| ክቡር ሚኒስትር |
|
|
| Wednesday, 23 April 2008 | |
|
ክቡር ሚኒስትር እንዲያው አቤት የምንልበት ቦታ አጥተን ነው፡፡ እርስዎ ጉዳዩን ይረዳሉ ንገርዋቸው ተብለን ነው የደወልነው፡፡
- ምንድነው ችግሩ? - ክቡር ሚኒስትር ይኸውልዎት ልናለማው የወሰድነውን መሬት ሊነጥቁን ነው፡፡ - ማን ነው የሚነጥቃችሁ? - ክልሉ ነዋ! - መቼ ነበር መሬቱን የወሰዳችሁት? - ከስድስት ዓመት በፊት ነበር፣ ክቡር ሚኒስትር፡፡ - እንዴት እስካሁን ድረስ ሳይወስድ ቀረ ታዲያ? - እንዴት ክቡር ሚኒስትር? - እናለማለን ብላችሁ መሬት ስትወስዱኮ ገበሬ ተፈናቅሎ ነው፤ ለእናንተ መሬቱ የተሰጠው፡፡ ወይ እናንተ አልሰራችሁበት ወይ ገበሬው አልተጠቀመበት፡፡ ለመሆኑ ስንት ካሬ ሜትር ነው? - አንድ ሚሊዮን ካሬ ሜትር ነው፡፡ ከአርሶ አደሮች አይደለም የወሰድነው ክቡር ሚኒስትር፡፡ - ከማን ነው ታዲያ? - ጣሊያኖች ሊያለሙት ነበር፡፡ የዓለም ባንክ ብዙ ገንዘብ አፍሶበታል፡፡ ልናለማው ከእነሱ ተነጥቆ ለእኛ ተሰጥቶ ነበር፡፡ - ይህ ከሆነማ ብቻ ሳይሆን መታሰርም አለባችሁ፡፡ - ክቡር ሚኒስትር መሬቱ የማን እንደሆነ አውቀዋል? - ይኸው ነገርከኝኮ፡፡ - አይደለም፡፡ እኔኮ የእሳቸው ሰራተኛ ነኝ እንጂ የመሬቱ ባለቤት አይደለሁም፡፡ ባለቤቱ ማን እንደሆነ ያውቃሉ? - አላውቅም፡፡ - ክቡር ሚኒስትር፣ የሰውየው ነው፡፡ - ማን ነው ሰውየው? - እንዴ ክቡር ሚኒስትር እያወቁት" - አላውቅም፣ አላውቅም፣ አወቅኩም አላወቅኩም ለውጥ የለውም፡፡ መሬቱን ለማልማት አልቻላችሁም፡፡ በቃ፡፡ - ክቡር ሚኒስትር ሰውየውኮ በየቦታው ብዙ ልማት ይሰራሉ፡፡ ስለበዛባቸው ነው፡፡ - ታዲያ የምትውጡትን ያህል አኝኳ" የማታለሙትን አትውሰዱ፡፡ ገና ለገና ታለማላችሁ እየተባለ ሕዝብ መጎዳት የለበትም፡፡ - ክቡር ሚኒስትር፣ ሕዝቡ እንዳይጎዳማ የፊታችን እሑድ ለሕዝቡ ትልቅ ድግስ አዘጋጅተናል፡፡ - ምን የሚሉት ድግስ? - አስር ሺህ ለሚሆን የአካባቢው ሕዝብ በሬ ታርዶ እንጀራ ቀርቦ በነፃ እንዲበላ፡፡ - ስማ! - አቤት ክቡር ሚኒስትር፡፡ ስለልማት እያወራን ስለምፅዋት ለምን ታወራለህ? - ክቡር ሚኒስትር ሰውየው ለሕዝቡ ያላቸው ፍቅር መግለጫ ነው፡፡ - በል እንግዲያውስ እኔ ስለልማት እንጂ ስለፍቅር ስለማላውቅ ሌላ ሰው ጋ ደውል፡፡ - ክቡር ሚኒስትር".እ". (ስልኩ ተዘጋ፡፡ ከሰዓታት በኋላ እንደገና ተደወለላቸው) - አቤት፡፡ - ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር፡፡ - ጤና ይስጥልኝ ማን ልበል? - በአካል አያውቁኝም ክቡር ሚኒስትር፡፡ ጧት አንድ ሰው ደውሎዎልዎት ነበር፡፡ አልተግባባችሁም መሰለኝ፡፡ ሰውየው ሃሳቡን መግለፅ አይችልም፡፡ ይቅርታ" ጉዳዩን ለማሳወቅ ነው የደወልኩት፡፡ ሰውየው ራሳቸው እኔ እንድደውል ስላዘዙኝ ነው፡፡ - ማን ናቸው ሰውየው? - እርስዎ ያውቃሉ ብለን ስለምናምን ነው ዝርዝር ውስጥ የማንገባው፤ ክቡር ሚኒስትር፡፡ - እስቲ ወደ ጉዳይህ ግባ ምንድነው የፈለግከው? - ለልማት የወሰድነውን መሬት ክልሉ ሊነጥቀን - ለልማት ኖሮ ባለማኸው ነበርኮ፡፡ - ቦታኮ ብዙ ልማት እያካሄድን ነው፡፡ በሌላ ቦታ ያለውም ይሄኔ ታጥሮ ቀርቶ ይሆናል፡፡ - አልገባኝም፤ ክቡር ሚኒስትር፡፡ - እናለማለን ብሎ መሬት ወስዶ አጥሮ መርሳትና አለማልማት በብዛት እየታየ ነው፡፡ ስለዚህ መቀማቱ ትክክል ነው፡፡ - በአገር ልማት መቀለድ አይሆንም? ክቡር ሚኒስትር፡፡ - አዎን በአገር ልማት መቀለድ ነው፡፡ ጥያቄው ቀልደኛው ማን ነው የሚለው ነው፡፡ - ክቡር ሚኒስትር እኔ ዋናው ምክንያት ለነገ ማታ እራት ሰውየው ራሳቸው እንዳይቀሩብኝ ብለው ስለጋበዝዎት አደራ ለማለት ነው፡፡ ውጭ ሆነው አሁን ደውለውልኝ ነው፡፡ ዛሬ ይመጣሉ፤ ግብዣው ለነገ ነው፡፡ - ይቅርታ እኔ ደግሞ ነገ ወደውጭ እሄዳለሁ፡፡ - ውጭ አገር ልትገናኙ ስለምትችሉ የት አገር ነው የሚሄዱት፤ ክቡር ሚኒስትር፡፡ - እንደዚህ ብሎ ነገር አለ እንዴ? ይቅርታ ስልክ እየመጣብኝ ነው፡፡ (ስልኩ ተዘጋ፡፡ ስራቸውን ጨርሰው ቤታቸው ገቡ፡፡ በሞባይላቸው ተደወለላቸው) - አቤት፡፡ - ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር፡፡ ራስህ ሚኒስትር ሆነህ እንዴት ክቡር ሚኒስትር ትለኛለህ ካላልከኝ በስተቀር እጅ ክቡር ሚኒስትር፡፡ - ምነው በእጅጉ ተለሳለስክ ዛሬ፡፡ - ይኸውልህ አንድ ጉዳይ ሰምቼ ነው የደወልኩልህ፡፡ ከእነሱ አባባል እንደተረዳሁት ነገሩ የገባህ አልመሰለኝም፡፡ - እንዴት አልገባኝም፤ የተከበሩ ክቡር ሚኒስትር፡፡ - መሬቱኮ ለሰውየው የተሰጠ ነው፡፡ - እና? - እናማ ሰውየው ለአገር ልማት የሚጠቅሙ ስለሆኑ እንቅፋት እንዳንሆንባቸው ለመምከር ነው የደወልኩልህ፡፡ - ለልማት እንቅፋት ስለሆነ ነውኮ መሬቱ የሚነጠቀው፡፡ - ስማ የሌላ ቢሆን ግድ የለኝም፡፡ ግን የሰውየው ስለሆነ እንዳትሳሳት፡፡ ሰውየው ራሳቸው ከውጭ ደውለውልኝ ነው፡፡ እራት ተጋብዘህም እምቢ ብለሃል አሉ፡፡ - የተከበሩ ሚኒስትር የተከበሩ ተላላኪ ሲሆኑ ያሳዝናል፡፡ - አትቀልድ". በኋላ ይቆጭሃል ብዬ ነው፡፡ ጠጠር አስቸገረኝ ስትለኝ አልነበረም? - አዎን፡፡ - እና ዝም ብለህ ሰውየውን አሳክሙኝ አትላቸውም? ከእልህ ጤና አይሻልህም፡፡ - ወይ ጣጣ፡፡ - እንዴት ወይ ጣጣ፤ በጣም የተገረምክ ትመስላለህ፡፡ እጅግ በጣም ተገርሜያለሁ እንጂ፡፡ - የተገረምከው? - ያ ጋዜጣ “ታዋቂ የተከበሩ ግለሰቦች ባሌስትራ ሆነው ተገኙ” ብሎ የፃፈው ምን ያህል ትክክለኛ እንደሆነ ገርሞኝ ነው፡፡ - እሺ ቻው፡፡ - ቻው! ከጥቂት ጊዜ በኋላ ስልክ ተደወለላቸው) - አቤት፡፡ - ይቅርታ ክቡር ሚኒስትር በማታ ደወልኩ፡፡ ካልተኙ ደውል ተብዬ ነው፡፡ - ምን ልታዘዝ? - ይኸውልዎት ክቡር ሚኒስትር፣ እርስዎን ጉዳዩ በቀጥታ ላይመለከትዎት ይችላል፡፡ በክልል የሚወሰን ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች እየደወሉ የእርስዎን ስም እየጠሩ አትንጠቁ ተብሏል ይላሉ፡፡ - የእኔ እንዴት ተነሳ? - አይነጠቁ ብለዋል እያሉ፡፡ - የት ደውለው? እኔ ጋ ብዙ ሰዎች ደውለውልኝ ነበር፡፡ የማይለማ መሬት መነጠቅ አለበት ነው ያልኩት፡፡ ለሚያለማማ ይሰጥ፡፡ እኔ እናንተ በክልል ደረጃ የወሰናችሁትን ውሳኔ እደግፈዋለሁ፡፡ ይነጠቁ ነው ያልኩት፡፡ አይነጠቁ አላልኩም፡፡ የሌላ ሚኒስትር ስም ጠርተውላችሁ እንዳይሆን፡፡ - ሌሎቹኮ እናውቃቸዋለን፡፡ እርስዎ ንፁህ ሰው ነዎት እየተባለ ከእርስዎ መጣ ሲባል ገርሞኝ ነው፡፡ - እንኳን ይህ ሌላም አጥረው ያስቀመጡት ካለ ቢቀሙ ደስ ይለኛል፡፡ - ክቡር ሚኒስትር በእኛ ክልል ብቻ አምስት ታጥሮ ስምንት ዓመት የቆየም አለ፡፡ - ንጠቋቸው አትቀልዱ በሏቸው፡፡ - አመሰግናለሁ፤ ክቡር ሚኒስትር፡፡ ጠንቀቅ ይበሉ፡፡ - መጠንቀቅን ምን አመጣው? - እጅግ በጣም ብዙ ደጋፊ አላቸው፡፡ - የማንቸስተርዩናይትድ ደጋፊ ቢበዛም እየተመለከተ ያደንቃል እንጂ ራሱ ጎል አያገባም፡፡ - አይ፣ አይ ክቡር ሚኒስትር፡፡ እነዚህ ከማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ለየት ያሉ ውጭ የወጣ ኳስም ጎል ነው ብለው ማስወሰን የሚችሉ ናቸው፡፡ - ስማ የኔ ወንድም፣ እኔ እንጀራ አጥቼ አይደለም ሹመት የተቀበልኩት፡፡ አገሬን ላገልግል ብዬ ነው፡፡ በዚህ በዚህ አገሬን ምን ትርጉም አለው? - አመሰግናለሁ፤ ክቡር ሚኒስትር፡፡ እንዲህ የሚለን ሰው ነው የናፈቀን፡፡ - ደህና እደር፡፡ - ደህና ይደሩ ክቡር ሚኒስትር፡፡ (ክቡር ሚኒስትሩ ጧት ቢሮ ሁለት ሰዎች እየጠበቁዋቸው ነበር፡፡ ፀሐፊያቸው ስትነግራቸው አስገቢያቸው አሉዋት) - ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር፡፡ - ጤና ይስጥልኝ፤ ቀጠሮ ነበረን? - አልነበረንም፡፡ ትላንት ግን በስልክ አነጋግረውኝ ነበር፡፡ - ትላንትማ እንኳን ለቀጠሮ ልንስማማ በሃሳብም ተለያይተን ነበር፤ ስልኩን የዘጋነው፡፡ - ነበር፤ ክቡር ሚኒስትር፡፡ እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ስለሆነ ነው የመጣነው፡፡ በመጀመሪያ ይህችን የፋሲካ ስጦታ ይቀበሉኝ፡፡ - ምንድነው እሱ? - ይኸው (እየፈቱት) ሰዓት ነው፡፡ ክቡር ሚኒስትር ልዩ ዘመናዊና ውድ ሰዓት ነው፡፡ - እኔ ምን ያደርግልኛል? - መቼስ ሚኒስትር ሥራ ይበዛበታል፣ አስሬ ሰዓት ያያል፡፡ ያስፈልጋል ብለን ነው፡፡ የእኛም አይደለም ሰውየው ራሳቸው ናቸው የላኩት፡፡ - እኔኮ ሰዓት አላስርም፡፡ - እንዴት ክቡር ሚኒስትር፡፡ - ድሮ ሰዓት አስር ነበር፡፡ ሞባይል ከመጣ ወዲህ ግን ሞባይሌ ለመልዕክት ብቻ ሳይሆን ለሰዓትም እጠቀምበታለሁ፡፡ እና". - እና አልፈልግም፡፡ ወደ ቁም ነገሩ እንግባና ምን ፈልጋችሁ ነው? - እርስዎ ከሌሎች ጋር የቅርብ ግንኙነት አለዎት፡፡ መሬቱን እንዳይነጥቁን ያደርጉልን፡፡ ሰውየው ስንት ነገር ለአገር ሰርተዋል፡፡ - በአጋጣሚ ከክልሉ ያገኘሁት መረጃ፣ ከክልሉ የወሰዱት ቦታ ሁሉ ታጥሮ ቀርቷል፡፡ ስምንት ዓመት ያስቆጠረም አለ፡፡ - ቢቀማኮ ልማቱ ይቀራል እንጂ የእሳቸውን ያህል ማንም አያለማውም፡፡ - ቻይናዎች እየጠየቁ ናቸው፡፡ ሕንዶችም እንደዚሁ ጠይቀዋል፣ ቱርኮችም፡፡ - እነዚህ ብለው ነው? - በስምንት ዓመት የሚያጥሩ ሳይሆኑ በስምንት ቀን ግንባታ ጀምረው በስምንት ወር የሚጨርሱ ናቸው፡፡ - እኛኮ ክልሉን ለማልማት ብለን ነው እንጂ ክቡር ሚኒስትር፣ ሌሎች ክልሎችኮ እየለመኑን ናቸው፡፡ - ምን ብለው? - የፈለጋችሁትን መሬት ውሰዱና አልሙ ብለው፡፡ - እንዲያውም ይህን ካነሳችሁልን ወዲህ በየክልሉ ስለሳቸው ኢንቨስትመንት ስጠይቅ ነበር፡፡ ሁሉም ታጥረው ተቀምጠዋል ነው ያሉኝ፡፡ - ክቡር ሚኒስትር የለማ የለም የታጠረ ብቻ ነው አሉ? - ያልታጠረም አለ አሉኝ፡፡ - እና በእርስዎ በኩል የውሳኔ ለውጥ የለም ማለት ነው? ክቡር ሚኒስትር፡፡ - ክልሉ ነው እንጂ እኔኮ አልወስንም፡፡ በግሌ መሬቱ መነጠቅ አለበት ነው የምለው፡፡ - ይህን ሲሉ ሰውየው አይቆጡም ብለው ነው? - ማ ሚኒስትሩ? - አይደለም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳይሆኑ ራሳቸው፡፡ - ራሳቸው ስትል ማንን ማለትህ ነው? - ሰውየው፡፡ - ወይ ሰውየው.... |
| < Prev | Next > |
|---|
ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ለሆነ...
ኢትዮጵያና ግብፅ፤ ሆድና ጀርባ
ለዘመናዊ ፍሳሽ ማስወገጃ ሥራ የ282 ሚሊዮን ብር ስምምነት ተፈረመ
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኘሮጀክት ከ25ዐ ሺ ያላነሱ ነዋሪዎችን የዘመናዊ ፍሳሽ ማስወገጃ ተጠቃሚ የሚያደርግ የ282 ሚሊዮን ብር ስምምነት ከቻይናው ሲ.አር.ቢ.ሲ ጋር ተፈራረመ፡፡
የኮንስትራክሽን ዘርፍና ኢኮኖሚያዊ ድርሻው
በናታን ዳዊት
የሥራ ባልደረባዬ የሠርጉ እለት የለበሰውን ሙሉ የሱፍ ልብስ ግሩም ነበር፡፡ ከየት እንደገዛው ጥያቄ ካቀረቡለት መካከል አንዱ እኔ ነኝ፡፡
"እኛ ማቅረብ አቃተን እንጂ...
"እኛ ማቅረብ አቃተን እንጂ የኅብረተሰቡ የበረኪና ፍላጎት በጣም ከፍተኛ ነው"
አቶ የበጋእሸት ታፈሰ
አቶ የበጋእሸት ታፈሰ የጮራ የጋዝና የኬሚካል ውጤቶች ማምረቻ ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ የፋብሪካውን እንቅስቃሴ በሚመለከት ዳዊት ታዬ አነጋግሯቸዋል፡፡
- ክቡር ሚኒስትር እ".
- እንዴ ተናገሪ እንጂ ፀሐፊዬ ሆነሽ ደግሞ እኔን ማናገር ሊከብድሽ ነው? ምንድነው ችግርሽ?
- የእኔ ችግር አይደለም፡፡ ስለእርስዎ መናገር ፈልጌ አይደለም፡፡ ስለሠራተኛው ስሜት ልነግርዎት ፈልጌ ነው፡፡
የግጭት አፈታት በቦረናና በገብራ
በሔኖክ ያሬድ
ኢትዮጵያ በርካታ ብሔረሰቦች የሚኖሩባትና የየራሳቸው መለያ የያዙ ባህላዊ ሥርዓቶች፣ ታሪክና ቋንቋ አላቸው፡፡ ከአነዚህ ሥርዓቶች መካከል አንዱ ባህላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓት ነው፡፡
ወደፊት ሲጠበቅ ወደኋላ የተመለሰ ኑሮ
በዓለም በመጠኑ ትንሹ እባብ ተገኘ
አሥር ሴንቲ ሜትር ወይም 4 ኢንች ርዝማኔ ያለው እባብ በካረቢያን ባርባዶስ በተባለ ደሴት አካባቢ ተገኝቷል፡፡ በዓለም ካሉ እባቦች ትንሽ መሆኑንም ጆርናል ኦፍ ዞታግዛ ዘግቧል፡፡
ሕብረቱ ዲያስፖራውን ለማጠናከር እርዳታ አገኘ
በጋዜጣው ሪፖርተር
የአፍሪካ ሕብረት አፍሪካዊ ዲያስፖራውን አስመልክቶ ላለው ኘሮግራም ማጠናከሪያ የሚውል የ487 ሺህ የአሜሪካ ዶላር እርዳታ ከአለም ባንክ አግኝቷል፡፡
የቪዲዮ ካሜራ ክሬን የፈጠራ ባለቤት
በምሕረት አስቻለው
መጠነኛ ስፋት ባለው ስፖርት ቤት ውስጥ ያሉት የመሥሪያ ማሽኖች በተለያየ ጊዜ ራሱ የሠራቸው እንደሆኑ ይናገራል የሀያ አራት ዓመቱ ወጣት ፍላጐት ይልማ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎችን የሚሠራ ሲሆን የቪዲዮ ካሜራ ክሬን በመሥራት 1999 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ባለቤትነት ማረጋገጫ አግኝቷል፡፡
ፌዴሬሽኑ "የአትሌቲክስ" ቢሆን ምን ይውጠን ነበር?
ታሪኩ ነገራ
አርብ ነሐሴ 2 ቀን 2000 ዓ.ም የሚከፈተውና የሚጀምረው ቻይና የምታስተናግደው የዘንድሮው 29ኛ ኦሊምፒያድ የአገራችንንም ጨምሮ የእያንዳንዱ አገር የውስጥ ዜና እና የመላው ዓለም ኢንተርናሽናል ዜናና አጀንዳ ሆኗል፡፡ ሆኖም ይቀጥላል፡፡ ከእያንዳንዱ አገር የኦሊምፒክ ቡድን ምልመላና ምርጫ እንጀምር፡፡
እናትነት ማየት ለተሳናቸው
በምሕረት አስቻለው
"ነፍሠ ጡር ሆኜ በመንገድ፣ አወቶብስ ላይ እንዲሁም ሆስፒታል ውስጥ የሚመለከቱኝ ሰዎች ምን አለበት ቢቀርባት፣ ምን ያደርግላታል የሚሉ አስተያየቶችን ይሰነዝሩ ነበር፡፡ በትዳር ያለሁ ሁሉ አይመስላቸውም፡፡ ተደፍራ ወይም ቀብጣ ነው የሚል እሳቤአቸው በንግግራቸው ይንፀባረቃል፡፡ አስተያየታቸውን ልስማ አልስማ እንኳ አያስተውሉም፡፡ ይህ ደግሞ ሞራልን የሚጐዳ ነገር ነው" ይላሉ ወ/ሮ ወይንሸት በዙ የተባሉ ማየት የተሳናቸው እናት፡፡
አባተ ስለሺ
በዚህ ጋዜጣ በ"ተሟገት" ዓምድ "የኢትዮጵያ ራዕይ እውን አሁን አንተ እሱ ነህ?" በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ጽሁፍ ላይ የማስታወቂያ ሚኒስቴር የሰጠውንና በሪፖርተር ጋዜጣ በሐምሌ 1 የ"ተሟገት" አምድ ላይ የወጣውን "ለማሳወቅ ቀድሞ ማወቅ" የሚል ርዕስ የተሰጠውን ምላሽና ማብራሪያ አንብቤያለሁ፡፡ ከሁሉ አስቀድሞ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ጽሁፌን "ብዙ አንባቢ እንደተመለከተው መገመት" እንደሚችል "አንባቢው በጉዳዩ ላይ ሚዛናዊ ግንዛቤ መያዝ እንዲችል ያደርጋሉ ተብለው በታመኑባቸውና በተመረጡ ነጥቦች ላይ ተወስኖ ማብራሪያና መልስ መስጠት ተገቢ ሆኖ"". ያገኘው መሆኑን ገልጾ መልስ መስጠቱን ማድነቅ ይህንንም አድናቆቱንም በአክብሮት መግለጽ እውዳለሁ፡፡
የአጉራሽ ተነካሽ!
ፍልሚያው ተፋፍሟል፡፡ በጭንቀት የተሞሉ ድምፆች ይሰማሉ፡፡ በማጣጣር ላይ ያሉት ዕጣ ፈንታቸውን እየጠበቁ ነው፡፡ በመከላከል ላይ የነበሩትም ወደ መሸነፍ አዘንብለዋል፡፡ ዙሩ በጣም ከርሯል፡፡ የሚንጠባጠቡት ከጉዞው እየቀሩ ነው፡፡
የፊፋ ውሳኔ ለጠቅላላ ጉባኤ ይቀርባል
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዲሱ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከቀድሞ አመራር ኃላፊነቱን ከተረከበ ከወራት በኋላ ፊፋ "የላኩት ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ተፈፃሚ አልሆነም" በሚል ኢትዮጵያን ከማንኛውም አህጉራዊም ሆነ ኢንተርናሽናል ወድድር እንዳትሳተፍ አግዷል፡፡
አንድ ሰሞን ሞቅ ሞቅ የሚሉ ንግግሮች ጊዜያቸውን ጠብቀው ተራ ይሆናሉ፡፡ ወይም ስለመነገራቸውም ይረሳል፡፡ ግልጽነትና ተጠያቂነትን በሚመለከት የተወረወሩ ቃላት ከእኛ በላይ የተጠቀመባቸው ያለም አይመስልም፡፡ ግልጽነትንና ተጠያቂነትን አሰፍናለሁ ብለው ተነስቶ ጭራሽ ሲያባብሱት ወቸው ጉድ ያሰኛል፡፡
የዚምባቡዌ መንግሥትና ተቃዋሚ ፓርቲ የጥምር መንግሥት ለመመስረት እየተወያዩ ነው
የዚምባቡዌ መንግሥትና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች በሀገሪቱ ጥምት መንግሥት ለመመስረት የመጨረሻ ዙር ውይይት እያካሄዱ መሆኑን የኦል አፍሪካ ዘገባ አመለከተ፡፡