| ከ600 በላይ ተፈናቃዮች... |
|
|
| Saturday, 26 April 2008 | |
|
ከ600 በላይ ተፈናቃዮች ለችግር ተጋለጡ
ከኤርትራ ተፈናቅለው በአድዋ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ከ600 በላይ የሚሆኑ ተፈናቃዮች የመቋቋሚያ ገንዘብ ስላልተሰጣቸው ለከፋ ችግር መዳረጋቸውን ምንጮች አስታወቁ፡፡ የትግራይ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ቢሮ የእርዳታ ፕሮግራም ኃላፊ ደግሞ የመቋቋሚያው ገንዘብ እንደደረሰ ወዲያውኑ እንደሚታደላቸው ገልፀዋል፡፡
ምንጮች እንዳመለከቱት እስካሁን ባለው አሠራርና ደንብ ተፈናቃዮቹ መጠለያ ጣቢያ ከገቡ ከአንድ ሳምንት በኋላ ለመቋቋሚያ የሚሆን በነፍስ ወከፍ 3ሺህ ብር እየተሰጣቸው ወደየዘመዶቻቸው እንዲቀላቀሉ ይደረግ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን ያሉት ተፈናቃዮች መጠለያ ከገቡ ሁለት ወር እንደሞላቸው፣ ቁርስ ምሳና ራት ከሚቀርብላቸው በስተቀር እስካሁን መቋቋሚያ እንዳልተሰጣቸው አስረድተዋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |