| የኤርትራ ሚሊሺያና መደበኛ ሰራዊት... |
|
|
| Thursday, 10 January 2008 | |
|
የኤርትራ ሚሊሺያና መደበኛ ሰራዊት እርስ በእርስ ተዋጉ በፆረና ግንባር የኤርትራ ሚሊሺያና መደበኛ ወታደሮች እርስ በእርስ መዋጋቸውን የአካባቢ ምንጮች ለሪፖርተር ገለፁ፡፡ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ኢትዮጵያ ወረረችን በማለት አስቸኳይ የካቢኔ ስብሰባ ጠርተው ነበር፡፡ እንደ ምንጮቹ ገለፃ ሚሊሻዎቹና የመደበኛ ሰራዊት አባላቱ ከሁለት ሳምንት በፊት ውጊያ የገጠሙት መደበኛ ወታደሮቹ ሚሊሺያዎቹን ለመተካት ስፍራው ሲደርሱ ነው፡፡ በሚሊሺያዎች ጥበቃ የሚደረግለት የፆረና ግንባር አካባቢ በመደበኛ ሰራዊት እንዲተካ የተደረገው በድንበሩ አካባቢ ሚሊሺያዎቹ ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጋር ወዳጅነትና ወንድማማችነት በመፍጠራቸው፣ ከጥቂት ወራት በፊት ከ2000 በላይ የኤርትራ ወታደሮችና መኮንኖች ድንበር ተሻግረው ለኢትዮጵያ እጅ በመስጠታቸው፤ በርካታ ሲቪሎች በፆረና በኩል ድንበር እየተሻገሩ ወደ ኢትዮጵያ በመግባታቸው የኤርትራ መንግስት ..የድንበር ጥበቃው ላልቷል.. በሚል ስጋት ገብቶት እንደሆነ ከምንጮቹ ገለፃ ለመረዳት ተችሏል፡፡ መደበኛ ሰራዊቱ ሲላክ ሚሊሻዎቹ እንዲያውቁ ባለመደረጉ ተኩስ መከፈቱና በተኩሱም ህይወት እንዳለፈ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ምንጮቹ እንደገለፁት ሚሊሻዎቹ በድንገት የተቀላቀላቸው መደበኛ ሰራዊት የኢትዮጵያ ይሁን የኤርትራ ስለማወቃቸው ያሉት ነገር የለም፡፡ እርስ በርስ የተደረገው ውጊያ ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከደረሰ በኋላ በመደናገጥ አስቸኳይ የካቢኔ ስብሰባ በመጥራት ኢትዮጵያ ወረረችኝ ማለታቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ገልፀዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ የእርስ በእርስ ግጭቱ ህዝብ ጆሮ ሳይደርስ አስቸኳይ ካቢኔ የጠሩት በኤርትራ ፖለቲካ ውስጥ የገቡበትን ለማስተንፈስ ሲባል የእርስ በእርስ ግጭቱን መጠቀሚያ ለማድረግ እንደሆነ ምንጮቹ ገልፀዋል፡፡ በስፍራው ያለው የአንሚ ተኩስ መሰማቱን፣ ነገር ግን ተኩሱ የተደረገው በየትኛውም ወገን መካከል እንዳልሆነ እንዳላወቀ መገለፁ አይዘነጋም፡፡ ሪፖርተር |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |