Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow “ባዮኒክ አይ” ለአይነ መድኃኒት...
“ባዮኒክ አይ” ለአይነ መድኃኒት... Print E-mail
Wednesday, 23 April 2008
Image“ባዮኒክ አይ” ለአይነ  መድኃኒት የመሆን ተስፋ አለው

በዘር ውርስ ለተፈጠረ አይነ ስውርነት በ”ባዮኒክ አይ” (ሰው ሰራሽ አይን) እንዲያገግም ለማድረግ የሚያስችል ተስፋ እንዳለው ባለሙያዎች አስታወቁ፡፡

በለንደን ሞርፊልድስ ዓይን ሆስፒታል የሚሠራው የሕክምና ቡድን በእንግሊዝ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ሕመምተኛ ላይ ለጥናት  ምርመራ እንደተደረገለት ገልጿል፡፡

ሰው ሰራሹ አይን መነፅር ጋር በሚያያዙ ካሜራዎች የሚገጠም ሲሆን ለሁለተኛ ጊዜ በአሜሪካ መሞከሩ ተገልጿል፡፡

ሕክምናው በጣም አስደሳች ቢሆንም ገና በሂደት ላይ መሆኑን የብሪቲሽ ሬቲኒስት ፒግሜንቶሳ ሶሳይቲ ሚ/ር  ተናግረዋል፡፡

ሙከራው በውርስ የሚፈጠር የማየት ችግርን ለማስተካከል ተስፋ ሰጪ ሲሆን በእንግሊዝ ከ20,000 እስከ 25,000 የሚደርሱ ሕመምተኞች መኖራቸው ተመልክቷል፡፡

የአይን ቀዶ ህክምናው ባለፈው ሳምንት የተካሄደ ሲሆን ለእይታ የሚረዱ መሳሪያዎች በትክክል እንደተገጠሙላቸውና ከቀዶ ህክምናው ማገገማቸው ተገልጿል፡፡
 
አውሮፓና አሜሪካ በሙከራ ሕክምናው እንደሚሳተፉ ተገልጿል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጥ በሚያጠቃው ስፍራ ጥናት ሊደረግ ነው

ሳይንቲስቶች በጃፓን የመሬት መንቀጥቀጥ በሚፈጠርበት አካባቢ ለማጥናት የሚያስችላቸውን ኘላን የመጀመሪያ ደረጃ ሂደት ማጠናቀቃቸውን አስታወቁ፡፡

በኘሮጀክቱ ከባህር ወለል በታች 1.4 ኪሎ ሜትር ጥልቀት ያለው ቀዳዳ 3ዳይሜንሽን ባላቸው ምስሎች መነሳታቸው ተገልጿል፡፡

በአውሮፓ ጄኦሳይንስ ዩኒየን ዓመታዊ ስብሰባ በመጀመሪያ ዙር በጃፓን በደቡብ ምሥራቅ ጠረፍ በናንካይ ሴስሞ ጄኒክ ዞን የሚደረገው ጥናት ውጤት የቀረበ ሲሆን የኘሮጀክቱ ዋና ሳይንቲስት ሀሮልድ ቶቢን እንደተናገሩት የመሬት መንቀጥቀጥን የሚፈጥሩ ችግሮችን ለማጥናት በባህር ውስጥ የሚያደርጉትን ጥናት ይቀጥላሉ፡፡

ጥናቱን ለማካሄድ በ2ዐዐ4 ተከስቶ የነበረው የሱናሜ አደጋ መነሻ እንደሆናቸውም ባለሙያው ገልፀዋል፡፡ ትልልቅ የሚባሉት የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች በማግኒትዩድ መለኪያ 8፣9 እና ከዚያ በላይ የሚሆኑት በባህር ውስጥ እንደሚፈጠር ገልፀው በባህር ውስጥ የማደረገው ጥናት በመሬት ውስጥ ያለው የመሬትን ቅርፅ የፈጠረው ድንጋይ ድንበርና የመሬት መንቀጥቀጥ የሚፈጥሩ ችግሮችን ለማጥናት እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡

ካለፈው መስከረም ወዲህ ባሉት አምስት ወራት የተለያየ ጥልቀት ያላቸው 8 ቀዳዳዎች በናንካይ አካባቢ መታየቱንም አዲሱ የጃፓን ተመራማሪዎች ቡድን አስታውቋል፡፡

በመጀመሪያ ዙር የተደረገው ይኸው ጥናት ሳይንቲስቶች በቀጣይ ለሚያደርጉት ጥናት መጓዝ ላለባቸው  አመላካች መሆኑ ተገልጿል፡፡

እንደ ዶ/ር ቶቢን ገለፃ በቀጣዩ አመት ሰፋፊ ጉድጓዶችን ለማጥናት ማቀዳቸውን በ2010 ወይም በ2012 እስከ 6 ኪሎ ሜትር ጥልቀት ያላቸውን ሁለት ጉድጓዶችን እንደሚያጠኑ ገልፀዋል፡፡ ውጤቱ የመሬት መንቀጥቀጥንና ሱናሚን ለመተንበይ እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡

የባዮፊውል ልማት በምግብ ላይ ጫና እየፈጠረ ነው

የባዮፊውል ልማት በምግብ እህሎች ላይ እየፈጠረ ያለውን ጫና እንዲቀንስ ሁለት የደቡብ አሜሪካ ባለሥልጣናት ማስጠንቀቂያ ሰጡ፡፡

የቦልቪያን ኘሬዚዳንት ኢቪ ሞራሌስ እንደገለፁት የባዮፊውል ልማት አነስተኛ አቅም ባላቸው ሰዎች ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እየፈጠረ ሲሆን የፔሩ ኘሬዚዳንት አላን ጋርቪያ በበኩላቸው መሬት ለባዮፊውል ማልሚያነት በመዋሉ ለደሃው በሚቀርበው ምግብ ላይ ጫና እየፈጠረ ነው ብለዋል፡፡

የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጎርደን ብራውን የባዮፊውል ምርትን ለማበረታታት የሚያስችል የአውሮፓ ፖሊሲ እንዲኖር የሚመክር ስብሰባ ጠርተዋል፡፡ ከስብሰባው ቀደም ብሎ እንግሊዝ ለባዮፊውል ልማት በምታደርገው እገዛ የምግብ ምርቶችን ለባዮፊውል ለመጠቀም የተሻለውን አማራጭ እንደምታይ ተናግረዋል፡፡

ታዳሽ የኃይል ምንጮችን መጠቀም የዓለም የሙቀት መጠን መጨመርን ለመቀነስ እንደሚረዳ ታምኖበታል፡፡

ረሃብን የመቋቋም ጥያቄ ሁሉንም አካል የሚመለከት ሲሆን ለፖለቲካና ኢኮኖሚ መረጋጋት ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረውም የእንግሊዙ ጠቅላይ ማኒስትር ጎርደን ብራውን ተናግረዋል፡፡ በዓለም የምግብ ምርቶች ዋጋ መጨመር የባዮፊውል ልማትን ለመቀነስ እንደሚያስገድ ተናግረዋል፡፡ የደቡብ አሜሪካ አገሮች ባዮፊውል በምግብ እህሎች ላይ ያለውን ጫና ለማጥናት ቸልተኝነት እንደሚታይባቸው ተገልጿል፡፡

በ2010 ከአሜሪካ 3ዐ በመቶ የሚሆነው የበቆሎ ምርቷ ለኢታኖል ማምረቻነት እንዲውል ታቅዷል፡፡ ባለፈው ሰኞ የብራዚል ኩባንያ ከጋና ጋር በሽርክና ለባዮኢታኖል ምርት የሚውል የሸንኮራ አገዳ ለማምረት መስማማቱን አስታውቋል፡፡ በጋና የሚካሄደው ኘሮጀክት 27"000 ሄክታር መሬት በሸንኮራ አገዳ በማልማት በዓመት 15ዐ ሚሊዮን ሊትር ኢታኖል በማምረት ለስዊዲን ገበያ ለማቅረብ መታቀዱ ተገልጿል፡፡

በፔሩ ከ12 ማሊዮን በላይ ህዝብ ከድህነት ወለል በታች የሚኖር በመሆኑ አሁን በተከሰተው የምግብ ምርቶች ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ እየተጎዱ ነው፡፡ የዓለም የስንዴ፣ የሩዝና የበቆሎ ዋጋ ባለፈው ዓመት ከነበረው በእጥፍ የጨመረ ሲሆን የወተትና የሥጋ ዋጋ ከእጥፍ በላይ ጨምሯል፡፡

የእጢ እድገትን ሊያዘግም የሚችል ጅን

የአሜሪካ ሳይንቲስቶች የጡት ካንሰር እድገትን የሚያፋጥነውን እጢ ሊያዘግም የሚችል ጅን ማግኘታቸውን ገልፀዋል፡፡

የአሜሪካ ናሽናል ካንሰር ኢንስቲትዩት ጥናቱን በዓይጥ ላይ የሞከረ ሲሆን ውጤቱም ቢ.አር.ዲ 4 የተሰኘው ጅን በውስጣቸው ያለ እጢዎች ከሌላቸው ሲነፃፀሩ በ1ዐ እጥፍ የእድገት መጠናቸው አንሶ ተገኝቷል፡፡

 ካንሰር ባለባቸው ሰዎች ላይ በተሞከረው የምርምር ውጤትም .አር.ዲ 4 ጂን በእጢ ውስጥ መገኘት የካንሰር እድገትን ሊያዘግም እንደሚችል ተመልክቷል፡፡

የካንሰር ተመራማሪዎች በግኝቱ ላይ ጥልቅ ምርምር እንዲደረግና የቢ.አር.ዲ 4 ጂን በሴሎች እድገት ላይ ሊያሳድር በሚችለው ተፅእኖ ላይ መስራት እንደሚገባ መክረዋል፡፡

የጡት ካንሰር እጢ እድገትን እንደሚገታ የተነገረለት ይኸው የምርምር ውጤት ለጡት ብቻ ሳይሆን ለሌላ የካንሰር አይነትም ሊረዳ እንደሚችል ተመራማሪዎቹ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡

ናሽናል ሳይንስ አካዳሚ የሙከራውን ሂደት አስመልክቶ እንደዘገበው አጥኚዎቹ የቢ.አር.ዲ 4 ጂንን በአይጦች የጡት ካንሰር እጢዎች ላይ ጨምረው ነበር፡፡ ከ28 ቀናት በኋላም የእጢዎቹ እድገት ውሱን የነበረ ሲሆን በሽታውም ወደ ሳንባ የመስፋፋት እድሉ በጣም ተወስኖ አግኝተውታል፡፡

የጂኑ ሙከራ በአይጦች ላይ ብቻ ተወስኖ አልቀረም፡፡ 1240 የጡት ካንሰር  በአምስት ቡድን ተከፋፍለውም ጥናቱ ተደርጓል፡፡

የሙከራው ውጤት ያሳየውም የቢ.አር.ዲ 4 ጂን የካንሰር እድገትን ለማዝገምና የህመምተኛውን የመኖር ጊዜ ለማራዘም የተሻለ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በጥቂቶቹ ላይ የታየው ውጤት ደግሞ ጅኑ ካልተሰጣቸው ሰዎች በእጥፍ በተሻለ ሁኔታ መገኘታቸው ነው፡፡
 
< Prev   Next >