Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ፆሙ ይራዘምልን! ፋሲካው ይተላለፍልን!
ፆሙ ይራዘምልን! ፋሲካው ይተላለፍልን! Print E-mail
Saturday, 26 April 2008
Imageፆም ይራዘምልን ፋሲካ ይተላለፍልን ስንል ይበልጥ ለመፅደቅ አመቺ ሁኔታ ይፈጠር ይሆናል ከሚል አይደለም፡፡ የበሬው፣ የበጉ፣ የዶሮው፣ የእንቁላሉና ሌሎች ከፋሲካ ጋር የሚሄዱ ውድ ነገሮች ስለመጡ ነው፡፡

የሥጋ ተወድዷል ስንል የጾም ምግብም ቢሆን ርካሽ ነው ማለታችን አይደለም፡፡ በርበሬና ጨው አሳሳቢ የአስቤዛ አጀንዳ መሆን ከጀመሩ ቆይተዋልና፡፡

ያለው አማራጭ ወይ ፆሙ እንዳያልቅ "በመፀለይ" ሥጋ የማይበላው በፆሙ አለማለቅ ምክንያት ነው እያልን ራሳችንን እያፅናናን መቆየት አልያም ደግሞ እስክንዘጋጅ ድረስ ፋሲካው እንዲራዘምልን መመኘት ነው፡፡

ቅቤ ዘጠና ብር እንዴት ሊሆን ቻለ? ምክንያቱ በትክክል አይታወቅም፡፡ ዘንድሮ የዓለም የምግብ ዋጋ በመናሩ ብቻ ሳይሆን ትክክለኛ ምክንያት በትክክል ለማስቀመጥ አስቸጋሪ መሆኑም ጭምር ነው፡፡

ይህን ሁኔታ ግን ማስተካከል ይቻላል፡፡ የመንግሥታትም የአገራችንም የምግብ ፖሊሲና የእርሻ ፖሊሲ መጠናከር መስተካከልና መለወጥ አለበት፡፡

ሰሞኑን በተካሄደው ከማሟያ ምርጫ አሸናፊነት ጋር የኢሕአዴግ መንግሥት ለሕዝብ ይዞ መቅረብ ያለበት አዲስ ነገር ጠንካራ የምግብና የእርሻ ፖሊሲ ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ በገጠር ያለው ሁኔታ የተሻለ ነው፡፡ የእርሻ ጥናት ከንግድ ጋር ተያይዞ ገበሬውን እየጠቀመው ነው፡፡ መንግሥት ከግል ባለሙያዎች ጋር ሆኖ እያሰበው ያለው አሻሻጥ ሁኔታ (ስቶክ ኤክስቼንጅ ዓይነት) ይበልጥ አምራቹንም ሸማቹንም የሚጠቅም ይሆናል፡፡

ሆኖም ግን ከዚሁ ጋር በተያያዘ የውጭና የአገር ውስጥ ባለሀብቶች ወደ እርሻ የሚገቡበት ስልት ሊፈጠር ይገባል፡፡ ይህም በፖሊሲ መደገፍ አለበት፡፡

የዓለም ባንክና የአለም የገንዘብ ድርጅት ታዳጊ የአፍሪካ አገሮች መሰረት ስለሌላቸው ሙሉ ድጋፍ ሊሰጡ ይገባል፡፡ ዕዳ ስረዛ እንዲደረጉና የተሰረዘው ዕዳ ለኢንቨስትመንት የሚውልበት መንገድ መመቻቸት አለበት፡፡

ሚሊንየም ዴቨሎፕመንት ጎል የሚባለውም ከዚህ የእህል ጥረት ጋር በተያያዘ መፍትሔ ካላመጣ ተረት ተረት ይሆናል፡፡

ይህን ጉዳይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና የበለፀጉ አገሮች በልዩ ፕሮግራም ሊያስተካክሉት ይገባል፡፡

እነዚህ ሁሉ ጥረቶች ከተደረጉ የምግብ እህል ችግሩ ሊፈታ ይችላል፡፡ እስካሁን ይህ አለመደረጉ መንግሥታት የሚወቀሱበት ነው፡፡

ተጨማሪ ወቀሳ እንዳይመጣ ግን አስቸኳይ እንቅስቃሴ ያስፈልጋል፡፡ ዋናው ደግሞ እርሻ ላይ ማተኮር ነው፡፡ ፖሊሲያችን አሰራሮችን መገደፍ ነው፡፡

ይህ ሲደረግ ነው መልካም የጥጋብ ፋሲካ ሊመጣ የሚችለው፡፡ ካልተደረገ ሥጋን ሌሎችንም በገንዘብ ገዝቶ መብላት አዳጋች ነው፡፡ ስለዚህ

ፆሙ ይራዘምልን! ፋሲካው ይተላለፍልን! ማለታችን አይቀርም፡፡
 
< Prev   Next >