| ኢትዮጵያ በመስጊድ የግድያን ውንጀላ አስተባበለች |
|
|
| Saturday, 26 April 2008 | |
|
በጋዜጣው ሪፖርተር
የኢትዮጵያ ወታደሮች በሶማልያ አንድ መስጊድ ውስጥ 21 ሰዎች ገድለዋል የሚል የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ውንጀላ ከ"እውነት የራቀና" "ኘሮፖጋንዳ" በማለት አጣጣለች ሲል ሮይተርስ ዘግበዋል፡፡ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድን "አምነስቲ ኢንተርናሽናል" ባለፈው ረቡዕ ከዚህ በፊትም በፀረ ዓማፂዎች ዘመቻ ወቅት በአልሂደያ መስጊድ አካባቢ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ወታደሮቹ በርካታ ህፃናትን በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ዘግበዋል፡፡ አንድ ኢማምና ሌሎች በርካታ የእስላማዊ አማፂ ቡድኖች ሲገደሉ ሌሎች ሰባት ተጠቂዎችም በሞት አፋፋ ላይ ይገኛሉ፡፡ የማስታወቂያ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቶ ዘመድኩን ተክሉ ጉዳዩን አስመልክተው "የአምነስቲ ውንጀላ መሰረት የሌለውና ከዓማፂዎች ቡድን የተነዛ ኘሮፖጋንዳ ነው" በማለት ውንጀላውን አስተባብለዋል፡፡ "አምነስቲ ሁል ጊዜ ስለኢትዮጵያ ከሚያሰራጨው መሰረተ ቢስ መረጃ የተለየና የሆነ አውንታዊ ነገር ቢያሰራጭ ነበር ኢትዮጵያ የሚደንቃት" በተጨማሪ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ልዩ አማካሪ አቶ በረከት ስምኦን ቡድኑ በአገሪቷ ተወካይ የሌለው አካል ነው በማለት ዘገባውን አብጠልጥለዋል፡፡ "በመሰረቱ አምነስቲ በሶማልያ ምድር ተወካይ የለውም፡፡ ቡድኑ ኢትዮጵያ የሚወነጅለው መሰረተ ቢስ የሆነው ወሬና ከእውነት የራቀ መረጃ በማሰባሰብ ነው" በማለት ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡ አንዳንድ አክራሪ ያልሆኑት እስላማውያን መሪዎች በመስጊዱ በተፈጠረው ሁኔታና በሞቃዲሾ እየተባባሰ በመጣው ውጊያ ምክንያት በተመድ የተዘጋጀው ድርድር ለቀጣይ እንዲራዘም አድርገዋል፡፡ በዋና ከተማዋ ዳርቻ ረቡዕ ዕለት አራት ተጨማሪ አስክሬኖች መገኘታቸውን ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡ እስላማዊ ታጣቂዎቹ ትናንሽ ከተሞችን ከተቆጣጠሩ በኋላ ወደ 103 የሚጠጉ ነዋሪዎች ለሞት ተዳርገዋል፡፡ በተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ባለሥልጣን የሆኑት ጆን ሆልምስ እንዳሉት የጥቃቱ ሰለባ የሆነው ሲቪሉ ማህበረሰብ አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልገዋል፡፡ " ሚያዚያ 2ዐ በሞቃዲሾ በምትገኘው ሄሊዋ ቀጠና ሃይዳያ መስጊድ በደረሰ ጥቃት በርካታ ሴቶችና ህፃናት ለዕልቂት ተዳርገዋል" ሲሉ ታጣቂዎቹን አምርረው ወንጅለዋል፡፡ ባለሥልጣኑ በሰጡት መግለጫ መሠረት ታጣቂዎቹ በመኖሪያ አካባቢዎች ከባድ መሳሪያዎችን የሚጠቀሙ ሲሆን በዚህ ለዓመት በዘለቀ ጦርነት ወቅት ሰላም አስከባሪ ኃይሎችም በሞቃዲሾ የሲቪሉን ማህበረሰብ ደህንነት ለማስከበር መጠነኛ ጥረት አድርገዋል፡፡ ሲቪሉ የጥቃቱ ዋነኛ ሰለባ ሲሆን የሃገሪቱ ሰብአዊ መብት አስከባሪዎች እንደሚሉት 6"500 ሰዎች በዓመት የተገደሉ ሲሆን አንድ ሚሊየን ህዝብ ደግሞ ለስደት ተዳርጓል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |