| ሴቶች በማደግ ላይ ባሉ በሚከሰት.. |
|
|
| Wednesday, 23 April 2008 | |
|
ሴቶች በማደግ ላይ ባሉ በሚከሰት በሽታና ጦርነት ተጠቂ ናቸው
በማደግ ላይ ባሉ አገሮች ድህነት፣ በሽታ፣ መፈናቀልና ጦርነት ሲከሰት፣ ሴቶች የበለጠ ተጋላጭ እንደሚሆኑ ተገለፀ፡፡ “የሴቶች ትምህርትና ለኤች.አይ.ቪ ተጋላጭነት” በሚል ርዕስ ላይ እንደተገለፀው፣ የችግሩ ገፈት ቀማሾች የሆኑትን ሴቶች የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ትምህርት አይነተኛ መሳሪያ መሆኑን፣ በአመራር ያሉ አፍሪካውያን ሴቶችም የሌሎችን ሴቶች ድምፅ በማሰማትና ችግሮቻቸውን በመጋራት ንቁ ተሳትፎ ሊያደርጉ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡ (ዋኢማ) የፓልም ዘይት በተመጣጣኝ ዋጋ ሊቀርብ ነው በአገሪቱ እየታየ ያለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት አንድ ሊትር የፓልም ዘይት ዋጋ በ14 ብር ማከፋፈል ሊጀመር ነው፡፡ ዘይቱ በአህፋ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አማካኝነት ከማሌዢያ ሁለት ሚሊዮን ሊትር አስመጥቶ ከጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ በማስገባት ላይ እንደሚገኝ፣ ከትናንትና ጀምሮ ማከፋፈል እንደሚጀምር በአዲስ አበባ፣ በሻሸመኔ፣ በመቀሌ፣ በባህር ዳር፣ ጐንደር፣ ጅማ፣ ሀዋሳና ወሊሶ እንደሚያከፋፍል፣ በተለይ አዲስ አበባ በማህበሩ ማከፋፈያ ቦታዎች፣ ተክለሃይማኖት አካባቢ መሀል መርካቶ ባንክ ጀርባና ሲዳሞ ተራ የሚያከፋፍል መሆኑን ገልጿል፡፡ (ኢዜአ) በአስረኛው ዓመተ ዓለም የተገነባ ህንፃ ፍርስራሽ ተገኘ በአክሱም ከተማ የንግሥት ሣባ ቤተ መንግሥት በነበረበት የፍርስራሽ ህንፃ አካባቢ በአስረኛው ዓመተ ዓለም የተገነባ ሌላ የሕንፃ ፍርስራሽ መገኘቱን የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የሕንፃ ፍርስራሹ የተገኘው በኘሮፌሰር ሒልመት ለገርት የሚመራ የጀርመን አርኪኦሎጂስት ቡድን ከጥር ወር 2ዐዐዐ ባካሄደው የከርሰ ምድር ጥናት መሆኑን፣ በአስረኛወ ዓመተ አለም ተገንብቷል ተብሎ እንደሚታመን፣ በፋሩም የተለያዩ ቅርሶች አብረው መገኘታቸውን፣ አንድ የታሪክ ባለሙያ በሰጡት አስተያየት እ.ኤ.አ 1960ዎቹ በፍራንሲስ አፍሬይ የተገኘውና ከ50 በላ ክፍሎች ያለት የንግስተ ሳባ ቤተ መንግሥት ሳይሆን አይቀርም የተባለለትን ሕንፃ ትክክለኛነት እንደሚያረጋግጥ ተናግረዋል፡፡ (ኢዜአ) ኮሌጁ ወደ ዩኒቨርሲቲ ለማሸጋገር ጥረት እየተደረገ ነው የቅድስት ልደታ ለማርያም የጤና ሳይንስ ኮሌጅን ወደ ዩኒቨርሲቲ ለማሸጋገር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አስታወቁ፡፡ ፓትሪያርኩ ከኮሌጁ መምህራንና ተማሪዎች ጋር በተወያዩ ወቅት፣ በኮሌጁ ውስጥ ያለው ያለውን ጤናማ የመማር ማስተማር ሂደት የበለጠ በማጠናከር ኮሌጁን ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ለማሸጋገር ጥረቱ መቀጠሉን፣ የትምህርት መሳሪያዎችን ለማሟላት ቤተ ክርስቲያኒቱ አቅሟ በፈቀደ በመንቀሳቀስ ላይ እንደምትገኝ አስታውቀዋል፡፡ (አዲስ ዘመን ሚያዚያ 12 ቀን 2ዐዐዐ) ባለሥልጣኑ 186 አዲስ ደረጃዎችን አፀደቀ የኢትዮጵያ ጥራትና ደረጃዎች ባለሥልጣን በተለያዩ መስኮች የተዘጋጁ 186 የኢትዮጵያ ደረጃዎችን ማፅደቁን አስታወቀ፡፡ ከፀደቁት ደረጃዎች መካከል ለግንባታ የሚያገለግሉ መሳሪያዎችና ኮምፒውተርን በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ለመጠቀም የሚያስችል፣ ጥሬ ቆዳና ሌጦ እንዲሁም በከፊል የተለፋ ቆዳ የቴክኒክ ዘርፎችን የሚመለከቱ ደረጃዎችም ከፀደቁት መካከል ይገኙበታል፡፡ (አዲስ ልሣን ሚያዚያ 11 ቀን 2ዐዐዐ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |