Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow ክቡር ሚኒስትር
ክቡር ሚኒስትር Print E-mail
Wednesday, 23 April 2008
ክቡር ሚኒስትር እንዲያው አቤት የምንልበት ቦታ አጥተን ነው፡፡ እርስዎ ጉዳዩን ይረዳሉ ንገርዋቸው ተብለን ነው የደወልነው፡፡

- ምንድነው ችግሩ?
- ክቡር ሚኒስትር ይኸውልዎት ልናለማው የወሰድነውን መሬት ሊነጥቁን ነው፡፡
- ማን ነው የሚነጥቃችሁ?
- ክልሉ ነዋ!
- መቼ ነበር መሬቱን የወሰዳችሁት?
- ከስድስት ዓመት በፊት ነበር፣ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- እንዴት እስካሁን ድረስ ሳይወስድ ቀረ ታዲያ?
- እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
- እናለማለን ብላችሁ መሬት ስትወስዱኮ ገበሬ ተፈናቅሎ ነው፤ ለእናንተ መሬቱ የተሰጠው፡፡ ወይ እናንተ አልሰራችሁበት ወይ ገበሬው አልተጠቀመበት፡፡ ለመሆኑ ስንት ካሬ ሜትር ነው?
- አንድ ሚሊዮን ካሬ ሜትር ነው፡፡ ከአርሶ አደሮች አይደለም የወሰድነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ከማን ነው ታዲያ?
- ጣሊያኖች ሊያለሙት ነበር፡፡ የዓለም ባንክ ብዙ ገንዘብ አፍሶበታል፡፡ ልናለማው ከእነሱ ተነጥቆ ለእኛ ተሰጥቶ ነበር፡፡
- ይህ ከሆነማ  ብቻ ሳይሆን መታሰርም አለባችሁ፡፡
- ክቡር ሚኒስትር መሬቱ የማን እንደሆነ አውቀዋል?
- ይኸው ነገርከኝኮ፡፡
- አይደለም፡፡ እኔኮ የእሳቸው ሰራተኛ ነኝ እንጂ የመሬቱ ባለቤት አይደለሁም፡፡ ባለቤቱ ማን እንደሆነ ያውቃሉ?
- አላውቅም፡፡
- ክቡር ሚኒስትር፣ የሰውየው ነው፡፡
- ማን ነው ሰውየው?
- እንዴ ክቡር ሚኒስትር እያወቁት"
- አላውቅም፣ አላውቅም፣ አወቅኩም አላወቅኩም ለውጥ የለውም፡፡ መሬቱን ለማልማት አልቻላችሁም፡፡ በቃ፡፡
- ክቡር ሚኒስትር ሰውየውኮ በየቦታው ብዙ ልማት ይሰራሉ፡፡ ስለበዛባቸው ነው፡፡
- ታዲያ የምትውጡትን ያህል አኝኳ" የማታለሙትን አትውሰዱ፡፡ ገና ለገና ታለማላችሁ እየተባለ ሕዝብ መጎዳት የለበትም፡፡
- ክቡር ሚኒስትር፣ ሕዝቡ እንዳይጎዳማ የፊታችን እሑድ ለሕዝቡ ትልቅ ድግስ አዘጋጅተናል፡፡
- ምን የሚሉት ድግስ?
- አስር ሺህ ለሚሆን የአካባቢው ሕዝብ በሬ ታርዶ እንጀራ ቀርቦ በነፃ እንዲበላ፡፡
- ስማ!
- አቤት ክቡር ሚኒስትር፡፡
 ስለልማት እያወራን ስለምፅዋት ለምን ታወራለህ?
- ክቡር ሚኒስትር ሰውየው ለሕዝቡ ያላቸው ፍቅር መግለጫ ነው፡፡
- በል እንግዲያውስ እኔ ስለልማት እንጂ ስለፍቅር ስለማላውቅ ሌላ ሰው ጋ ደውል፡፡
- ክቡር ሚኒስትር".እ".

(ስልኩ ተዘጋ፡፡ ከሰዓታት በኋላ እንደገና ተደወለላቸው)

- አቤት፡፡
- ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ጤና ይስጥልኝ ማን ልበል?
- በአካል አያውቁኝም ክቡር ሚኒስትር፡፡ ጧት አንድ ሰው ደውሎዎልዎት ነበር፡፡ አልተግባባችሁም መሰለኝ፡፡ ሰውየው ሃሳቡን መግለፅ አይችልም፡፡ ይቅርታ" ጉዳዩን ለማሳወቅ ነው የደወልኩት፡፡ ሰውየው ራሳቸው እኔ እንድደውል ስላዘዙኝ ነው፡፡
- ማን ናቸው ሰውየው?
- እርስዎ ያውቃሉ ብለን ስለምናምን ነው ዝርዝር ውስጥ የማንገባው፤ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- እስቲ ወደ ጉዳይህ ግባ ምንድነው የፈለግከው?
- ለልማት የወሰድነውን መሬት ክልሉ ሊነጥቀን  
- ለልማት  ኖሮ ባለማኸው ነበርኮ፡፡
-  ቦታኮ ብዙ ልማት እያካሄድን ነው፡፡
 በሌላ ቦታ ያለውም ይሄኔ ታጥሮ ቀርቶ ይሆናል፡፡
- አልገባኝም፤ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- እናለማለን ብሎ መሬት ወስዶ አጥሮ መርሳትና አለማልማት በብዛት እየታየ ነው፡፡ ስለዚህ መቀማቱ ትክክል ነው፡፡
- በአገር ልማት መቀለድ አይሆንም? ክቡር ሚኒስትር፡፡
- አዎን በአገር ልማት መቀለድ ነው፡፡ ጥያቄው ቀልደኛው ማን ነው የሚለው ነው፡፡
- ክቡር ሚኒስትር እኔ  ዋናው ምክንያት ለነገ ማታ እራት ሰውየው ራሳቸው እንዳይቀሩብኝ ብለው ስለጋበዝዎት አደራ ለማለት ነው፡፡ ውጭ ሆነው አሁን ደውለውልኝ ነው፡፡ ዛሬ ይመጣሉ፤ ግብዣው ለነገ ነው፡፡
- ይቅርታ እኔ ደግሞ ነገ ወደውጭ  እሄዳለሁ፡፡
- ውጭ አገር ልትገናኙ ስለምትችሉ የት አገር ነው የሚሄዱት፤ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- እንደዚህ ብሎ ነገር አለ እንዴ? ይቅርታ  ስልክ እየመጣብኝ ነው፡፡

(ስልኩ ተዘጋ፡፡ ስራቸውን ጨርሰው ቤታቸው ገቡ፡፡ በሞባይላቸው ተደወለላቸው)

- አቤት፡፡
- ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር፡፡ ራስህ ሚኒስትር ሆነህ እንዴት ክቡር ሚኒስትር ትለኛለህ ካላልከኝ በስተቀር እጅ  ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ምነው በእጅጉ ተለሳለስክ ዛሬ፡፡
- ይኸውልህ አንድ ጉዳይ ሰምቼ ነው የደወልኩልህ፡፡ ከእነሱ አባባል እንደተረዳሁት ነገሩ የገባህ አልመሰለኝም፡፡
- እንዴት አልገባኝም፤ የተከበሩ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- መሬቱኮ ለሰውየው የተሰጠ ነው፡፡
- እና?
- እናማ ሰውየው ለአገር ልማት የሚጠቅሙ ስለሆኑ እንቅፋት እንዳንሆንባቸው ለመምከር ነው የደወልኩልህ፡፡
- ለልማት እንቅፋት ስለሆነ ነውኮ መሬቱ የሚነጠቀው፡፡
- ስማ የሌላ ቢሆን ግድ የለኝም፡፡ ግን የሰውየው ስለሆነ እንዳትሳሳት፡፡ ሰውየው ራሳቸው ከውጭ ደውለውልኝ ነው፡፡ እራት ተጋብዘህም እምቢ ብለሃል አሉ፡፡
- የተከበሩ ሚኒስትር የተከበሩ ተላላኪ ሲሆኑ ያሳዝናል፡፡
- አትቀልድ". በኋላ ይቆጭሃል ብዬ ነው፡፡  ጠጠር አስቸገረኝ ስትለኝ አልነበረም?
- አዎን፡፡
- እና ዝም ብለህ ሰውየውን አሳክሙኝ አትላቸውም? ከእልህ ጤና አይሻልህም፡፡
- ወይ ጣጣ፡፡
- እንዴት ወይ ጣጣ፤ በጣም የተገረምክ ትመስላለህ፡፡
 እጅግ በጣም ተገርሜያለሁ እንጂ፡፡
-  የተገረምከው?
- ያ ጋዜጣ “ታዋቂ የተከበሩ ግለሰቦች ባሌስትራ ሆነው ተገኙ” ብሎ የፃፈው ምን ያህል ትክክለኛ እንደሆነ ገርሞኝ ነው፡፡
- እሺ ቻው፡፡
- ቻው!

 ከጥቂት ጊዜ በኋላ ስልክ ተደወለላቸው)

- አቤት፡፡
- ይቅርታ ክቡር ሚኒስትር በማታ ደወልኩ፡፡ ካልተኙ ደውል ተብዬ ነው፡፡
-  ምን ልታዘዝ?
- ይኸውልዎት ክቡር ሚኒስትር፣ እርስዎን ጉዳዩ በቀጥታ ላይመለከትዎት ይችላል፡፡ በክልል የሚወሰን ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች እየደወሉ የእርስዎን ስም እየጠሩ አትንጠቁ ተብሏል ይላሉ፡፡
- የእኔ  እንዴት ተነሳ?
- አይነጠቁ ብለዋል እያሉ፡፡
- የት ደውለው? እኔ ጋ ብዙ ሰዎች ደውለውልኝ ነበር፡፡ የማይለማ መሬት መነጠቅ አለበት ነው ያልኩት፡፡ ለሚያለማማ ይሰጥ፡፡ እኔ እናንተ በክልል ደረጃ የወሰናችሁትን ውሳኔ እደግፈዋለሁ፡፡ ይነጠቁ ነው ያልኩት፡፡ አይነጠቁ አላልኩም፡፡ የሌላ ሚኒስትር ስም ጠርተውላችሁ እንዳይሆን፡፡
- ሌሎቹኮ እናውቃቸዋለን፡፡ እርስዎ ንፁህ ሰው ነዎት እየተባለ ከእርስዎ መጣ ሲባል ገርሞኝ ነው፡፡
- እንኳን ይህ ሌላም አጥረው ያስቀመጡት ካለ ቢቀሙ ደስ ይለኛል፡፡
- ክቡር ሚኒስትር በእኛ ክልል ብቻ አምስት  ታጥሮ ስምንት ዓመት የቆየም አለ፡፡
- ንጠቋቸው አትቀልዱ በሏቸው፡፡
- አመሰግናለሁ፤ ክቡር ሚኒስትር፡፡ ጠንቀቅ ይበሉ፡፡
- መጠንቀቅን ምን አመጣው?
- እጅግ በጣም ብዙ ደጋፊ አላቸው፡፡
- የማንቸስተርዩናይትድ ደጋፊ ቢበዛም እየተመለከተ ያደንቃል እንጂ ራሱ ጎል አያገባም፡፡
- አይ፣ አይ ክቡር ሚኒስትር፡፡ እነዚህ ከማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ለየት ያሉ  ውጭ የወጣ ኳስም ጎል ነው ብለው ማስወሰን የሚችሉ ናቸው፡፡
- ስማ የኔ ወንድም፣ እኔ እንጀራ አጥቼ አይደለም ሹመት የተቀበልኩት፡፡ አገሬን ላገልግል ብዬ ነው፡፡ በዚህ በዚህ አገሬን  ምን ትርጉም አለው?
- አመሰግናለሁ፤ ክቡር ሚኒስትር፡፡ እንዲህ የሚለን ሰው ነው የናፈቀን፡፡
- ደህና እደር፡፡
- ደህና ይደሩ ክቡር ሚኒስትር፡፡

(ክቡር ሚኒስትሩ ጧት ቢሮ  ሁለት ሰዎች እየጠበቁዋቸው ነበር፡፡ ፀሐፊያቸው ስትነግራቸው አስገቢያቸው አሉዋት)

- ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ጤና ይስጥልኝ፤ ቀጠሮ ነበረን?
- አልነበረንም፡፡ ትላንት ግን በስልክ አነጋግረውኝ ነበር፡፡
- ትላንትማ እንኳን ለቀጠሮ ልንስማማ በሃሳብም ተለያይተን ነበር፤ ስልኩን የዘጋነው፡፡
- ነበር፤ ክቡር ሚኒስትር፡፡ እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ስለሆነ ነው የመጣነው፡፡ በመጀመሪያ ይህችን የፋሲካ ስጦታ ይቀበሉኝ፡፡
- ምንድነው እሱ?
- ይኸው (እየፈቱት) ሰዓት ነው፡፡ ክቡር ሚኒስትር ልዩ ዘመናዊና ውድ ሰዓት ነው፡፡
- እኔ ምን ያደርግልኛል?
- መቼስ ሚኒስትር ሥራ ይበዛበታል፣ አስሬ ሰዓት ያያል፡፡ ያስፈልጋል ብለን ነው፡፡ የእኛም አይደለም ሰውየው ራሳቸው ናቸው የላኩት፡፡
- እኔኮ ሰዓት አላስርም፡፡
- እንዴት ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ድሮ ሰዓት አስር ነበር፡፡ ሞባይል ከመጣ ወዲህ ግን ሞባይሌ ለመልዕክት ብቻ ሳይሆን ለሰዓትም እጠቀምበታለሁ፡፡
 እና".
- እና አልፈልግም፡፡ ወደ ቁም ነገሩ እንግባና ምን ፈልጋችሁ ነው?
- እርስዎ ከሌሎች ጋር የቅርብ ግንኙነት አለዎት፡፡ መሬቱን እንዳይነጥቁን ያደርጉልን፡፡ ሰውየው ስንት ነገር ለአገር ሰርተዋል፡፡
- በአጋጣሚ ከክልሉ ያገኘሁት መረጃ፣ ከክልሉ የወሰዱት ቦታ ሁሉ ታጥሮ ቀርቷል፡፡ ስምንት ዓመት ያስቆጠረም አለ፡፡
- ቢቀማኮ ልማቱ ይቀራል እንጂ የእሳቸውን ያህል ማንም አያለማውም፡፡
- ቻይናዎች እየጠየቁ ናቸው፡፡ ሕንዶችም እንደዚሁ ጠይቀዋል፣ ቱርኮችም፡፡
- እነዚህ  ብለው ነው?
- በስምንት ዓመት የሚያጥሩ ሳይሆኑ በስምንት ቀን ግንባታ ጀምረው በስምንት ወር የሚጨርሱ ናቸው፡፡
- እኛኮ ክልሉን ለማልማት ብለን ነው እንጂ ክቡር ሚኒስትር፣ ሌሎች ክልሎችኮ እየለመኑን ናቸው፡፡
- ምን ብለው?
- የፈለጋችሁትን መሬት ውሰዱና አልሙ ብለው፡፡
- እንዲያውም ይህን ካነሳችሁልን ወዲህ በየክልሉ ስለሳቸው ኢንቨስትመንት ስጠይቅ ነበር፡፡ ሁሉም ታጥረው ተቀምጠዋል ነው ያሉኝ፡፡
- ክቡር ሚኒስትር የለማ የለም የታጠረ ብቻ ነው አሉ?
- ያልታጠረም አለ አሉኝ፡፡
- እና በእርስዎ በኩል የውሳኔ ለውጥ የለም ማለት ነው? ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ክልሉ ነው እንጂ እኔኮ አልወስንም፡፡ በግሌ መሬቱ መነጠቅ አለበት ነው የምለው፡፡
- ይህን ሲሉ ሰውየው አይቆጡም ብለው ነው?
- ማ  ሚኒስትሩ?
- አይደለም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳይሆኑ ራሳቸው፡፡
- ራሳቸው ስትል ማንን ማለትህ ነው?
- ሰውየው፡፡
- ወይ ሰውየው....
 
< Prev   Next >