| ኮንፌዴሬሽኑ ባዘጋጀው የንግድ... |
|
|
| Saturday, 26 April 2008 | |
|
ኮንፌዴሬሽኑ ባዘጋጀው የንግድ ትርዒት ያቀደውን ያህል ተሳታፊ ሳያገኝ ቀረ
በዳዊት ታዬ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን የዘንድሮውን የሜይዴይ በዓል ምክንያት በማድረግ ባዘጋጀው ሜይዴይ ሚሊኒየም የንግድ ትርዒት የተጠበቀውን ያህል ተሳታፊ አለማግኘቱ ተገለፀ፡፡ በሚሊኒየም አዳራሽ የተከፈተውና ለሰባት ቀናት እንደሚቆይ በተገለፀው በዚህ የንግድ ትርዒት ላይ ይሳተፋሉ ተብለው የተጠበቁት 2ዐዐ የሚደርሱ የአገር ውስጥና የውጭ ኩባንያዎች ሲሆኑ ትርዒቱ ላይ የተሳተፉት ግን ከ2ዐ ኩባንያዎች በታች ናቸው፡፡ የተሳታፊ ኩባንያዎቹ ቁጥር አነስተኛ በሆነበት በዚህ የንግድ ትርዒት የጐብኝዎችም ቁጥር እጅግ አነስተኛ በመሆኑ ከትርዒቱ ይገኛል ተብሎ የተጠበቀውን ገቢ ማግኘት እንዳልተቻለ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የኮንፌዴሬሽኑ ኃላፊዎች እንደጠቆሙት ከሆነ የተጠበቀውን ያህል ተሳታፊ ያልተገኘው ትርዒቱን ማዘጋጀት በሚጀመርበት ጊዜ የሚሊኒየም አዳራሽ እንዳልተፈቀደ በመገለፁ ተሳታፊ ኩባንያዎችን የማፈላለጉ ሥራ ቆሞ ስለነበር ነው፡፡ የንግድ ትርዒቱ ይጀመራል ተብሎ ቀደም ብሎ ተይዞ የነበረው ቀን ሊደርስ ሦስት ሳምንታት ሲቀሩት አዳራሹ እንደተፈቀደ ስለተነገረ በሦስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ አሁን የተሳተፉትን ያህል ኩባንያዎች ብቻ ማግኘት መቻሉን እኒሁ ያነጋገርናቸው የኮንፌዴሬሽኑ ኃላፊ አስረድተዋል፡፡ ከየንግድ ትርዒቱ የሚገኘውን ገቢ በደብረዘይት እየተገነባ ላለው የአበራ ገሙ የሠራተኞች ማሰልጠኛ ማዕከል ለማዋል አስቦ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |