Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ሴቶች እንቁላላቸውን እየለገሱ ነው
ሴቶች እንቁላላቸውን እየለገሱ ነው Print E-mail
Wednesday, 09 January 2008

የ..ኒውካስትል ፈርቲሊቲ ሴንተር..ን በመጥቀስ ቢቢሲ እንደዘገበው ለጥናት ይረዳ ዘንድ ሴቶች እንቁላላቸውን እየለገሱ ነው፡፡

..ኒውካስትል ኤን ኤች ኤስ ፈርቲሊቲ ሴንተር.. የተባለ የጤና ተቋም ከአንድ መቶ ሴቶች ውስጥ አስራ አምስቱን በመምረጥ የአይ.ቪ.ኤፍ. ሕክምና ለማድረግ አስቧል፡፡

በልገሳ በተገኘው እንቁላል ሕክምናው በቅርቡ በስድስት ሴቶች የሚጀመር ሲሆን ለዚህም በ1500 ፓውንድ የአይ ቪ ኤፍ ሕክምና ይደረግላቸዋል፡፡ ይህም ከተለመደው የህክምና ወጪ በግማሽ ያንሳል ተብሏል፡፡

የሕክምና ሳይንቲስቶቹ እንደተናገሩት፣ ለጥናታቸው ተጨማሪ እንቁላል ማግኘታቸው ለሴል ቴራፒ ሕክምና ይረዳል፡፡ ይህ ሕክምናም በተለይ ለፓርኪንሰንስ ጥሩ መፍትሄ እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡

የ..ሂዩማን ፈርቲላዜሽን ኤንድ ኢምብሪዮሎጅ አውቶሪቲ..ም ጥናቱ የተቀላጠፈ ይሆን ዘንድ የ2 ዓመት የፕሮጀክት ፈቃድ ሰጥቷል፡፡

የጥናት ቡድኑ መሪ ፕሮፌሰር አሊሰን ማርዶች ..ከሴቶች ያገኘነው በጐ ምላሽ አስደስቶናል፡፡ ይህም ጥናታችንን የተሳካ ያደርገዋል.. ብለዋል፡፡ ፕሮፌሰሩ አክለውም ..ይህ የምንሰራው ጥናት በአይ.ቪ.ኤፍ ሕክምና አማካይነት መውለድ ያልቻሉ ጥንዶችን ባለልጅ ለማድረግ እንደሚያስችለን ባለሙሉ ተስፋ ነን.. በማለት ገልፀዋል፡፡

ሐኪሞች ምህፃረ ቃላት እንዳይጠቀሙ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ

ሰሞኑን ቢቢሲ ባወጣው ዘገባ መሠረት ዶክተሮች የሚጠቀሙዋቸው የህክምና ምህፃረ ቃላት ለታካሚው ሞት ምክንያት እየሆኑ ሲሆን ሀኪሞች ምህፃረ ቃል እንዳይጠቀሙም ማስጠንቀቂያ እየተሰጠ ነው፡፡

የእንግሊዝ ሜዲካል ዲፌንስ ዩኒየን ባወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው በሕክምና ምህፃረ ቃላት አለመነበብና አንዳንዴም ከአንድ በላይ ትርጉም መስጠት የተነሳ ታካሚዎች ችግር እየደረሰባቸው መሆኑን ገል..ል፡፡

ሪፖርቱ እንዳብራራው አንዳንድ ታካሚዎች ከተገቢው በላይ መድሃኒት የተሰጣቸው ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ የተሳሳተ ህክምና ተደርጐላቸዋል፡፡ እንደ ሪፖርቱ ገለፃ በቅርቡ በተደረገ ጥናት መሠረት በአሜሪካ ብቻ ከ30 ሺህ በላይ የህክምና ስህተቶች የተመዘገቡ ሲሆን 5 በመቶው ከምህፃረ ቃላት ችግር ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡

የእንግሊዝ ሜዲካል ዲፌንስ ዩኒየን አማካሪ የሆኑት ዶ/ር ሳሊ ኦልድ እንደጠቆሙት በምህፃረ ቃላት የተነሳ ከሚፈጠሩ ችግሮች መካከል የመድሃኒት ስምና መጠን ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛሉ፡፡ 

የቻይና ..አንድ ልጅ ለአንድ ቤተሰብ.. ፖሊሲ ተቀባይነት እያጣ ነው

በሕዝብ ብዛት ከፍተኛውን ድርሻ የምትይዘው ቻይና ይህን ቁጥር ከእድገቷ ጋር ለማመጣጠን አንድ ልጅ ለአንድ ቤተሰብ የሚል ፖሊሲ ብትከተልም ተቀባይነት እያጣ መሆኑን ዘገባዎች ጠቁመዋል፡፡

ዥንዋን ጠቅሶ ቢቢሲ እንዳመለከተው ከ90 ሺህ በላይ የሚሆኑ በሁቤ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች በ2007 ፖሊሲውን እንዳልተቀበሉት ታውቋል፡፡ ከእነዚህም 1..687 የሚሆኑት ባለስልጣናትና የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እንደሆኑ ተገል..ል፡፡

ቻይና ይህን ፓሊሲዋን ያረቀቀችው በ1970ዎቹ በአካባቢ ሲሆን ለከተማ ነዋሪዎች አንድ ልጅ ለገጠር አካባቢዎች ደግሞ ሁለት ልጅ ያውም የመጀመሪያ ልጅ ሴት ከሆነች ብቻ የሚል ነበር፡፡

ይሁን እንጂ ሃብታምና የልጆቻቸውን ወጪ የመሸፈን አቅም ያላቸው ዜጐች ፖሊሲውን ሳይተገብሩት ቆይተዋል፡፡

የቤተሰብ ምጣኔ ፕሮግራም ኃላፊ የሆኑት ያንግ ዩዋንግ ..የፖለቲካ ፓርቲ አባላት፣ ባለስልጣናትና ዝነኛ ሰዎች ፖሊሲውን እየጣሱ ነው.. ያሉ ሲሆን በአንዳንዶቹም ጉዳያቸው ምርመራ እየተካሄደበት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ቻይና አንድ ልጅ ብቻ ለሚወልዱ የጥቅማጥቅም ድጐማ የምታደርግ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ጤናማ ኑሮ ከዕድሜ ላይ 14 ዓመት ይጨምራል

የቫይታሚን ዲ እጥረት ለልብ ህመም ያጋልጣል

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘውተር፣ ብዙ አልኮል አለመጠጣት፣ አትክልትና ፍራፍሬ መመገብና አለማጨስ አንድ ሰው ከሚኖረው ዕድሜ 14 ዓመት እንደሚጨምሩ አንድ ጥናት አመለከተ፡፡

በ20 ሺህ ሰዎች ላይ ከአስር ዓመት በላይ በተደረገ ጥናት መሠረት ከላይ የተጠቀሱ ነገሮችን የሚያሟሉት የ14 ዓመት ዕድሜ ጭማሪ ሲኖራቸው የማያሟሉት ደግሞ በአራት እጥፍ የመሞቻ ጊዜያቸው ይፋጠናል፡፡

ጥናቱ የተካሄደው በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ካምብሪጅ ኤንድ ሜዲካል ሪሰርች ካውንስል አማካኝነት ከ1993 እስከ 2006 ሲሆን እድሜያቸው ከ45 እስከ 79 የሚጠጉ ሰዎች የጥናቱ አካል መሆናቸው ተገል..ል፡፡

በሌላ ዜና የቫይታሚን ዲ እጥረት ለልብ ህመም እንደሚያጋልጥ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የሃርቫርድ ሜዲካል ስኩል የጥናት ቡድንን ጠቅሶ ቢቢሲ እንደጠቆመው በተለይ የደም ግፊት ባለባቸው ሰዎች ላይ የበለጠ ችግር እንደሚያመጣ ተገል..ል፡፡

ቫይታሚኖች ዝቅተኛ የቶክሲክ ውጤት ያላቸው ሲሆን ቶክሲክን ለመቆጣጠርም ይረዳሉ፡፡ ቫይታሚን ዲ ከፀሃይ ብርሃን እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

 
< Prev   Next >