| በማደጎ የሚወሰዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ጨምሯል |
|
|
| Wednesday, 30 April 2008 | |
|
ከጋዜጣው ሪፖርተር
በማደጎነት የሚወሰዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ባለፈው ዓመት ብቻ 71 በመቶ መድረሱን አሶሽየትድ ኘሬስ ዘገበ፡፡ "ኢትዮጵያ በግልፅነት ችግር ምክንያት አብዛኛዎቹ በማደጎነት የሚወስዱበት ሃገር ሆናለች" ሲል በማደጎ የሚወሰደውን ንግግር ጠቅሶ የዜና ወኪሉ ዘግቧል፡፡ በአዲስ አበባ የአሜሪካ አሳዳጊዎች በከተማዋ ሆቴሎች የሚታዩ መሆናቸውንም ጠቅሷል፡፡ ከኢትዮጵያ በማደጎነት ለመውሰድ 30"000 የአሜሪካን ዶላር እንደሚፈጅና በአሜሪካ ከሚከፈለው ግን አነስተኛ መሆኑን በዜናው ተመልክቷል፡፡ በተያያዘ ዜና ቬትናም ዜጎቿ ወደ አሜሪካ በማደጎነት እንዳይሄዱ ከልክላለች፡፡ ክልከላው የፀናው አሶሽየትድ ኘሬስ ከቬትናም ወደ አሜሪካ በማደጎ የሚወሰዱ ልጆች ሕፃናቱ ለሆስፒታሎች እንደሚሸጡ፣ ጫና እንደሚደረግባቸው፣ በየመንደሩ ደላሎች እያሰሱ እንደሚወስዱዋቸው፣ ከአያቶቻቸው ጋር የሚያድጉ ሕፃናትን የእናታቸውን ስም ሳይነግሩ እንደሚልኳቸው ከዘገበ በኋላ ነው፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |