Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Saturday
Jul 05th
Home arrow Sections arrow በመስቀል አደባባይ ሊካሄድ የነበረው...
በመስቀል አደባባይ ሊካሄድ የነበረው... Print E-mail
Thursday, 10 January 2008

በመስቀል አደባባይ ሊካሄድ የነበረው መንፈሳዊ ዝግጅት ተከለከለ

እስራ አመቱን ሚሌኒየሙን ምክንያት በማድረግ በመስቀል አደባባይ ሊካሄድ የነበረው የመዝሙርና የትምህርት ፕሮግራም ተከለከለ፡፡ ማህበረ ቅዱሳንና ቤተክህንት በመተባበር ትናንት ሊያካሂዱት የነበረው መንፈሳዊ ዝግጅት የተከለከለው ከፖሊስ በመጣ ትዕዛዝ ነው፡፡

የእስራ አመቱ ኮሚቴ ሰብሳቢ ቄስ ዶክተር ሙሉጌታ ስዩም ለሪፖርተር  እንደገለፁት ዝግጅቱ በተጠናቀቀበት በመጨረሻ ሰዓት ላይ የእገዳ ትዕዛዝ መምጣቱ እንቆቅልሽ ሆኖባቸዋል፡፡

ዝግጅቱን ለማካሄድ ኮሚቴው ዝርዝር ጉዳዩን በማሳወቅ ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ፈቃድ ማግኘቱን የገለፁት ቄስ ዶክተር ሙሉጌታ ለዝግጅቱ ከፍተኛ ወጪ ከወጣና ህዝቡ ፕሮግራሙን እንዲከታተል በቴሌቪዥን ማስታወቂያ ከተላላፈ በኋላ በፖሊስ ትዕዛዝ ፕሮግራሙ እንዲሰረዝ መደረጉ ተገቢ አለመሆኑን አመልከተዋል፡፡

ቄስ ዶክተር ሙሉጌታ እንዳሉት ትናንት ከ8፡00 ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ሊካሄድ ታስቦ ለነበረው ዝግጅት በመቶ ሺ የሚቆጠር ገንዘብ ወጥቷል፡፡ ለመድረክ ግንባታውም  ብር በላይ ወጥቷል፡፡

አሰባሳቢ ኮሚቴው ፕሮግራሙን እንዲሰርዝ የሚገልጽ ደብዳቤ እስከ ትናንት ድረስ አልደረሰውም ያሉት የኮሚቴው ሰብሳቢ በመጨረሻ ሰዓት ላይ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊሶች ዝግጅቱ ወደሚካሄድበት ቦታ በመሄድ የመንፈሳዊ ዝግጅቱ በጃን ሜዳ እንዲካሄድ ማዘዛቸው እንዳስገረማቸው 

አያይዘውም  ፕሮግራሙን የምናካሂደው  ነን፡፡ መቀየር ካስፈለገም ተስማምተንና ተነጋግረን መሆን አለበት፡፡ ልናዘጋጀው ባላሰብንበት ቦታስ ፕሮግራሙን እንዴት ልናካሂድ እንችላለን?.. ብለዋል፡፡

ጉዳዩን አስመልክተን ያነጋገርናቸው የፌደራል ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ደምሳሽ በመስቀል አደባባይ ሊካሄድ የነበረው መንፈሳዊ ዝግጅት የተከለከለው በአዲስ  ከተማ መስተዳድር በተፃፈ ደብዳቤ መሰረት መሆኑን ገልፀውልናል፡፡

እንደ ኮማንደር ገለፃ በመስቀል አደባባይ ሊካሄድ የነበረው ዝግጅት ወደ ጃን ሜዳ እንዲዛወር ተደረገ እንጂ አልታገደም፡፡ ዝግጅቱ በጃን ሜዳ እንዲካሄድ የተወሰነውም ቀደም ሲል በመስቀል አደባባይ እንዲካሄድ የተያዘ ሌላ ዝግጅት በመኖሩና የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይከሰት በማሰብ መሆኑን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡

መንፈሳዊ ፕሮግራሙ በመስቀል አደባባይ እንዳይካሄድ የሚገልጽ ደብዳቤ በግልባጭ ለፌደራል ፖሊስ እንደተላከ የገለፁት ኮማንደር ደምሳሽ በመስተዳድሩ ውሳኔ የፕሮግራሙ አዘጋጆች መስማማታቸውን ተናግረዋል፡፡

በኃይሌ ሙሉ

 
< Prev