Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ከ141 ሚሊዮን ብር በላይ...
ከ141 ሚሊዮን ብር በላይ... Print E-mail
Saturday, 26 April 2008
ከ141 ሚሊዮን ብር በላይ የብድር አገልግሎት ተሰጠ

አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ141 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር መስጠቱን አስታወቀ፡፡

 

በተሰጠው የብድር አገልግሎት ከ22 ሺ በላይ ተበዳሪዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን፣ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት የተሰጠው የብድር አገልግሎት ለ13ሺ 785 ሰዎች ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ እንደነበር ከአሁኑ ጋር ሲነፃፀር በተበዳሪ ብዛት ከ62 በመቶ በላይ እድገት ማሳየቱን፣ ብድሩ ስለተሰጣቸው ዘርፎች መካከል በአልባሳት፣ በምግብ ዝግጅት፣ በብረታ ብረትና እንጨት ሥራ፣ ኮንስትራክሽን፣ ከተማ ግብርና፣ ማዘጋጃ ቤታዊ ሥራዎች፣ ቤት መስሪያና እድሳት እንደሚገኝባቸው አስታውቋል፡፡

(ኢዜአ)
*         *         *

ጤፍ በተመጣጣኝ ዋጋ እየተከፋፈለ ነው

የሉሜ አዳማ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን በሀገሪቱ የተከሰተውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት ከ7 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ከአባላቱ የገዛውን 15ሺ ኩንታል ጤፍ ለሸማቾች እያከፋፈለ ነው፡፡

ዩኒየኑ ከአባላቱ ገዝቶ ያጠራቀማቸውን የጤፍ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ በካሺና በብድር የሚያከፋፍለው በአዲስ አበባ፣ ሞጆ፣ በአዳማና አካባቢው ለሚገኙ ሸማቾች፣ የመንግሥት መስሪያ ቤት ሠራተኞችና ድርጅቶች ሲሆን፣ በተለይ ለመንግሥት መስሪያ ቤት ሠራተኞች በመሥሪያ ቤቱ ዋስትና በሦስት ወራት ተከፍሎ በሚያልቅ ክፍያ በብድር የሚሰጥ መሆኑን ገል"ል፡፡

(ዋኢማ)
*         *         *


የትምህርት ቢሮ ኃላፊው መኪና ተሸለሙ

የድሬዳዋ ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ በአስተዳደሩ መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎች የተዘጋጀላቸውን የመኪና ሽልማት ተረከቡ፡፡

ኃላፊው የተሸለሙት ለትምህርት ሥራ መሳካት ትጋት የተሞላበት አመራር በመስጠታቸውና በሥነ፣ ምግባራቸው አርዓያ ሆነው በመገኘታቸው፣ ለመምህራን ሥራ መሳካት ተገቢውን ድጋፍ ማድረጋቸው ለሽልማት ካበቋቸው ነጥቦች መካከል አንዱ መሆኑን ተወካዩ ገልፀዋል፡፡

(አዲስ ዘመን ሚያዚያ 15 ቀን 2000 ዓ.ም)

*         *         *

ከ15 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የተለያዩ ፕሮጀክቶች እየተካሄዱ ነው
በአገራቱ በተለያዩ ወረዳዎች ከ15 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተመድቦ የአቅም ግንባታ ፕሮጀክቶች እንደሚካሄድ የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚኒስቴሩ የገጠር አቅም ግንባታ ሰነድ እንደጠቆመው፣ ፕሮጀክቶቹ ተግባራዊ የሚሆኑት የአገሪቱን ልዩ ልዩ ስነ ምህዳር በሚወክሉ ወረዳዎች በሚቋቋሙ ሁለት ሺ 500 የገበሬዎች ማዕከላት ውስጥ መሆኑንና በአገሪቱ በሚገኙና 100 በተመረጡ ወረዳዎች ተግባራዊ እንደሚሆኑም አመልክቷል፡፡

(ኢዜአ)

*         *         *

የሙስና ወንጀል የፈፀሙ በገንዘብና በእስራት ተቀጡ

የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጀማሪ የባንክ ፀሐፊ ሆኖ ሲሰራ የነበረ ግለሰብና ግብር አበሮቹ ሀሰተኛ ሰነዶች በማዘጋጀት በፈፀሙት ወንጀል በ13 ዓመት፣ በሰባት ዓመት እስራትና በገንዘብ እንዲቀጡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ሚያዚያ 10 ቀን 2000 ዓ.ም በዋለው ችሎት ወስኖባቸዋል፡፡

(ኢዜአ)

 
< Prev   Next >