Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ታታ የመኪና መገጣጠሚያ...
ታታ የመኪና መገጣጠሚያ... Print E-mail
Saturday, 26 April 2008
ታታ የመኪና መገጣጠሚያ ለመገንባት እየተዘጋጀ ነው

የሕንድ የመኪና አምራች የሆነው ታታ ኩባንያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሰባት አገራት ውስጥ የተለያዩ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎች የመገጣጠሚያ ፋብሪካዎችን ለመገንባት በመዘጋጀት ላይ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የኩባንያው የአፍሪካ ተወካይ ለኢንዲያን ታይምስ እንዳስታወቁት፣ በአሁኑ ጊዜ ትልቅ ኢንቨስትመንት ያላቸው በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ነው፡፡ እስካሁን ባለው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴያቸውም በደቡብ አፍሪካና በሌሎች የደቡባዊ አፍሪካ አገሮች ከ1.4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስት አድርገዋል፡፡

እስከ እ.ኤ.አ 2010 ባለው ጊዜ ውስጥ ደግሞ ኢትዮጵያን ጨምሮ 7 በሚሆኑ አገራት ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ በማድረግ የተሽከርካሪዎች መገጣጠሚያና ከዚሁ ሥራ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ኢንቨስትመንቶችን ውስጥ እንደሚገቡ ለዚህም የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች በማድረግ ላይ መሆናቸውን ተወካዩ አመልክተዋል፡፡

ታታ በአፍሪካ ውስጥ ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰቱን በእቅዱ መሰረት የሚተገብር ከሆነ በአፍሪካ ውስጥ ያለው ኢንቨስትመንት ከ2.5 ቢሊዮን ብር በላይ እንዲደርስ ያደርገዋል፡፡
 
< Prev   Next >