| የኢንቨስትመንት የግብር እፎይታ ደንብ ተሻሻለ |
|
|
| Saturday, 26 April 2008 | |
|
በጋዜጣው ሪፖርተር
በማምረቻ እና በአግሮ ኢንዱስትሪ፣ በመረጃና መገናኛ ቴክኖሎጂ ልማት፣ በግብርና ምርቶችን በማምረት ለውጭ ገበያ ለሚያቀርቡ ባለሀብቶች የግብር እፎይታ ጊዜ የሚሰጠውን ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አሻሻለ፡፡ ምክር ቤቱ ስለኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችና ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች ስለተከለሉ የሥራ መስኮች የወጣውን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ለማሻሻል በቅርቡ ደንብ ቁጥር 146/2000 የተሰኘ አዲስ ደንብ አውጥቷል፡፡ በዚሁ መሠረት በማምረቻ ኢንዱስትሪዎች፣ በአግሮ ኢንዱስትሪ ወይም የኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ቦርድ በሚያወጣው ዝርዝር መመሪያ በሚወስኑ የመረጃና የመገናኛ ቴክኖሎጂ ልማት ኢንቨስትመንት መስኮች ወይም የግብርና ምርት ዓይነቶች ማምረት ሥራ የተሰማራ ማንኛውም ባለሀብት ካመረተው ምርት ወይም ከሚሰጠው አገልግሎት ቢያንስ ከ50-75 በመቶ ለውጭ ገበያ የሚያቀርብ ከሆነ ለአምስት ዓመት ከገቢ ግብር ነፃ ይሆናል፡፡ ከ50 በመቶ በታች የሚያመርቱትን ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡ ወይንም ምርቱን ወይም አገልግሎቱን ለሀገር ውስጥ ገበያ ብቻ የሚያቀርቡ ባለሀብቶች ለሁለት ዓመት ከገቢ ግብር ነፃ እንደሚሆኑ ደንቡ ይጠቅሳል፡፡ ሆኖም የኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ቦርድ ምርቱን ወይንም አገልግሎቱን ለሀገር ውስጥ ገበያ ብቻ የሚያቀርቡ ባለሀብቶች የመብቱ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ መመሪያ ሊያወጣ ይችላል ይላል፡፡ ለተጠቀሱት የኢንቨስትመንት ተቋማት ብቻ ነባር ድርጅቶቻቸውን በማስፋፋት ወይንም በማሻሻል ከ25 በመቶ በላይ እሴታቸውን ካሳደጉ፣ የግብር ነፃ መብት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ ደንቡ አያይዞም ባለሀብቶች ለሠራተኞች ለአደጋ ጊዜ አገልግሎት የሚውሉ አምቡላንሶችን፣ ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ደንቡ ለአስጎብኚነት ሥራ ከዚህ ቀደም ከቀረጥ ነፃ እንዲገባ ይፈቅድ የነበረውን አንድ የመስክ ተሽከርካሪ ወደ ሦስት አሳድጎታል፡፡ ለሌሎች የኢንቨስትመንቶች እንደኘሮጀክቱ ዓይነትና ባህሪ የሚወሰኑ ተሽከርካሪዎችን በሚመለከት ወደፊት መመሪያ እንደሚያወጣ ጠቁሟል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
ከሁሉም በላይ መንግሥት...
የሶማሊያ ሠላም - ውሃ ቅዳ፤ ውሃ መልስ
በጌታቸው ንጋቱ
ሶማሊያ ማዕከላዊ መንግሥት ካጣች አሥራ ስምንት ዓመታት ሞላት፡፡ የሶማሊያ ሕዝብ አገር አልባ ሆኖ በስደት ከተበታተነ አሥራ ስምንት ዓመት ሆኖታል፡፡ ይህ ሂደት አሁንም አልቆመም፤ የአገሪቱ ዜጐች፣ ጐረቤት አገራትና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በሶማሊያ ሠላም ለማስፈን፤ ማዕከላዊ መንግሥት ለመገንባት ጥረት ያደርጋሉ፡፡
ባጃጅ እና ታክሲ በክልል ከተሞች
“እስካሁን ፕሮቶኮል በሕግ አልተወሰነም...
ዝክረ ቅዱስ ያሬድ ጳጉሜን 2 ይከበራል
ከስደተኝነት ወደ ባለሃብትነት
የማሕፀን ካንሠር
በምሕረት አስቻለው
“የማህፀን በር ካንሰር በሴቶች ላይ በብዛት የሚታየው የካንሰር አይነት ነው፡፡ ዲስፕላዣ ወይም ወደ ካንሰር የሚያመሩ ለውጦች ሲታዩ ከተደረሰበት ሕክምናው ቀላል ይሆናል፡፡ ዲስፕላዣ ወይም ወደ ካንሰር የሚያመሩ ለውጦች ሲታዩ ከተደረሰ የተጎዳውን አካል ብቻ ቆርጦ በማውጣት (cryosurgery)፣ ከዚያም በቀጣይ ሕክምናዎች ማከም ይቻላል፡፡ ህክምናዎች ካንሰር ካለበት ደረጃ አንፃር የሚሰጡ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ህግ ከወረቀት ዘሏልን?
በሠለሞን ጎሹ
በድምቀት እየተካሄደ ቆይቶ ዛሬ የሚጠናቀቀው የቤጂንግ ኦሎምፒክ ከመጀመሩ በፊት ቻይና ለአካባቢ ጥበቃ የምትሰጠው ትኩረት የላላ መሆኑን በማንሳት ምዕራባዊያኑ መገናኛ ብዙሀን ውርጅብኝ ሲያወርዱባት ነበር፡፡ ቻይና በቅርብ ዓመታት በኢኮኖሚው ረገድ ያደረገችው እምርታ ዜጎቿ በንፁህና ጤናማ አካባቢ ለመኖር እንዲችሉ ባለማድረጉ በርካታ ጥያቄዎች እየተነሱባት ይገኛሉ፡፡ የቻይና በቴክኖሎጂ መራቀቅ ለአካባቢ ጥበቃ ዋስትና የሚሰጥበት ስርዓት እስካልዘረጋ ድረስ ጥያቄዎቹ ወደፊትም ይቀጥላሉ፡፡
ጂን ብራንዲ አረቄ ቬርሙጥ ከመራራ
ዊስኪ ኮኛክ ቢተር ጂንጀርና ቢራ
በየመደርደሪያው ተቀምጠው በተራ
ሙዚቃው ሲያንባርቅ ከሩቁ ሲያቅራራ
ብልጭልጩ መብራት ግቡ ሲል ሲጣራ
የነእንኮዬ ገላ ሲያባብል ሲያበራ
ከደንበኞቼ አንዳንዶቹ ከመሸ ስልክ ማናገር እንደማይፈልጉ አጫውተውኛል፡፡ ተንቀሳቃሽ ስልካቸውን ይዘጋሉ፡፡ እኔ ለዚህ ድርጊታቸው ድጋፍ አልሰጠሁም፡፡ እንዲያውም ስልክ የመረጃ መሣሪያ በመሆኑ ቀንም ማታም ባይዘጋ ይሻላል ባይ ነበርኩ፡፡ እነሱ ደግሞ “የሚረባውም የማይረባውም” ስለሚመጣ መዝጋቱ ይመረጣል ብለውኛል፡፡ እኔን ለማሳመን የተለያዩ ምክንያቶችን ቢደረድሩም አልተቀበልኳቸውም፡፡ ለጽሑፍ የማይውል ምክንያትም ነግረውኛል፡፡ ለአላፊ አግዳሚው ስልክ ሰጥተው ሰላም አጣሁ ያሉም አሉ፡፡ አንዳንድ የመረቀኑ፣ የጠጡ ሰዎች ሰዓትን ከግምት ውስጥ አያስገቡም፡፡ ከሌሊቱ 6 ሰዓት፣ ከሌሊቱ 9 ሰዓት ደውለው የሚቀሰቅሱ ሁሉ አሉ፡፡
በምሕረት ሞገስ
ዛሬ እንደቀድሞው በተበላሹ መኪኖች ሥር እየተንከባለለ አይሠራም፡፡ የመካኒክነት ሥራውን ተወት አድርጐ ሞባይሉንና መፅሐፍ ቅዱሱን በጥቁር ቦርሳው አዝሎ በየመንገዱ ይዘዋወራል፡፡
በቤጂንግ ኦሊምፒክ በርካታ የመገናኛ ብዙሃን አዎንታዊም፤ አሉታዊም ዘገባዎችን ሲያቀርቡ ሰንብተዋል፡፡ ከነዚህ ውስጥ ፎርዝ ፕሌስ ሜዳል የሚባል ድርጅት አሜሪካ ላገኘችው 36 የወርቅ ሜዳሊያዎች ክብር በሚል በኦሊምፒክ የታዩ አስገራሚ መረጃዎች አስነብቧል፡፡
ሩሲያ በፖላንድ ላይ የኒዩክሌር ጥቃት እንደምትፈጽም አስታወቀች
የዩናይትድ ስቴትስና የፖላንድ የፀረ ሚሳኤል ግንባታ ስምምነት አዲስ የጦር መሳሪያ እሽቅድምድም እንደሚፈጥር ያስጠነቀቀችው ሩሲያ በፖላንድ ላይ የኒዩክሌር ጥቃት ልትፈጽም እንደምትችል አስታውቃለች፡፡
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |
Share your thought and ideas with others on our public forum. Just register here and participate on our new and improved forum. Note that all members of the old version forum have to register again to post on the new version forum.