል ርእስ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች እንደሚቀርቡም ገልጸዋል፡፡

የአፍሪካ አንድነት የተመሠረተበትን 45ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ አጣምሮ በሚኖረው ዝግጅት በአፍሪካውያን ሥነ ጠበብት (አርቲስቶች) የተደረሱት ሲኒማና ሥነጽሑፍ፣ ሥዕል፣ ቅርጻ ቅርጽና ሙዚቃ የሚቀርቡበት ይሆናል፡፡

አቶ ሥዩም መድረኩ ኅብረተሰቡ ስለ አኅጉሩ መልካም ግንዛቤ እንዲኖረው የሚያደርግና በተለይ በምዕራባውያን ፊልምና እግር ኳስ የተወጠረበትና ልቡ የሸፈተው ቆም ብሎ እንዲያስብ የሚያደርገውና የአፍሪካ ኤምባሲዎችም የየአገሮቻቸው መገለጫና የቱሪስት መስህብ የሚያስተዋውቁበት አጋጣሚ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲናነቷን ለማሳየት የምትችልበት አገራዊና አኅጉራዊ አሻራዎች መከበር እንደሚገባቸው የጠቆሙት ዳይሬክተሩ በከተማው ውስጥ የሚታዩት ልዩ ልዩ ተቋማት መደብሮች ስያሜ ወደ ምዕራቡ ያደላና የውጭ መሆኑ የሚያሳስብ መሆኑና ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ መሆኑ ሉላዊነት (ግሎባላይዜሽን) በአንድ በኩል ቢኖርም የእኛ የሆነው ነገር ሲሸረሸር ማየት የለብንም ብለዋል፡፡

በአራቱ የአፍሪካ አገሮች በሚኖረው የበዓል ዝግጅት የመድረክ ውይይቶች፣ የአገሪቱን ገጽታ የሚያሳዩ የፎቶ ግራፍና የሥዕል ዐውደርዕይ፣ በቪዲዮና በቪሲዲ የሚሰራጩ መልእክቶችና የሙዚቃ መሰናዶ እንደሚቀርቡ አዘጋጁ አካል ገልጿል፡፡

በታኅሣሥ 1999 በተካሄደው የሚሌኒየሙ ምክር ቤት ጉባኤ በበዓሉ ለአገሪቱ ታሪክ እውቅና እንዲሰጥ በበዓሉ ዝግጅትም ነባሩን ታሪክ ለትውልድ የሚተላለፍበትን ነገር ማካተት እንደሚገባ ማሳሰቢያ ቢሰጥም እስካሁን በተጨባጭ ጽ/ቤቱ ያከናወነው ተግባር የለም ለሚለው ጥያቄ ዳይሬክተሩ በሰጡት ምላሽ ጽ/ቤቱ የያዘው የማስተባበር ሥራ ነው፡፡ የታሪክ ጉዳይ ልዩ ሙያ በመሆኑ በቅርበት የሚመለከታቸው ተቋማት ተሰባስበው መድረኩን ቢፈጥሩ እኛ ለማስተባበር፣ አዳራሹን ለማዘጋጀት እንችላለን፡፡ በተለይ የጥናት ጉዳይ ስለሆነ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ክፍል ማዘጋጀትና ከእኛ ጋር መተባበር ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

ባለፈው ጉባኤ ፕሮፌሰር ላጵሶ ጌታሁን ድሌቦ “የአፍሪካ ማዕከል ያደረገን ታሪካችን ነው፡፡ መንግሥታዊና ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን አዋሕዶ ለዚህ ደረጃ ያበቃን ስለሆነ ታሪኩ በበዓሉ እውቅና ሊሰጠው ይገባል፡፡ መንግሥታዊ ሥርዓት፣ ክርስትናና እስልምና ለዛሬ አንድነት ስላበቁን ለነገም ብልጽግና የሚያበቁን ስለሆነ ተድበስብሰው ማለፍ የለባቸውም” ብለው መናገራቸው ይታወሳል፡፡

በጥር 2000 ዓ.ም በብሔራዊ ጽ/ቤቱ ተባባሪነት በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን አማካይነት በተካሄደው የቅድመ ታሪክ፣ የአርኪዮሎጂ፣ ፖለንቲኦሎጂ ዓለማቀፍ ጉባኤ በኢትዮጵያ በ100 ዓመታት ውስጥ ስለተከናወኑት ጥናቶችና ምርምሮች፣ ስለነሉሲና ሰላም ግኝቶች ለሦስት ቀናት ዓለም አቀፍ  መክረዋል፡፡ የሚቃረኑ ሐሳቦች ያላቸው ሁሉ በአንድ መድረክ የተሰባሰቡበት እንደነበረ ዳይሬክተሩ አስታውሰዋል፡፡

ከሰው ዘር መነሻ አንስቶ በቅርሶቻችን ዙሪያ በተካሄዱ ምርምሮች ላይ በመመሥረት ብሔራዊ ቅርሶች ለሀገር ልማትና ዕድገት አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ለማድረግ የጋራ ግንዛቤ የተፈጠረበት መድረክ ነው፡፡

በብሔራዊ ምክር ቤትና በሥራ አስፈፃሚው ከጸደቁት 17 ፕሮጀክቶች ሌላ ልዩ ልዩ ሃይማኖታዊና ታሪካዊ በዓላት ከሺሕ ዓመቱ ጋር በማቆራኘት ሃይማኖታዊ አከባበሮች ከባህላዊ ገጽታዎች ጋር በመቆራኘት ለአገሪቱ ገጽታና ለቱሪስቶች መስህብ የሚሆኑ ዝግጅቶችን በማስተባበር መሠራቱን አቶ ሥዩም ገልጸዋል፡፡

በአንድ በኩል ሚሌኒየሙ በፈጠረው መድረክ የባህል አብዮት እንደተነሣ፣ ሰዎች የባህል ልብሳቸውን ለብሰው የሚታዩበት በተዘጋጁት ክብረ በዓላትም በየክልሉና ዞኑ የታየው መንፈስ የሚያረካ መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ በሥነ ጽሑፍና በሥነ ጥበብ በሙዚቃና በባህል የበለጸገችውን አገር ታሪክ የየጉዳዩ ባለቤቶች ገፍተው ወጥተው ኅብረተሰቡን ማነቃቃትና ማስተዋወቅ እንደሚገባቸው አጽንዖት ሰጥተውበታል፡፡

በሥነ  በባሕረ ሐሳብ (ካሌንደር) ዙር ዓለም አቀፍ ጉባኤ በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ አስተባባሪነት በሰኔ መጀመሪያ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንደሚካሄድና ቅድመ ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ መሆኑን አቶ ሥዩም ገልጸዋል፡፡

ከተለያዩ የአውሮፓና  ዩኒቨርሲቲዎች በሚመጡ ፕሮፌሰሮች ከሚቀርቡት 8 ጥናቶች መካከል የግእዝ ሐሳበ ዘመን (Ethiopia Calendar and Era) ከጥንታውያን ግብፃውያን ጋር ስላለው ተዛምዶ የአይሁድ፣ የአርመንና የባቢሎን ካሌንደሮች ላይ የሚቀርቡት ይገኙበታል፡፡

በመጽሐፈ  የግእዝ እትምና የሺሕ ዓመት (ሚሌኒየም) ጽንሰ ሐሳብ ዙሪያ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ የሚያቀርቡት ጥናትም አለ፡፡ በሺሕ ዓመት አከባበሩ መነሻ ላይ በእቅዱ እንደተመለከተው ሃያ እጅ ያህል አድማቂ 80 እጅ ለትውልድ የሚተርፉ ቅርሶች ላይ ማተኮሩን ያወሱት አቶ ሥዩም ቀደም ሲል በተያዘው  በቀለበት መንገድ አደባባዮች ላይ  ሐውልቶች (ለዘጠኙ ክልሎች ለሴቶችና ለአፍሪካ) ለማሠራት የታሰበው በማሻሻል በተመረጡ አደባባዮች ሦስት ሐውልቶች እንደሚሠሩ ጠቁመዋል፡፡

የበዓሉ ስኬት ኢትዮጵያዊነትን ማንፀባረቁ ላይ በመሆኑና ብሔራዊ ስሜትና አገራዊነቱን ለማጉላት ለሐውልቱ ግንባታ ከውጭ ይልቅ አገራዊ  እንዲይዙት መደረጉ ተገቢ መሆኑን ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡ ኢትዮጵያ በዓለም ገናና ስም እንድታገኝ ያደረጓት  አትሌቶች ተግባር የሚያሳይ የአትሌቲክስ ሙዚየም ለማቋቋም ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር ግንኙነት መፈጠሩንና ዲዛይኑን በተመለከተም ሎዛን (ስዊዘርላንድ) የሚገኘው የኢንተርናሽል ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሙዚየምን ዲዛይን የሠራው ሜክሲኳዊ እንዲያዘጋጀው በኢትዮጵያ የሜክሲኮ አምባሳደር ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸውን አቶ ሥዩም ጠቁመዋል፡፡

መዘክሮች (ሙዚየሞች) ቅርስን፣ ባህልንና ታሪክን በማስተዋወቅ ረገድ ዐቢይ ስፍራ እንዳላቸው፣ ኢትዮጵያ የቡና መፈጠርያና መገኛ በመሆኗ ስለቡና አመጣጥ ስለ ሥርዓቱና አፈታሪኩ ወዘተ የሚያሳይ ሙዚየም ከማቋቋም ባሻገር እንደ አቶ ሥዩም አገላለጽ አንዳንድ አገሮች በተለይም የመን ቡና (ሞካ ይሉታል) ከእኛ ነው የተገኘው እያሉ እያስተዋወቁ ስለሆነ ስለ ቡናችን አጉልተን መናገር ቀዳሚነታችን መግለጽ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ መሥራት ይጠበቅብናል፡፡   

በሔኖክ ያሬድ
 
< Prev   Next >