Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow የስሜት ማዕበል ለምን ያናውፀናል?
የስሜት ማዕበል ለምን ያናውፀናል? Print E-mail
Saturday, 26 April 2008
ሙሴ ፍፁም

አንዳንድ ጊዜ ባልታሰበና ባልተጠበቀ ሰዓት ለሚታዩ ክስተቶች በአነስተኛም ይሁን በበርካታው ሕዝብ ዘንድ የ"ሰጠው ምላሽ ወይም ትኩረት ጥያቄ የሚያስነሳ ይሆናል፡፡ ትኩረት ተሰጥቷቸው መፍትሔው ከወዲሁ ካልተፈለገላቸው ለሁሉም የሚዳረስ አደጋ ያዘሉ ቢሆንም እንኳ ዘወር ብሎ የሚያያቸው በጣም ጥቂቱ የሚሆንበት ጊዜ አለ፡፡ ተመሳሳይ ድርጊቶች በየራሳችን ወይም በቅርባችን እስኪፈጠር ድረስ የሃገር ጉዳይ እንኳ ቢሆን፣ የፍትህ ጉዳይ እንኳ ቢሆን በደመምታ ይታለፋሉ፡፡ ውሎ አድሮ ግን ተመልሶ በራስ ላይ እባብ ከመጠምጠም የከፋ ችግር እንደሚያስከትል እንረሳዋለን፡፡

 

የዚህች ሃገር ዜጎች የሆንን ሁሉ ወይም በአብዛኛው አሸባሪነትን እንደምናወግዝ ይሰማኛል፡፡ አሸባሪ ማነው? በሚለው ትንተና እንለያይ እንደሆነ እንጂ ሽብርን እንደሸብር የሚደግፍ ብዙም ያለ አይመስለኝም፡፡ በዚች ሃገር ፍትህ እንዲሰፍን የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ፣ ሕግ ለድሃውም፣ ለሀብታሙም፣ ለወንዱም፣ ለሴቱም፣ ለወጣቱም፣ ለሽማግሌውም፣ ለታዋቂ ባለሙያውም፣ በሙያው ለማይታወቀውም እኩል እንዲሆን፣ እኩል እንዲተገበር የማይፈልግ ሰው ያለ አይመስለኝም፡፡ ባይሆን በፍትሕ ሂደቱ ላይ ያከራክረን ይሆናል እንጂ ደካማውን ከጉልበታሙ የሚታደገው የሕግ የበላይነት ሲሰፍን መሆኑ በማንም ዘንድ የታመነ ይመስለኛል፡፡

ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሁለት ፍንዳታዎች ደርሰዋል፡፡ ሁለቱም በነዳጅ ማደያ ላይ የተደረጉ ሲሆን ሁለቱም በኖክ ነዳጅ ማደያን ያነጣጠሩ ናቸው፡፡ ፍንዳታው ከተፈፀመ ጀምሮ በጋዜጦችና በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ የተሰጠው ሽፋን ማነስና በሕዝቡም ዘንድ ሊያስከትል የሚችለው ስጋት ታስቦ መነጋገሪያ ሲሆን አላየሁም፤ ወይም ያየሁ አልመሰለኝም፡፡ ለምን ይሆን?

የኖክን ነዳጅ ማድያ ለማጋየት የተጠመደ ፈንጂ በምንም መለኪያ ቢሆን አደጋው ከባለቤቱ ይልቅ ሰላማዊውን ዜጋ እንደሚጎዳ አያከራክርም፡፡ ማደያው ቢቀጣጠል የሚያደርሰው ጉዳት በአካባቢው ዙሪያ በሚንቀሳቀሱ ሰዎችና በቤቶች ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር አይደለም፡፡ በድርጅቱ የሚሰሩትና አገልግሎት ለማግኘት ወደ ማደያው በሚሄዱት በአካልና በሕይወታቸው ላይ አደጋ ይወድቃል፡፡ አሁንም የታየው ይኸው ነው፡፡ መጀመሪያውኑ ፈንጂው በማደያዎች ላይ እንዲያነጣጥር ሲደረግና ሲመረጥ የሕዝብን ጥፋት ተፈልጐ እንደሆነ መገመት ይቻላል፡፡

አሁን በተጨባጭ በታየው አደጋም ቢሆን የተጎዱት ሰላማዊ ዜጎችና ዝቅተኛ ኑሮ የሚኖሩ ናቸው፡፡ ሰው ሆኖ ስለተፈጠረ ብቻ አደጋ እንዲደርስበት ታስቦና ታቅዶ? ፈንጅ መቅበር፣ ከአሸባሪነት በስተቀር የፖለቲካ ዓላማ ሊያራምድ ይችላል ተብሎ አይታሰብም፡፡ የኑሮ ውጣ ውረድ ያንገላታቸው፣ ባላሰቡትና ባልጠበቁት ሁኔታ እንዲገደሉ ለአካል መቁሰል እንዲዳረጉ ማድረግ የጨካኝነትና የአረመኔነት ምግባር ከመባል ሌላ ምን ስም ሊሰጠው ይችላል?

ድርጊቱን የፈፀመው ቡድን ወይም ግለሰብ የእነዚህን ንፁሐን ደም መፍሰስ ብቻ ዓላማው አድርጎ የተንቀሳቀሰ ካልሆነ በቀር ሌላ ዓላማውን በዚህ መንገድ ለማስፈፀም ይችላል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ዛሬ ከጎናችን በድንገት የተለዩትን ወገኖቻችንን ማሰብና ማዘን መጨነቅና መጠበብ ግዳጃችን መሆን ያለበት ይመስለኛል፡፡ አደጋው በኛና በቤተሰባችን ላይ ቢደርስ የሚደርስብንን የልብ ስብራት ለእነሱም ማድረግ አለብን፡፡ ከዚህ በላይ ሊያነጋግረንና ሊያሳስበን የሚችል ጉዳይስ ምን አለ?

ይኸ የግፍ ሥራ፣ በሌላ በኩል በአደጋ ውስጥ እንዳለን የማስጠንቀቂያ ደውል ሊሆነን ይገባል፡፡ ዛሬም ሆነ ቀደም ብለው በመጓጓዣዎች ላይ፣ በመንገድና በግንባታዎች የተቀበሩት ፈንጅዎች የወገኖቻችንን እድሜ መቅጠፉን እያስታወስን ድርጊቱ በጋለና በጠነከረ መንፈስ መቃወም ይገባናል፡፡ አለበለዚያ "ሞኝ ልጅ የአባቱ ቤት ሲቃጠል ሊሞቅ ይቀርባል" እንደሚባለው ይሆናል፡፡

በዚህ ረገድ ሁኔታውን የሚዲያ ሽፋንና የሕዝቡንም ስሜት ስመለከት አደጋው አስፈሪና ልንጠነቀቀው የሚገባ የኛው አደጋ መሆኑን የተገነዘብን አልመሰለኝም፡፡ የቦንብ ፍንዳታው የአንድ ሰው ጉዳይ አለመሆኑን ተገንዝበናል ወይ? የሚል ስሜትም ፈጥሮብኛል፡፡ የሽብር ድርጊት፣ የጥፋት ሥራው የኖክ ኩባንያ ላይ በመታየቱ የኖክ ጉዳይ ብቻ ተደርጎ መወሰድ የለበትም፡፡ ወይም በግፍ ደማቸው የፈሰሰው ዜጎች ጉዳይ አይደለም፡፡ ዛሬ እኛ የአደጋው የመጀመሪያ ተጠቂ ባለመሆናችን በግድየለሽነትና በአይመለከተኝም ስሜት የምናየው ሊሆን አይገባም፡፡ ነገ የሁሉንም በር የሚያንኳኳ መሆኑን አንርሳ፡፡

የጥላቻ ወይም የመውደድ ስሜት ሳያሸንፈን ግምታችንን ለመነጋገር ከቻልን በርካታ ጥያቄዎች ልናነሳ እንችላለን፡፡

የኖክ ኩባንያ የሼህ መሐመድ አላሙዲ ንብረት መሆኑን ሰምቼያለሁ፡፡ ድርጊቱን የፈፀሙት አሸባሪዎች መቼም ኖክን በማቃጠል የሼህ መሐመድን የፋይናንስ አቅም እናንገዳግዳለን፤ ብለው የሚያስቡ ሞኞች ናቸው ብዬ አልገምትም፡፡ ከዚያ ይልቅ አደጋውን በሕብረተሰቡ ላይ ለመፈፀም የፈለጉ መሆናቸው ነው የሚገባኝ፡፡

አንዳንዶች እንደሚገምቱት በአንድ ቀን በተቀራረበ ሰዓት ሁለት የኖክ ነዳጅ ማዲያዎች ፈንጂ እንዲፈነዳባቸው መደረጉ ምናልባት ባለሃብቱ በሃገራችን ላይ በጀመሩት ታላቅ ኢንቨስትመንታቸው፣ የሚያናድዳቸውና የሃገሪቱ ልማት እድገት የሚያስፈራቸው፣ ኢትዮጵያን እንደሃገር፣ ጠላት ብለው የፈረጁ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ስለዚህም ከአፍንጫ ሥር ባለፈ አስተሳሰብ ባለሃብቱ እንዲደናገጡና ኢንቨስትመንታቸውን እንዲስቡ ለማድረግ ታስቦ ይሆናል፡፡ ከዚህ አኳያ የድርጊቱ ፈፃሚዎች ያሰቡት ይሳካላቸው ይሆናል፤ አይሆንም፤ የምንለውን እንተወው ብንል እንኳ፣ በዚህ በኩል ኢላማው ሕብረተሰቡን በመጉዳት ላይ ያነጣጠረ እቅድ መሆኑ በግልፅ ይታያል፡፡

በኢንቨስትመንቶቹ መታጠፍ ከባለሃብቱ ይልቅ የሚጎዳው ኢትዮጵያዊው ነው፤ ሕዝብ ነው፤ ሃገር ናት፡፡ ማንም ሰው በተለይም እንደ ሼህ መሐመድ ያለ ኢንቨስተር በሃገሩ ላይ ቀልቡን ጥሎ ሰፊ ተግባር እያራመደ ባለበት ወቅት የሽብርተኞች ማስፈራሪያ ያስደነግጠዋል፤ ተብሎ አይታሰብም፡፡ ስለዚህም የአሸባሪዎች ጥቃትና ኢላማ የፈረደበት የኢትዮጵያ ሰላማዊው ሕዝብ መሆኑን እስከ እግር ጥፍራችን ድረስ ዘልቆ ልንረዳ እንችላለን፡፡

እንዲህ ዓይነቱ በሕዝብ ላይ የተቃጣ ክፉ ተግባርን መመከት የሁሉም ጉዳይ መሆን አለበት፡፡ ሌሎች ልጆቻችን ሳይሞቱ፣ ሌሎች ተቋማት ሳይፈርሱ ቀድሞ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ባለሃብቱን በስሜታዊነት ተነስተው የሚደግፉም ሆነ የሚቃወሙ ካሉ ያ ሌላ ጉዳይ ሆኖ ፍንዳታውን ማዬት ያለባቸው ከሃገር አኳያ ብቻ መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ ልንነጋገርበት ይገባል፤ ሊያስጨንቀን ይገባል፤ አደጋው እንዳይቀጥል ምን እናድርግ ማለት አለብን፡፡ በዝምታና አንዳችም ነገር እንዳልተፈጠረ፣ ቢፈጠርም ቀላል እንደሆነ ሁሉ ጋዜጦች ገፃቸውን ሊዘጉ አይገባም፡፡ ሼህ መሐመድ መተቸት ባለባቸው፣ በፖለቲካ አቋማቸው ጭምር አስተያየት መስጠት ትክክል የመሆኑን ያህል ማንኛውም ንብረታቸው በሽብር አደጋ ላይ ሲወድቅ እንደራሳችን መቁጠር የግድ ነው፡፡ ያን ጊዜ ጉዳዩ የሃገር ይሆናል፡፡

ይኸንን ያመጣሁት አንዳንዶች ውዴታቸውንና ጥላቻቸውን በስሜት ስለሚያደርጉት፣ አጠቃላይና ተጨባጭ እውነታው እየተጋረደብን የኖክ ማደያ ፍንዳታን የግለሰብ ጉዳይ አድርገን ዝምታችንን ማፅናታችንና መነጋገሪያችን አለመሆኑ አግባብ ስላልመሰለኝ ነው፡፡

በሌላ በኩልም ሰሞነኛው ወሬ የቴዲ አፍሮ (የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን) በወንጀል ድርጊት ተጠርጥሮ ፍርድ ቤት መቅረቡና መታሰሩ ነው፡፡ ቴዎድሮስ ተደናቂ ድምፃዊ መሆኑ አይካድም፡፡ ወደፊትም ዕድሜና ጤና ካገኘ ለሃገራችን ሙዚቃ እድገት ከፍ ያለ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ አይጠረጠርም፡፡ በእስካሁኑ ሥራዎቹ የሃገራችን ዜማና ግጥም ከሴቶች ፍቅር አውጥቶ፣ ወደ ሃገርና ወደ ወገን ፍቅር የለወጠው እሱ ነው፤ ብዬ አምናለሁ፡፡ ወቅታዊና ልብ ሰንጥረው የሚገቡ ዜማዎች ለማቅረብ የቻለ አርቲስት ነው፡፡ ቴዲ አፍሮ በዚህ ሙያው በርካታ ደጋፊ አፍርቷል፡፡ ይኸ አንድ ነገር ነው፡፡

አሁን የተከሰሰበት ግን በነፍስ ማጥፋት ወንጀል ተጠርጥሮ ነው፡፡ ሟቹም ኢትዮጵያዊና ገና "ቀን ያልወጣለት"ና የኑሮ ከባድ እጅ የተለቀ ነበር፡፡ በአማሟቱ የሚታዘንለት ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ ይኸንን ወንድማችንን አርቲስቱ እንዳልገደለው በወንጀሉም የሌለበት መሆኑን በተደጋጋሚ ገል"ል፡፡ በሌላ በኩል ዐቃቤ ሕግና ፖሊስ ማስረጃ አለን ብለዋል፡፡ እንዲያ ከሆነ እንደራሳችን እንፍረድ፡፡ እስከ ዛሬ በቆየው አሰራር ሰው በድብቅም ሆነ በግልጽ ሲገድል አጣርቶ የሚያቀርበውና የሚመረምረው ፖሊስ ነው፡፡ ዐቃቤ ሕግም ማስረጃውን መዝኖ ወደ ፍርድ ቤት ይወስዳል፡፡ ፍርድ ቤት ደግሞ ግራ ቀኙን አይቶ የደረሰበትን ውጤት መሠረት አድርጎ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ ይኸ አሰራር ሃብታም ወይም ድሃ ስለሆነ፣ አርቲስት ወይም ገበሬ ስለሆነ". አይናወፅም፤ አይለወጥም፡፡

በተለይም ወገን ለሌላቸው፣ ደጋፊ ላጡ ደማቸው ደመ ከልብ ሆኖ እንዳይቀር ሊጠብቃቸው የሚገባው የፍትህ አካሉ ነው፡፡ የፍትህ አካሉን የምንጨቀጭቀው ለማንም ሳያዳላ ወንጀልን እንዲከላከል እንጂ፣ እንደተጠርጣሪው ሁኔታ የተለያየ ደንብ እያወጣ በራሱ ፈቃድ እንዲፈፅም አይደለም፡፡ ስለዚህ ማንም በሕግ ፊት እኩል ነው የምንል ከሆነ ሁሉም እኩል መስተናገድ አለበት፡፡

የቴዲ አፍሮ ጉዳይ በፍርድ ቤት የተያዘ በመሆኑ በክሱ ላይ አስተያየት ለመስጠት አልፈልግም፡፡ ነገር ግን በደጋፊነት ስም ወደ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሄዱ አድናቂዎቹ በጩኸት የገለፁት አንዳንድ ንግግሮቻቸው ትክክል አልመሰሉኝም፡፡ አርቲስቶች እንዲፈታ ሰልፍ ሲያደርጉ አባባላቸው በራሱ ግራ ያጋባል፡፡ ሰልፉ ውዴታ"ቸውን ለመግለፅ ነው? ወይስ ቴዲ ወንጀል ሊሠራ አይችልምና ይፈታ ከሚል ግምት ነው? ወይስ ቴዲ ወንጀል ቢሰራም ሊከሰስና ሊወቀስ አይገባም ነው?

ማንም ይሁን ማን የአንድ ንፁህ ዜጋ ደም መፍሰሱ በፖሊስ ተረጋግጧል፡፡ ፖሊስ ፈፃሚውን በማስረጃ አስደግፌ አቅርቤያለሁ ብሏል፡፡ ከዚህ በኋላ ሚዛኑን መለካት የፍርድ ቤት ጉዳይ ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ አዳልቷል፤ አላዳላም፤ ለማለት ሂደቱን መከታተል አለብን፡፡ በዚያ ሂደት ቴዲ ነፃ ከወጣ ደስታችን ነው፡፡ በዚያው ልክ የዚያ ወጣት ደም ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር የፍትህ አካላቱን መጨቅጨቃችን አስፈላጊ ነው፡፡

ይኸን ስል ደጋፊዎቹ ለምን ፍርድ ቤት ሄደው ድጋፋቸውን ሰጡ ማለቴ አይደለም፡፡ ድጋፋቸው ግን ለአርቲስትነቱ እንጂ ከተከሰሰበት ጉዳይ ጋር መሆን የለበትም፡፡ ድጋፉ አድናቂዎች እንደ አንድ ቤተሰብ እውነታውን ለመስማት የሚሄዱ እንጂ ምንም ያድርግ ምን ቴዲ አይጠየቅም፤ ከሚል መነሻ መሆን የለበትምና፡፡

 
< Prev   Next >