Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Thursday
Nov 20th
Home
You are not authorised to view this resource.
You need to login.
Headline
  • Pause
  • Previous
  • Next
1/10
Image ኢጋድ ለጸጥታው ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ
በኃይሌ ሙሉ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት የሶማሊያ ፌዴራላዊ የሽግግር መንግሥት ተቋማትን ከመፈራረስ ማዳን የሚያስችል ኀላፊነቱን እንዲወጣ ከዚህም በመነጨ ሊከተል የሚችለውን የባሰ ሰብዓዊ ቀውስ እንዲታደግ የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ፡፡ በሶማሊያ መፍትሄ ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ችግር ለሚፈጥሩ አመራሮች የኢጋድ የመንግሥታትና የአገር መሪዎች የሚሰጡትን ፖለቲካዊ እውቅናና ድጋፍም መልሰው እንዲያነሱ የሚኒስትሮች ምክር ቤቱ ጠይቋል፡፡

Read more...
 
Zena
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስምንት...
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስምንት ምክትል ፕሬዚዳንቶችን ሹመት ይፋ አደረገ

በፍሬው አበበ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባካሄደው መሠረታዊ የአሠራር ሥርዓት ጥናት (ቢፒአር) መሠረት ስምንት ያህል ምክትል ፕሬዚዳንቶችን ከኅዳር 8 ቀን 2001 ዓ.ም. ጀምሮ ሾመ፡፡

Editorial
Image ሁሉም ለአገሩ መስዋዕትነት ይክፈል!
በአንድ ዘርፍ፣ በአንድ ግለሰብ፣ በተወሰነ ቡድንና በተወሰነ አጋጣሚ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ብቻ አገር አይቀናም፣ ሕዝብ አይበለፅግም፣ ነፃነትና ሉአላዊነት አይረጋገጥም፡፡ ሁሉም በየሙያውና በየዘርፉ የድርሻውን ሲጫወት እንጂ፡፡

 
Politics
Image "ሶማሊያውያንን ልንረዳቸው እንችላለን...
"ሶማሊያውያንን ልንረዳቸው እንችላለን እንጂ ኃላፊነታቸውን መሸከም አንችልም"
ውጭ ጉዳይ ሚ/ር አቶ ሥዩም መስፍን

በየማነ ናግሽ

አቶ ሥዩም መስፍን የሶማሊያ ወቅታዊ ጉዳይ አስመልክተው ለኢጋድ ባቀረቡት ሪፖርት፣ የሶማሊያ ጉዳይ ኃላፊነት በዋናነት የራሳቸው የሶማሊያውያን እንደሆነ በመጥቀስ፣ በአገሪቱ ያሉት የኢትዮጵያ ወታደሮችና የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ኃይሎች (አሚሶን) ከዚህ በላይ የሚከፍሉት መስዋዕት እንደማይኖር አሳወቁ፡፡ ኢትዮጵያም ሶማሊያን ከመርዳት ውጭ የሶማሊያውያንን ኃላፊነት ራሳቸው መሸከም እንደሚገባቸው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

Briefs
አርብቶ አደሩ ፕሮጀክቱን አጠናቀቀ

በአገሪቱ ባለፉት አምስት ዓመታት በ60 ሚሊዮን ዶላር የተካሄደው የመጀመሪያው ምዕራፍ የአርብቶ አደሩ ማህበረሰብ የልማት ፕሮጀክት ተጠናቀቀ፡፡

 

 
Business & Economy
Image የመንግሥት የፋይናንስ ተቋማት...
የመንግሥት የፋይናንስ ተቋማት የደመወዝ ጭማሪና የቦነስ ጥያቄ

በዳዊት ታዬ

የመንግሥት የፋይናንስ ተቋማት ሊደረግላቸው ይገባ የነበረ የደመወዝ ጭማሪና ቦነስ የጊዜ ገደብ እየተጠናቀቀ በመሆኑ በህብረት ስምምነታቸው መሠረት ተፈፃሚ እንዲሆን ጥያቄ አቀረቡ፡፡ ጉዳያቸው በአገር አቀፉ የባንክና መድን ኢንዱስትሪ ሠራተኞች ፌዴሬሽን በኩል ክትትል እየተደረገበት ነው፡፡

Shemach
እውነቱ ይነገረን

በናታን ዳዊት

በአገራችን ትላልቅ አገልግሎት ሰጪዎች ከሚባሉት መንግሥታዊ ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን፣ የአዲስ አበባና የክልል የውሃና ፍሳሽ አገልግሎት መሥሪያ ቤቶች እና የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ተጠቃሽ ናቸው፡፡

 

 
Interview
"ኢትዮጵያ ከኦርጋኒክ ግብርና...

"ኢትዮጵያ ከኦርጋኒክ ግብርና የምታገኘው ምንዛሪ በ10 እና በ20 በመቶ ማደግ አለበት"
አቶ አዲሱ አለማየሁ

አቶ አዲስ አለማየሁ የኢትዮጵያን አሶሴሽን ኦፍ ኦርጋኒክ አግሪካልቸር የቦርድ አባልና ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ ከማህበሩ መስራቾች መካከልም አንዱ ናቸው፡፡ በማህበራቸው የሥራ እንቅስቃሴ ዙሪያ ዳዊት ታዬ አነጋግሯቸዋል፡፡

 

Fermata
ከሳሽና ተከሳሽ
ደቢሮ አሰኔ፣ አሊ ኢብራሂምን እኔና አንተ እጮኛሞች ነንና በመንገድ ስሄድ እንዲያው ምንም ሳልልህ ደብድበኸኛልና እሞታለሁ ብላ ከሳ አምጥታው፣

 
Kibur Minister
ክቡር ሚኒስትር

(ሰውየው ራሳቸው ያለውን ሁኔታ ከአንድ ባለሥልጣን ጋር ሊነጋገሩበት ፈልገዋል፡፡ ባለሥልጣኑም የሰውየው ችግር ምንድነው? ያለው ሁኔታስ ወዴት እያመራ ነው? የሚለው ጉዳይ ስላሳሰባቸው ከዋናው ሰውዬ ጋር ለመነጋገር ፈልገዋል፡፡ ባለሥልጣኑ ክቡር ሚኒስትሩ ናቸው፡፡ ሰውዬው ደግሞ ዋነኛው ባለሃብት ናቸው)

Life & Art
Image ልጅነት

በሔኖክ ያሬድ

"ያ ልጅነት በጊዜያቱ ደስ ማለቱ" አንጎራጉር ነበር ያኔ ስሰማ የነበረው የድምፃዊው ዜማ ዛሬ የተከሰተልኝ ከሪደርስ መጻሕፍት መደብር ስወጣ ነበር፡፡ ልጅነትን የሚያስታውስ በተለይም የእኔን የልጅነት ዘመን በ1950ዎቹ መካተቻና በ1960ዎቹ መጀመሪያ ዘመን መቼቱን ያደረገ በልብ ወለድ መልክ የቀረበ መጽሐፍ መመልከቴ ነበር፡፡

 

 
Social
Image አርባ አንድ ዓመታት በአሰጋጅነት

በሠለሞን ጐሹ

ሼህ መሐመድ ኑር ያሲን በሰሜን ወሎ ዞን ሐብሩ ወረዳ መርሳ ከተማ የሚገኘው ሃረመይን መስጊድ ኢማም ናቸው፡፡ በስራቸው ላይ በመርሳ ከተማ ብቻ ከ1960 ዓ.ም. ጀምሮ እንደቆዩ ይናገራሉ፡፡ በዋና አሰጋጅነት ከ41 ዓመት በላይ ቆይተዋል፡፡

 

Science & Technology
Image ኦቫሪ ተተክቶላት መውለድ የቻለች...

ኦቫሪ ተተክቶላት መውለድ የቻለች የመጀመሪያዋ እናት

የሴቴ እንቁላል ማምረቻ አካል (ኦቫሪ) በቀዶ ሕክምና የተተካላት በዓለም ላይ የመጀመሪያዋ የሆነችው እናት በሰላም መገላገሏ ሴት ልጅ ተዓምር ማሰኘቱን ቢቢሲ ዘገበ፡፡

 

 
Diaspora
Image "ዲያስፖራው የበለጠ እንዲሰራ...

"ዲያስፖራው የበለጠ እንዲሰራ የመንግሥት እገዛ ያስፈልገዋል"
በዳዊት ታዬ

አቶ ጥላሁን ጌታቸው ከ22 ዓመታት በላይ በስደት ቆይተው ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡ የ42 ዓመት ጐልማሳ የሆኑት አቶ ጥላሁን ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ናቸው፡፡

 

Youth
Image እንዲሸፍቱ የተገደዱ ልቦች

በምሕረት አስቻለው

ጠባቡ ቢዝነስ ሴንተር ዲቪ በሚሞሉ ሰዎችና እነሱን ለማስተናገድ ወዲያ ወዲህ በሚሉ ሠራተኞቹ ተጨናንቋል፡፡ ከቀኑ አምስት ሰዓት ገደማ ላይ ሃያ ሁለት አካባቢ ከሚገኘው አለም ቢዝነስ ሴንተር ስንደርስ፣ ፎርም የተቀበሉና መቀመጫ ያገኙ ተስተናጋጆች ቁጭ ብለው የዲቪ ፎርም ሲሞሉ መቀመጫ ያላገኙት ደግሞ ቆመው በመጠባበቅ ላይ ነበሩ፡፡ ወደ ውስጥ ለመግባት ሞከርን፡፡ የዲቪ ፎርም በመሙላት ላይ የነበሩት (ሁሉም ማለት ይቻላል) ወጣቶች ነበሩ፡፡ ጠጋ ብለን ልናናግራቸው እንደምንፈልግ የጠየቅናቸው ፎርሙን ሞልተው ከጨረሱ በኋላ እንደሚያነጋግሩን ቃል ገቡልን፡፡ እኛም ቢዝነስ ሴንተሩ ደጃፍ ላይ ቆመን መጠባበቅ ጀመርን፡፡

 

 
Opinion
መቻቻልና ፣ተው ቻለው ሆዴን '...

መቻቻልና ፣ተው ቻለው ሆዴን ' ምን አንድ አረጋቸው?
አንዳርጋቸው ተሻገር

በየዓመቱ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አማካኝነት ተሰይመው አባል አገራት እንዲያከብሯቸው ከተወሰኑ የዓለም ወይም ኢንተርናሽናል "ቀን" ከሚባሉት መካከል በዚህ በያዝነው ወር ከ"ተከበሩት" ወይም ተከበሩ ተብለው በአገር ውስጥ ዜና ሲነገሩ ከፊሎቻችን በጨረፍታ ወይም ድንገት ሌሎች ደግሞ በቁም ነገር ሆን ብለው የሰማነው የ"መቻቻል" ቀን የተባለውን ነው በእንግሊዝኛው ቶለራንስ ይሉታል፡፡ ከአማርኛው "መቻቻል" ጋር ወይም ከሱ በተጨማሪ የእንግሊዝኛውን "ቶለራንስ" ማንሳት የተገደድኩበት ምክንያት ከእንግሊዝኛው ይበልጥ የአማርኛው ቃል በጣም የሚያሳጣው መደበቅ የማይቻለው "ሰብዓዊ መብተኛ" (ሂውማን ራይትስ ፍሬንድሊ) ያልሆነ የሚተናነቀው "አሉታዊ" ነገር ስላለው ነው፡፡ የእንግሊዝኛው "ቶለራንስ"ም ቢሆን የጠራ የነጠረ ስለመሆኑ፣ አለዚያም በሌላ አነጋገር ያልተበረዘ ያልተከለሰ ነው ተብሎ የጤንነት ወይም የጤናማነት የንጽህና ማረጋገጫ የሚሰጠው አይደለም፡፡

 

Letter to Reporter
የነርስነት ሙያ
በሪፖርተር ጋዜጣ ጥቅምት 30 ቀን 2001 ማኅበራዊ ገጽ "የኢትዮጵያ ነርሶች ማኅበር ወደፊት ወይስ ወደ ኋላ?" በሚል ርዕስ የቀረበው ጽሁፍ የነርስነት ሙያ ቀድሞ ከነበረበት ደረጃ በአሁኑ ጊዜ መሻሻሉን ያመለክታል፡፡

 
Women
Image ኮሜርስ መግባት ማለት መራብ ማለት ሆነ?

"ኮሜርስ (ንግድ ሥራ ኮሌጅ) መግባት በራሱ መራብ፣ መቸገር ማለት እንደሆነ ነው የሚገባኝ፡፡ ወንዶችስ ወንድ ስለሆኑ ጎዳና ላይም ሊያድሩ ይችላሉ፡፡ የሚያድሩም አሉ፡፡ እኛ ሴቶች ግን ይሄንን ብናደርግ ራሳችንን አደጋ ላይ መጣል ይሆናል፡፡ ስለዚህ እየተራብን የምንበላው ሳይኖረን ለምንኖርበት ቤት ኪራይ እየከፈልን መኖር የግድ ነው፡፡ በኪራይ እየተኖረም ለሴቶች ችግሩ ብዙ ነው፡፡ አብረን ወጭ እየተጋራን እንኖራለን ብለው ከወንዶች ጋር ከተከራዩ ሴቶች መካከል አንዷ ለመመረቅ ሁለት ወር ሲቀራት አብሯት ከተከራየ ልጅ ፀንሳ ወደ ቤተሰቦቿ መመለሷን አውቃለሁ፡፡ እስካሁንም አልመጣችም፡፡" ይሄንን ያለችን የክፍለ ሃገር ልጅ የሆነችውና በንግድ ሥራ ኮሌጅ የሦስተኛ ዓመት ተማሪ የሆነችው ቢ (ማንነቷን ለመደበቅ ሲባል ስሟ በምህፃረ ቃል ተገልጿል) ናት፡፡

 

Temuaget
በድህነታችን ላይ ነጻ ያልሆነ ...

በድህነታችን ላይ ነጻ ያልሆነ ሚዲያ መደረብ አንችልም
ከበደ ፍሬው

የፕሬስ ነጻነት የሰብአዊ መብት መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ የእውቀትና የመታወቅ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ማንም በዚህ ላይ የተለየ ሃሳብ፣ ሌላ ግኝት አለኝ የሚለው የለውም፡፡ የፕሬስ ነጻነት ራሱ የተለየ ብቻ ሳይሆን ያልተለመደ፣ የማይወደድ፣ የሚያስደነግጥ፣ የሚያስፈራ ሃሳብ የሚፈቅድ፣ የማይከለክል ሆኖ እያለም ጭምር ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ ነው ኢትዮጵያ በንጉሠ ነገሥቱም በወታደራዊው መንግሥትም ዘመን በነበሩት ሕገመንግሥቶች ጨምሮ በመላው ዓለም ዙሪያ ያሉና የነበሩ መንግሥታት ሕገመንግሥቶች ወይም አቻ ህጎች ከዚህ ጉዳይ ፈቀቅ ወይም ፈንገጥ የሚል የተለየ ወይም የተቃረነ ነገር የሌላቸው ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያም ጨምሮ በመላው ዓለም ዙሪያ 60ኛ ዓመቱን የሚያከብረው የዩኒቨርሳል ዲክላሬሽን ኦፍ ሂውማን ራይትስ መሰረታዊ ድንጋጌዎች ባጠቃለለ እና አንቀጽ 19 በተለይ የብዙ አገሮች ሕገመንግስቶች የቋንቋ የቃል አግባብ እና የይዘት ቅድመ መሰረት የሆኑት ከዚህ የተነሳ ነው፡፡ ይህንኑ በምስክርነት የሚያረጋግጥ ነው፡፡

 

 
Law
የህፃናት ህገ ወጥ ዝውውር እና ጉልበት ብዝበዛ

የህፃናት ህገ ወጥ ዝውውር

የህጻናት ህገ ወጥ ዝውውር እድሜአቸው ከ18 ዓመት በታች በሆኑ ህፃናት ላይ የሚፈፀም በህፃናት ላይ ከሚደርሱ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች አንዱ ሲሆን ህፃናትን ለመበዝበዝ ወይም መጠቀሚያ ለማድረግ ታስቦ ወይም አላማ አድርጎ በመመልመል፣ ከቦታ ወደ ቦታ፣ ሀገር ውስጥ ማጓጓዝ ወይም ከሀገር ውጭ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት ወይም ከአንድ ሀገር በማስወጣት ወደ ሌላ ሀገር መወሰድ ወይም ለሌላ ወገን በማስተላለፍ ወይም በመደበቅ ወይም በመቀበል የድርጊቱ ፈፃሚዎች ላቀዱት የብዝበዛ ዓይነት ህፃናቶቹን ማዋል ማለት ነው፡፡

 

Zennk
ስለ ኅዳር በሽታ

በ1911 ዓ.ም የበሽታ መቅሠፍት በኢትዮጵያ ላይ ወርዶ ብዙ ሰው አለቀ፡፡ በሽታው አዲስ አበባ ደርሶ በጣም የታወቀው በኅዳር ወር ስለሆነ በሕዝብ ቃል "የኅዳር በሽታ" የሚል ስም ወጣለት፡፡ ፈረንጆች ግን የበሽታውን ስም ግሪፕ ብለውታል፡፡ በአገራችንም አንዳንድ ሰዎች "ቸነፈር" ብለውት ነበር፡፡

 

 
Delalaw
ጊዜና እኛ
ሁሉም በጊዜ ይወሰናል፡፡ ጊዜ ይሄዳል፣ ጊዜ ይመጣል፡፡ ያለወቅቱ የመጣው ዝናብ ብዙዎችን አስደንግጦ ነበር፡፡ ገበሬው የደረሱ ሰብሎቹን እንዲያነሳ ማሳሰቢያ ተሰጥቶታል፡፡ 2000 ዓ.ምን ያየ ቢሰጋ፣ ቢደነግጥ ትክክል ነው፡፡ ያለፈው ዓመት ድርቅ፣ የኑሮ ውድነት፣ የዋጋ መናር ወደ 2001ም ተላልፏል፡፡

Teles
ለልጁ ሲል ሕይወቱን የሚፈልገው...

ለልጁ ሲል ሕይወቱን የሚፈልገው ወንድወሰን
በትዕግሥት ዘሪሁን

ወንድ ወሰን ፈረደ ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ውስጥ ነው፡፡ ለበርካታ ዓመታት በጠቅላይ ቤተክህነት የደህንነት ጥበቃ አባል ሆኖ ሰርቷል፡፡ በዚህ የሥራ ዘርፍ ላይ እያለም ከሦስት ልጆችና ባለቤቱ ጋር ጥሩ የሚባል ኑሮ ይኖሩ እንደነበር ገልፆልኛል፡፡ ከአራት ወር በፊት ጀምሮ ግን ኑሮውና ሕይወቱ ተቀይሯል፡፡

 

 
Sport
Image ድክመትን በመስተዋት

በኃይሉ አስፋው ገብረየስ

የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ፣ የስፔን ላ ሊጋ፣ የኢጣሊያ ሴሪ አ እንደ ጅብ ጥላቸውን የጣሉበት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ስፖርት ችግር ከመባባስ በስተቀር ሲፈታ አይታይም፡፡ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚባለው በኢትዮጵያ የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን በጨዋታና በውጤት የበላይነት በውድድር ሜዳ፣ የኢትዮጵያ ቡና ቡድን የውድድር ዝግጅት እና ሥነ ሥርዓት ኮሚቴ በቢሮ በሰጠው ውሳኔ ያስመዘገቡት ድል በዳኝነት የሕግ አተረጓጎም፣ በተጨዋች ተገቢነትና በስፖርታዊ ጨዋነት ዙሪያ ያስነሳው ውዝግብ እና የስፖርት ጋዜጠኞች ያዘመመ አስተያየት ያልታደለውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ስፖርት የበለጠ በማቁሰል ጠባሳውን ጥሎ አልፏል፡፡

 

Taxi
ስንቋጥር ስንፈታ
ጥንቁቅ ታክሲዎች ከሥራ ገበታቸው አልተስተጓጐሉም፡፡ ትናንት ማታ ነዳጅ በመቅዳታቸው ዛሬ ሥራ ላይ ተሰማርተዋል፡፡ ነዳጅ ያልቀዱት ረዥም ሰልፍ ወረፋ ይዘዋል፡፡ ቤንዚንና ኢታኖል ከተቀላቀሉ ወዲህ አንዳንድ ጊዜ የነዳጅ እጥረት ይታያል፡፡ ነዳጅ ማደያዎች በመኪና ይጨናነቃሉ፡፡ ይህ ሰሞኑን ተደጋግሟል፡፡ አስቀድሞ በሚገባ ለምን ዝግጅት እንዳልተደረገ አይታወቅም፡፡

 
World
ክፍት የሥራ ቦታዎች በኦባማ አስተዳደር

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ወደ ስልጣን ሲመጡ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ወሳኝ በሆኑ የሀላፊነት ቦታዎች ይሾማሉ፣ ከ2.6 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የፌዴራል መንግሥቱ ሰራተኞች ግን የያዙትን ሥራ ይዘው ይቀጥላሉ፡፡

 

Fere Kenafir
ፍሬከናፍር የምትጽፈውን ሲበዛና አጥብቄ እጠላዋለሁ፡፡ የመፃፍ መብትህን በቀጣይነት ማረጋገጥ ይቻል ዘንድ ግን ሕይወቴን አሳልፌ እስከ መስጠት ድረስ እሄዳለሁ፡፡
ቮልቴር 1770
 
  • Do You Know ?
    How To Increase Font Size
    You can increase the font size of the website if it appears smaller than normal. Just click the member area link at the top right of this page and the page will slide down. At the top left corner of the page, look for three small buttons. To increase font size, click the button with "+" sign and "-" sign to decrease font size.
  • Tips !
    Tips for Amharic Version
    • Use Internet Explorer version 6 or better
    • Adjust your screen resolution to 1024 X 768
    • Use the font resizer to increase font size if needed
    • Though it is not strictly needed having power geez unicode font could enhance the font rendering in your browser
 

Notice

Dear Visitors, we are currently moving our web site to a new server to better serve you with fast and accessible site. While we are doing this you might find broken links and missing images. Therefore, we would like to ask you to wait patiently until we restore our site to its original state with all missing images and a new streaming audio/video service.