|
Wednesday, 30 April 2008 |
|
በሪፖርተር ጋዜጣ ሚያዚያ 19 ቀን 2000 በ"እኔ የምለው" ገጽ ላይ "የስሜት ማዕበል ለምን ያናውጸናል?" በሚል ርዕስ የቀረበው ጽሁፍ አንብቤያለሁ፡፡
የአንድ ባለሃብት ንብረት በሆኑ ሁለት የነዳጅ ማዲያዎች ላይ ያነጣጠሩ ፍንዳታዎች ንጹሀንን ዜጎችን ለህልፈተ ሕይወት ዳርገዋል፡፡ ማደያዎቹን ለማጋየት የተጠመደው ፈንጂ ድሆችና ሰላማዊ ሰዎችን ጎድቷል፡፡ ባለሃብቱ በዚህ ተደናግጠው እያካሄዱ ያሉትን ልማት እንዲያቆሙ ለማድረግ የተሞከረ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህን የመሰለ ጥፋት የሚፈጽሙ በድርጊታቸው ሊያፍሩ እንጂ ሊደሰቱ አይገባም፡፡ ሕብረተሰቡ ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች እያንዳንዱ እንቅስቃሴ መከታተል ያስፈልጋል፡፡ ሰውን በጅምላ በማጥፋት የሚረኩ ሰዎች ስላሉ ምንጊዜም መዘናጋት አያስፈልግም፡፡ በንፁሃን ላይ ያነጣጠሩ ከእንደዚህ ዓይነት ድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል፡፡ በፈንጂ የሰውን ልጅ በማቃጠል የሚገኝ አዎንታዊ ነገር የለም፡፡ ሰውን መግደል በሰውም በፈጣሪ ዘንድም የተወገዘ ነው፡፡
(ፈለቀ ደሳለኝ፣ ከመርካቶ) |