Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home
በሐረር ከተማ የመሬት የሊዝ እዳ... Print E-mail
Wednesday, 30 April 2008
በሐረር ከተማ የመሬት የሊዝ እዳ አከፋፈል ውዝግብ አስነሳ

በተሾመ ንቁ

በሐረር ከተማ የተሰማሩ ኢንቨስተሮች ከአስር አመት በላይ የተጠራቀመ የመሬት የሊዝ እዳ ክፍያ እንድንከፈል ተጠይቀናል ሲሉ አማረሩ፡፡ የከተማው መስተዳድር የክፍያው ሁኔታ ፍትሐዊ መሆኑን በመግለፅ አቤቱታውን አስተባበለ፡፡

በሐረር ከተማ በኢንቨስትመንት መስክ የተሰማሩ ባለሀብቶች፤ ከ1986 ዓ.ም. ጀምሮ ታሳቢ የሚደረግ የሊዝ እዳ ክፍያ መጠየቃቸውን በመግለፅ፤ የእዳ እሳቤውን ተቃወሙ፡፡ ባለሀብቶቹ አንደኛ ደረጃ በካሬ ሜትር 650 ብር ሁለተኛ ደረጃ 550 ብር፣ ሦስተኛ ደረጃ 5ዐዐ ብር ታሳቢ የሚደረግ ክፍያ መጠየቃቸውን አስታውቀዋል፡፡ በዚህም የመሬት ርክክብ ሲደረግ የክፍያ መጠኑ ያልተወሰነ መሆኑን በመጥቀስ ፍትሐዊ ያልሆነ ከፍተኛ ክፍያ መጠየቃቸውን ገልፀዋል፡፡

ባለሀብቶቹ ከከተማው አስተዳደር ጋር የኢንቨስትመንት ውል ሲገቡ የክፍያ መጠን ካሬ ሜትር ተተምኖ ያልተገለፀላቸው መሆኑን በመጥቀስ፤ አስተዳደሩ ያስታወቃቸው የሊዝ ክፍያ መጠን ድንገተኛ እንደሆነባቸው ገልፀዋል፡፡ በዚህም "የከተማው አስተዳደር ከውል ውጪ ከፍተኛ ክፍያ ጠይቆናል" ሲሉ አማርረዋል፡፡

ባለሀብቶቹ የከተማው አስተዳደር የክፍያ ሁኔታውን ለረዥም ጊዜ ሳያሳውቃቸው ቆይቶ፤ በያዝነው ወር ድንገተኛ የክፍያ ውዝፍ መግለፁን ተቃውመዋል፡፡ በተሰጣቸው መሬት ላይ ግንባታ ማከናወናቸውን በመጥቀስ፤ በቅርቡ የተገለፀላቸውን የሊዝ እዳ ለማስከፈል አስተዳደሩ በመሬቱ ላይ የገነቡትን ግንባታ በመያዣነት እንደያዘባቸው ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም የከተማው አስተዳደር ከአስር ዓመት በላይ የተጠራቀመውን እዳ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲከፍሉ ማስገደዱን ጠቅሰዋል፡፡ እንደ ባለሀብቶቹ ገለፅ አንድ ባለሀብት በሊዙ እሳቤው ከአንድ እስከ አራት ሚሊዮን ብር ለመክፈል የሚገደድ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ባለሀብቶቹ የሊዝ ክፍያውን በመቃወም የፊርማ ማሰባሰብ ሥራ መጀመራቸውን ገልፀዋል፡፡ የተቃውሞ ፊርማውንም ለሚመለከታቸው የከተማው፣ የክልሉና የፌደራል መንግሥት አመራሮች እንደሚያስታውቁ ገልፀዋል፡፡

የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ አሪፍ መሀመድ በበኩላቸው የክልሉ ምክር ቤት እስከ 1999 ዓ.ም. ድረስ የሊዝ ደንብ ያልነበረው መሆኑን ጠቅሰው፤ "የሊዝ ደንቡ ትግበራ መዘግየቱ የክልሉ አስተዳደር ችግር ነበር" ሲሉ ገልፀዋል፡፡ አቶ አሪፍ የሊዝ ደንቡ ዘግይቶ ቢፀድቅም ኢንቨስተሮች እዳቸውን መክፈል እንደሚገባቸው ገልፀዋል፡፡

የክፍያው ሁኔታ በተለያየ የከተማው የይዞታ ደረጃ በካሬ ሜትር ከ150 እስከ 650 ብር መሆኑን የገለፁት አቶ አሪፍ፣ ባለሀብቶች የሊዝ አዋጅ በፌዴራል ደረጃ ከወጣበት ከ1986 ዓ.ም. ጀምሮ ያለባቸውን እዳ መክፈል እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡ የአከፋፈሉ ሁኔታ ግን በአንድ ጊዜ አለመሆኑን ሥራ አስኪያጁ ገልፀው፤ የክፍያ ጊዜውን በተመለከተ መመሪያ የማውጣት ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አቶ አሪፍ በከተማው በኢንቨስትመንት የተሰማሩ ባለሀብቶች መሬት ሲረከቡ በሊዝ ደንብ ክፍያ ለመፈፀም በገቡት ውል መሠረት ክፍያ እንዲፈፅሙ መደረጉ አግባብ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ "ባለሀብቶቹ አሁን የተጠየቁት ውዝፍ እዳ እንዲከፍሉ ሳይሆን፤ የ2ዐ በመቶ የቅድሚያ ክፍያ ነው" ሲሉ አስተባብለዋል፡፡ የከተማው ባለሀብቶች በሊዝ ህጉ መሠረት የሊዝ ውለታቸውን እንዲፈርሙ፣ አዲሱን የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲወስዱ ስራ አስኪያጁ አሳስበዋል፡፡

ሥራ አስኪያጁ የከተማው አስተዳደር ባለሀብቶቹ የሀያ በመቶው የቅድሚያ ክፍያ ውጭ ያለውን የውዝፍ ሂሳብ አከፋፈል በተመለከተ ፍትሀዊ የክፍያ ጊዜ እያመቻቸ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በዚህም የክፍያ ጊዜው እስከ ሀያ አመት ሊደርስ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

በቅድሚያ ክፍያ አከፋፈል መሠረት ሁለት መቶ ካሬ ሜትር የያዘ ባለሀብት ከአርባ እስከ ሀምሳ ሺህ ብር ብቻ የሚከፍል መሆኑን ጠቅሰው፤ "ክፍያው የባለሀብቱን የኢንቨስትመንት ሥራ የሚያደናቅፍ አይደለም" ብለዋል፡፡

ከዚህም ባሻገር በሆቴል፣ በቱሪዝምና በህክምና የተሰማሩ ኢንቨስተሮች ከ50 እስከ 60 በመቶ ቅናሽ እንደሚደረግላቸው አቶ አሪፍ ገልፀዋል፡፡

ስራ አስኪያጁ በከተማው ከተሰማሩት ኢንቨስትሮች አብዛኛው ከ1995 ዓ.ም. ወዲህ ውል የገቡ በመሆናቸው ከፍተኛ ውዝፍ እዳ በባለሀብቱ ላይ እንደማይኖር ገልፀዋል፡፡ ከባለሀብቶች ጋር ውይይት መጀመራቸውንና ከሀያ በላይ ኢንቨስተሮች ክፍያ መጀመራቸውን አቶ አሪፍ ገልፀዋል፡፡
 
< Prev   Next >
Headline
  • Pause
  • Previous
  • Next
1/10
Image የመናፈሻው ባለቤት ማነው?
በብሔራዊ ቤተመንግስት ምስራቅና፣ ከአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ምዕራብ እያዋሰነ እስከ ታላቁ ቤተ መንግስት የሚደርሰውና ለሕዝብ ክፍት ሆኖ የኖረው መናፈሻ   ማናቸውም ዜጋ እንዳይገለገልበት ዝግ ሆኖ ቆይቷል፡፡

Read more...
 
 
Politics
ከእኛ በላይ ስለኛ ማንም ሊናገር አይችልም!
እንደሚታወቀው ሁሉ አምባገነኑ የደርግ መንግስት በመጣል ለሰላም፣ ለፍትህ፣ ለዴሞክራሲና ለብሄር ብሄረሰቦች መብት መከበር የተካሄደው የትጥቅ ትግል ለድል የበቃል በመላው ህዝባችን ተሳትፎና በጠራ መስመር የሚመራ አላማ መሆኑ ፀሐይ የሞቀው አገር ያወቀው ሃቅ ነው፡፡ የታገልንለት ህዝባዊ መሰረት ያለው አላማም የታጋዩን የመላው ኅብረተሰብ የአላማ ጽናትና አይበገሬነት በተግባር ያስመሰከረ፣ ለአረመኔው የደርግ ስርዓትና ጋሻጃግሬዎቹ እንደ እግር እሳት እያንገበገበ ህዝባዊ ቀንዲልን ያወገገ ታሪካዊ ፍጻሜ እንደሆነም ሁሉም የሚመሰክርለት ጉዳይ መሆኑ አንድና ሁለት የለውም፡፡

Briefs
በእንስሳት ማድለብ ሥራ 1ዐ...

በእንስሳት ማድለብ ሥራ 1ዐ ሚሊዮን ብር ትርፍ ተገኘ

በትግራይ ማዕከላዊ ዞን ስምንት ወረዳዎች በእንስሳት ማድለብ ሥራ የተሰማሩ አርሶ አደሮች አስር ሚሊዮን ብር ትርፍ ማግኘታቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

 

 
Business & Economy
Image የሆላንድ ካርን ድርሻ ለመግዛት...
የሆላንድ ካርን ድርሻ ለመግዛት የቻይና ኩባንያ እየተደራደረ ነው

ከ370 በላይ የሚሆኑ አባይ አውቶሞቢሎች ተሸጡ

በዳዊት ታዬ

Shemach
ለተወደደው ኑሮ መፍትሄ ምን?
በናታን ዳዊት

ወቅታዊው የምግብ እህል እጥረትና የኑሮ ውድነት አለም አቀፋዊ ይዘት እንዳለው ሰምተናል፡፡ በምግብ እጥረትና በኑሮ ውድነት ዙሪያ የሚሰራጩ ዓለም አቀፍ መረጃዎችም ይህንኑ ይጠቁማል፡፡ ከምግብ እጥረት ጋር ተያይዞ የተፈጠረው የዋጋ ንረት እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገራትን በጣም እየጎዳ መሆኑን እያንዳንዳችን ማስረጃ ልንሆን እንችላለን፡፡

 
Interview
Image "ካለን ውስን የሰው ኃይል፣ ፋይናንስና...
"ካለን ውስን የሰው ኃይል፣ ፋይናንስና ጊዜ አንጻር ትልቅ ሥራ አከናውነናል"
አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ
የአዲስ አበባ ከተማ ሚሌኒየም ጽ/ቤት ምክትል ዳይሬክተር

አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ የአዲስ አበባ ከተማ ሚሌኒየም ጽ/ቤት ምክትል ዳይሬክተር ናቸው፡፡ ጽ/ቤቱ የተቋቋመበትን ተግባር ለማጠናቀቅ ሁለት ወራት ብቻ በቀ ረበት በዚህ ወቅት ከጽ/ቤቱ የሥራ ክንውን ጋር በተያያዘ ፍሬው አበበ አነጋግሯቸዋል፡፡

Fermata
አማን በአማን
ከከባድ እንቅልፍ ሰውን ለመቀስቀስ
ከጥንታዊ ክብሩ ዳግም ለመመለስ
ቢነሣ ሶክራቲስ ቢወለድ ኢየሱስ፤
እነ ስም አይጠሩ
ሳይፈሩ ሳያፍሩ
 
Kibur Minister
ክቡር ሚኒስትር

(ሚኒስትር መሥሪያ ቤት በኃላፊነት እንዲያሳካ የተሰጠውን ፕሮጀክት የሚገመግም ከአገር ውስጥና ከውጭ የተውጣጣ የኤክስፐርቶች ቡድን ክቡር ሚኒስትሩ መሥሪያ ቤት ድረስ መጥቷል፡፡ እሳቸውም ከባለሙያዎቻቸው ጋር ናቸው፤ ስብሰባው ተጀምሯል)

 

Life & Art
Image ጀግኖቻችንን ለማክበር

በሔኖክ ያሬድ

በኢትዮጵያ ከስም የዋለ ተግባር ያከናወኑ ምርጥ ሰዎች መኖራቸው፣ ማለፋቸው የተመዘገበ ነው፡፡ በጀግንነትም ይጠቀሳሉ፡፡ ከሰብዓዊ ጥናት በተለይም በኪነ ጥበባት ዘርፍ አንቱ የተባሉ ኢትዮጵያውያን የመኖራቸውን ያህል በጦር ውሎ የተወደሱት ጀግኖች ያህል ክብር የተሰጣቸው ምን ያህል እንደሆኑ እምብዛም አይታወቅም፡፡

 

 
Social
Image "ጃንጥላና ሹራብ ሰሪ ክረምት ይወዳል"

በምህረት አስቻለው

መርካቶ ራጉኤል ቤተክርስቲያን አቅራቢያ ከሚገኝ አንድ የልብስ ሱቅ ደጃፍ ላይ የተበላሹ ጃንጥላዎችን ሲጠግኑ አገኘኋቸው፡፡ አቶ አራርሳ ሔርጶ ለሃያ ዓመታት በእሳት አደጋ መከላከያ ብርጌድ ውስጥ በጥበቃነት፣ በአደጋ ተከላካይነት እንደሰሩ ይናገራሉ፡፡  አሁንም በሰራተኛ ልሸፍት ኃላፊነት እዚያው እሳት አደጋ ውስጥ በመስራት ላይ ናቸው፡፡

 

Science & Technology
Image የምግብና የነዳጅ ፍላጎት መጨመር...

የምግብና የነዳጅ ፍላጎት መጨመር ደንን እያወደመ ነው

የምግብና የነዳጅ ሰብሎችን ማምረት እንዲሁም የእንጨት ፍላጎት መጨመር የደን መጥፋትን ያስከትላል ሲል የ"ዘ ራይትስ ኤንድ ሪሶርስስ ኢንሽየቲቭ" ሪፖርት አስጠንቅቋል፡፡

 

 
Diaspora
Image በትውልድ አገራቸው በልማት...
በትውልድ አገራቸው በልማት ውጤታማ የሆኑትን ማስተዋወቅ ይጀመራል

በምሕረት ሞገስ

ነዋሪነታቸው በኔዘርላንድስ ሆኖ በትውልድ አገራቸው አዋጭና እድገትን መሰረት ያደረገ ሥራ የሚሰሩ ዲያስፖራዎችን የማስተዋወቅ ሥራ ሊጀምሩ መሆናቸውን ሚ/ር ኢዋን ሶንደር ተቀማጭነቱን በኔዘርላንድስ ያደረገው ኢንተርናሽናል ኢንተርፕሩነርሽፕ (ኢንትኤንት) አማካሪ ገልፀዋል፡፡  

Youth
Image የወጣቶቹ ፍሬ

በጋዜጣው ሪፖርተር

የተለያዩ የፈጠራ ውጤቶችን እንዲመጡ ማበረታቻዎች መኖር አለባቸው፡፡ አገሪቱ የፈጠራ ሥራን ካበረታታችና ከደገፈች አገሪቱን የሚጠቅሙ በርካታ የፈጠራ ባለሙያዎች ይመጣሉ፡፡ ለፈጠራ ባለቤትነት ወይም እውቅና የማይሰጥባቸው ዘርፎችም ብልሃት ሊፈለግላቸው ይገባል፡፡ በኮምፕዩተር ዘርፍ እውቅና የሚሰጠው ማን ነው? ሣይንስና ቴክኖሎጂ አቅምና ብቃቱ የለውም ወይ ለሚሉት ጥያቄዎች ምላሽ ያስፈልጋቸዋል፡፡ በፈጠራ ባለሙያዎች ዘንድ ሌላው የሚነሳው ለፈጠራ ባለቤትነት ክፍያ መፈፀሙ ተገቢ አለመሆኑን ነው፡፡ ይህንን ክፍያ መክፈል ባለመቻል ፈጣሪዎችና ፈጠራቸው ተዳፍነው ይቀራሉ የሚል ቅሬታ አለ፡፡

 

 
Opinion
ገልጦ የሚያይ 'አምላክ'ማ አይከለክልም

በሪሁን ተሻለ

የአገራችንን የሥራ ፈላጊዎች፣ ሥራ አጦችን፣ ሥራ ፈላጊዎችን፣ ሥራ ላይ ሆነው፣ ሥራ እያላቸው የተሻለ ሥራ የሚያፈላልጉትን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በላይ በሚገኝ ከፍተኛ ሥራ የፖለቲካ ሥልጣን ላይ ያሉትን ጭምር ሲበዛ ሊያሰገርም ሊያስደንቅ የሚችል አንድ "የሥራ ማስታወቂያ" ያየሁት በአሜሪካው የዋይት ሀውስ ዌብ ሳይት (ድረ ገጽ) ላይ ነው፡፡ ከ115 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የሚደረገው የአሜሪካ የፕሬዚዳንትነት ምርጫ ከስልጣን የሚሰናበተውና የሚተካውን ግለሰብ/ ግለሰቦች ብቻ ሳይሆን ፓርቲውንም ጭምር አብሮን ከእኛ ጋር የሚያውቀው የቡህ ቸኒ አስተዳደር ይህንን የሥራ ማስታወቂያ ወይም የከፍተኛ ሹመት ማመልከቻ ጥሪ በዋይት ሀውስ ድረ ገጽ ላይ የለጠፈው ሥልጣን ከያዘበት ከስምንት ዓመት ወዲህ ጀምሮ ነው፡፡ ዛሬም አሁንም አለ፡፡

 

Letter to Reporter
ዱላ ቀረሽ አስተያየት
የሀገር መሪ የቃላት አጠቃቀሙ፣ የፊቱ ሁኔታና የድምፅ አወጣጡ ሁሉ ትርጉም እንደሚኖረው በሐምሌ 6/2000 ሪፖርተር ጋዜጣ በእኔ የምለው ጉድ ተጠቅሷል፡፡ የሚያስቆጣና የሚያበሳጭ ጉዳይ ቢያጋጥመው እንኳ በተረጋጋ መንፈስ የመናገር ብቃት ሊኖረው ይገባል፡፡ አለበለዚያ ንዴትና ብስጭት በተቀላቀለበት መልክ በቁጣ ለመመለስ መሞከር እርምጃ ለመውሰድ የተዘጋጀ ያስመሰልዋል፡፡ ማስፈራራትም ይመስላል፡፡ እነዚህ ሁሉ ተደማምረው መተማመንን ያመነምናሉ፡፡ ባለሙያዎቹም እየራቁ ይሄዳሉ፡፡

 
Women
Image ፣የዓመቱ ምርጥ የፈጠራ ሴት፣

በምህረት አስቻለው

"መንገድ ላይም ይሁን በማንኛውም ቦታ የሰዎችን አለባበስ በትኩረት እመለከታለሁ፡፡ እዚህ ጋር እንዲህ፣ ቀለሙ የዚህ ዓይነት ቢሆን ብዬ አስባለሁ፡፡ የማውቀው ሰው ከሆነ ደግሞ አስተያየት እሰጣለሁ፡፡ ማንኛውም ሰው በሄደበት ሁሉ ከሙያው ጋር የሚገናኙ ነገሮችን ማስተዋሉ አይቀርም፡፡ የምገዛቸው ልብሶችንም ቢሆን በምፈልገው መንገድ አስተካክላቸዋለሁ" ትላለች ፣የዓመቱ ምርጥ የፈጠራ ሴት፣ ተብላ ሽልማት ማግኘት የቻለችው የልብስ ዲዛይነር፡፡

 

Temuaget
ዋናው ተቆጣጣሪ!
ከጎይቶም አዳነ

ዋናው ኦዲተር የሁሉም፣ የሦስቱም የኢትዮጵያ ሕገመንግስቶች ጉዳይ ሆኖ ኖሯል፡፡ በሌላ አነጋገር ዋናው ኦዲተር ሕገመንግስታዊ የሥልጣን አካል ስለመሆኑ በተለይም በሦስቱ ሕገመንግስቶች የተፈፃሚነት ዘመን ውስጥ እውነት ነበር፡፡

 
Law
Image ለኦዲዮ ቪዥዋል ሥራ ኘሮዲውሰሩ ማን ነው?
በሰለሞን ጐሹ

ሰኔ 22 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በወጣው የሪፖርተር ጋዜጣ ‘ኪንና ባህል’ ዓምድ ላይ (“ለአባቷ” ፊልም ብሩክ ፊልሞችንና ናቭኮም ኢነርጂን እያወዛገበ ነው) በሚል ርዕስ ማስነበባችን ይታወሳል፡፡ በወቅቱ የናቭኮም ኢነርጂ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር አድማሱ ገብሬ ምላሽ ለመስጠት ባይችሉም ከፅሁፉ መውጣት በኋላ ብሩክ ፊልሞች አሳስቷል ባሏቸው ነጥቦች ላይ ከአሉላ ኤ.አንደሚካኤል ጋር በመሆን ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

Zennk
የፍቅር አይነቶች

ግሪኮች ለፍቅር ሦስት ዓይነት ስያሜ ሲሰጡት ሮማውያንም እንዲሁ በሦስት ይከፍሉታል፡፡ በግሪክ የመጀመሪያው ዓይነት ፍቅር "ኤሮስ" የሚሉት ሲሆን ይኸውም ከፍትወት ፍቅር ጋር በቀጥታ የተገናኘ ነው፡፡ ሁለተኛው ዓይነት ፍቅር ደግሞ "ፊሎ" ይሉታል፡፡ ይኸ ደግሞ እንደ ፊሎዞፊ የራሱ የሆነ ሥነ ቃል ሲሆን ይኸውም የሰው ልጅ ፍቅር ወይም የጥበብ ፍቅር ተደርጐ ይወሰዳል፡፡ ሦስተኛው ዓይነት ፍቅር "አጋፔ" የሚሉት ነው፡፡ ይኸ ዓይነቱ ፍቅር ለአምላክ የሚኖርን ፍቅር በቀጥታ የሚመለከት ነው፡፡

 

 
Delalaw
ቁዘማ
እኛ ለማዘንም ሆነ ለመደሰት ጊዜ አይፈጅብንም፡፡ ወደ  ይሁን ወደቀኝ  ቢሉ ደስታና ሐዘን፣ ረሃብና ጥጋብ ጎን ለጎን ያገኟቸዋል፡፡ ድሎትና ብሶት፣ ጥፋትና ልማት ጎን ለጎን፡፡ ሳይራራቁ፣ ሳይለያዩ ቅርብ ለቅርብ ናቸው፡፡ ለዚህ ዋቢ መጥራት አያስፈልግም፡፡

Teles
በግልፅነት የተገኘ ለውጥ

በጋዜጣው ሪፖርተር

ሸመቱና ጓደኛዋ ስራነሽ ለማንም የማይነግሩትና ለሁለት ዓመታት በጋራ የያዙት ሚስጢር አላቸው፡፡ ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በደማቸው መኖሩንና የፀረ ኤች.አይ.ቪ መድኃኒት መውሰድ ከጀመሩ ሁለት ዓመታት ማሳለፋቸውን ለማንም ለመንገር አይደፍሩም፡፡

 

 
Sport
Image "ከፖሊሲው በተቃራኒ ፌዴሬሽኖችን...

"ከፖሊሲው በተቃራኒ ፌዴሬሽኖችን ወደ አንድ ዕዝ ለመመለስ ይመስላል"
አቶ ተስፋዬ ሽፈራው የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት


የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ከአትሌቲክስና ቦክስ ፌዴሬሽኖች ቀጥሎ በኢንተርናሽናል የውድድር መድረክ ኢትዮጵያን የሜዳሊያ ባለቤት አድርጓል፡፡ ይሁንና ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በአሁኑ ሰዓት በምንም መመዘኛ እውቅና ለሌለው ማርሻል አርት ለሚባል ፌዴሬሽን ሙሉ ጽ/ቤቱ እንደተሰጠበትና ያለ ቢሮ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ተስፋዬ ሽፈራው ይገልፃሉ፡፡ አነጋግረናቸዋል፡፡

 

Taxi
ተሞክሯችን
ኑሮ የጎነተላቸው ተሳፋሪዎች ከጀርባዬ ሆነው ሲያወሩ ይሰማኛል፡፡ የገቢ ምንጭን ማብዛት ባለመቻላቸው ተቸግረዋል፡፡ ለዚህ ችግራቸው አማራጭ ያደረጉት በየዕለቱ ፍላጎታቸውን መቀነስ ነው፡፡ ሻይ ቡና፣ መክሰስ ብሎ ነገር እየቀረ ነው፡፡ ቁርስም ቢሆን ማስመሰል እንጂ መብላት አይደለም፡፡ የኑሮ ውድነቱ በፍጥነት እየቀጠለ ሲሄድ የዳቦው መጠንም በዚያው ፍጥነት ያፈገፍጋል፡፡ እያነሰ፣ እያነሰ ነጥብ ለሆን ነው፡፡ የአንዳንዶቻችን ቁርስ በየቀኑ እያነሰ፣ እያነሰ የሚሄደውን ዳቦ በሻይ ማለት ነው፡፡ ይህም ቢሆን መካከለኛ ገቢ ባላቸው ዘንድ ነው፡፡

 
World
እስራኤል በኢራን ላይ እርምጃ...

እስራኤል በኢራን ላይ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቷን ገለፀለች
በጋዜጣው ሪፖርተር

እስራኤል ጥቃት ይደርስብኛል የሚል ስጋት ካደረባት በኢራን ላይ እርምጃ ለመውሰድ የተዘጋጀች መሆኗን መከላከያ ሚኒስትሩ ገለፁ፡፡

 

 
  • Do You Know ?
    How To Increase Font Size
    You can increase the font size of the website if it appears smaller than normal. Just click the member area link at the top right of this page and the page will slide down. At the top left corner of the page, look for three small buttons. To increase font size, click the button with "+" sign and "-" sign to decrease font size.
  • Tips !
    Tips for Amharic Version
    • Use Internet Explorer version 6 or better
    • Adjust your screen resolution to 1024 X 768
    • Use the font resizer to increase font size if needed
    • Though it is not strictly needed having power geez unicode font could enhance the font rendering in your browser
 

Important Links

Visit Ethiopian Yellow PagesA forum on Dialogue, Democracy & Development