| አስቸኳይ ፀረ ድህነት እንቅስቃሴ... |
|
|
| Wednesday, 23 April 2008 | |
|
አስቸኳይ ፀረ ድህነት እንቅስቃሴ በአፍሪካ እንደሚያስፈልግ ባንኪሙን አስታወቁ
አለማቀፋዊውን የድህነት ቅነሣ ዕቅድ ከግብ ለማድረስ በተለይም ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገሮች የተዛመተውን ድህነት ለማጥፋት ሁሉም ተባብሮ መሥራት እንዳለበት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ባንኪሙን እንዳስታወቁ አጃንስ ፍራንስ ዘገበ፡፡ ሰኞ አክራ፤ ጋና በተደረገው ስብሰባ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት መድረስን በማረጋገጥ፣ የጤና አገልግሎትን በማሻሻልና በኤች.አይ.ቪ ላይ የተሻለ በመሥራት በ2015 ድህነትን በግማሽ ለመቀነስ ያቀደውን የሚሊኒየሙን የልማት ጎል ከግብ ማድረስ ይቻላል ብለዋል፡፡ ንግድና ልማትን በተመለከተ በተደረገው በዚህ ስብሰባ ሴኔጋል በውሃ፣ ኒጀር ቶጎና ዛቢያ ደግሞ በወባ ቁጥጥርና አጎበር ዕደላ ሥራዎች ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል፡፡ ባንኪሙን በጋና፣ በኬንያ፣ በታንዛኒያና በኡጋንዳ የታየውን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት መስፋፋትን እንደምሣሌ የጠቀሱት ፀሐፊው ይህ የስኬት ታሪክ በሁሉም የአፍሪካ ሀገሮች ተስፋፍቶ ከአለም አቀፍ ማህበረሰብ እርዳታ ጋር መጣጣም ይኖርበታል ብለዋል፡፡ በስብሰባው አንዲት ሀገር ብቻ ሳትሆን ከሰሀራ በታች ያሉት ሀገሮች ሁሉ በ2015 ግብ ይመታል ተብሎ ለታቀደው ፕሮግራም መፈፀም አስጊ ናቸው ተብሏል፡፡ የምግብ ምርትን በአስቸኳይ በመጨመር፣ የዋጋን ንረት በመቀነስና በተከሰተው ቀውስ ላይ መሠረታዊ ለውጥ በማምጣት የበለፀገ ዜጋን ለመገንባት ሁሉም ቃል ይግባ ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ከ2007 አጋማሽ በኋላ በመላው ዓለም 40 ከመቶ የምግብ ዋጋ ጭማሪ የታየ ሲሆን ይህም በካሜሩን፣ ቡርኪናፋሶ፣ ሃይቲና ግብፅ ላይ ግጭቶችን ቀስቅሷል፡፡ ባንኪሙን ቡርኪናፋሶንና አይቬሪኮስትን በሚቀጥለው ሳምንት ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ቻይና የፈረንሣይ መሆኗን ቀጠለች ቻይናና ፈርንሣይ ልዩነታቸውን እንዲያጠቡ ይጠበቃል፡፡ ከኦሎምፒክ ችቦ ዝውውር ጋር በተያያዘ በቻይናና በፈረንሣይ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት የሚቀረፍ ቢሆንም እንቅፋቶች እንዲወገዱ ጥሪ ቀረበ፡፡ የብሄራዊ አንድነት ተምሳሌት የሆኑት ጂን ጂንግ እንደገለፁት ለፈረንሣይ ፕሬዚዳንት ይቅርታ ከማድረግ ተቆጥበዋል፡፡ የፈረንሣዩ ሴናትር ክርስቲያን ፓንክሌት ሰኞ ሻንጋይን በጎበኙበት ወቅት ለአካለ ስንኩሏ አትሌት ደብዳቤ ቢሰጡም ጂን “ፕሬዚዳንቱ በተገቢ መልኩ ይቅርታ አልጠየቁኝም” ብለዋል፡፡ ደብዳቤውን በተመለከተም “ፍርሃትና ከለላ መጠየቅ እንጂ ይቅርታ መጠየቅ አይደለም” ሲል የቤጂንግ ዜና ዘግቧል፡፡ የቲቤቱን እንቅስቃሴ በተመለከተ የፈንሣይ ከንቲባ ቤትራላንድ ዴላኒዮ “የሰላም ሻምፒዮን” ሲሉት ለሚያደርጉት የነፃነት ትግልም ፈረንሣይ ዕርዳታ እንደምታደርግ ገልፀዋል፡፡ የቲቤታዊያኑ ተቃውሞ ወር ድረስ በዋና ከተማዋ ላሣና በሌሎችም የቻይና አካባቢዎች ቀጥሏል፡፡ በተቃውሞው ቻይና 18 ሲቪሎችና 2 ፖሊሶች ተገድለዋል ቢሉም የቲቤት ተቃዋሚ መሪዎች ደግሞ 150 ሰዎች ተገድለዋል ይላሉ፡፡ ሱዳን ወሳኝ ምዝገባ ጀመረች ሱዳን ከ15 ዓመታት ቆይታ ማክሰኞ ፀጥታዋን አገኘች፡፡ በአፍሪካ ረጅሙን የሲቪል ጦርነት ለማብረድ የመሠረት ድንጋይ አኖረች፡፡ ፀጥታው የመቀጠሉ ሁኔታ አሳሳቢ ነው ሲል ኤ ኤፍ ፒ ዘገበ፡፡ በ2005 በሁለቱ የሰሜንና የደቡብ የጦር መሪዎች መካከል በተደረገው መሰረት በሁለቱ ሳምንታት ቆይታ ውስጥ ለሚደረገው ብሄራዊ ምርጫ ሁለቱም ተወካዮች ያዘጋጃሉ፣ በማዕከላዊ መንግሥት የሚጋሩትን የሀብት መጠንም ግልፅ ያደርጋሉ፡፡ ይሁን እንጂ ያላደገው የደቡቡ የዳርፉሩን ስምምነት በመቃወም ምዝገባውን አቋርጧል፡፡ ካርቱም “ሱዳን ከብሪታንያን ቅኝ ግዛት ነፃ ከወጣችበት ከ1956 በኋላ የተደረገ ከፍተኛ የሕዝብ ቆጠራ ነው” ብላለች፡፡ ሱዳንና የአለማቀፍ ማህበረሰብ 103 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ባደረጉበት በዚህ ቆጠራ 40 ሚሊዮን ከሚጠጋው ሕዝብ ውስጥ 200 ታዛቢዎች በተሣተፉበት 60,000 ሰዎች ተመዝግበዋል፡፡ በሚያዚያ ወር ታይቶ የማይታወቀው ዝናብ ማክሰኞ የዘነበ ሲሆን ቆጠራው ግን በኤሌክትሪክ መቋረጥ ምክንያት እንኳ አልተቋረጠም ነበር፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |