| ኢትዮጵያ በኳታር ላይ የወሰደችው... |
|
|
| Wednesday, 30 April 2008 | |
|
ኢትዮጵያ በኳታር ላይ የወሰደችው እርምጃ ኤርትራ ተቃወመች
በጋዜጣው ሪፖርተር የኤርትራ ዋነኛ ሽርካ የሆነችው ኳታር በቀጣናው ሽብርተኝነትን እያስፋፋች ነው በማለት ኢትዮጵያ የወሰደችው የግንኙነት መቋረጥ እርምጃ ኤርትራን ማስደንገጡን ኤ.ኤፍ.ፒ የተባለው የዜና ወኪል ዘገበ፡፡ የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጉዳዩን አስመልክቶ ለኤ.ኤፍ.ፒ በሰጠው መግለጫ "እርምጃው በጣም አስደንጋጭ ነው" ብለዋል፡፡ የመግለጫው መከራከሪያ ነጥብ ኢትዮጵያ የወሰደችው ውሳኔ ኤርትራ በተለይ "ወደ ሶማሊያ የሚጎርፈው የኳታርና የሊብያ ድጋፍ ታጓጉዛለች" በሚል ክስ አሜሪካ በአሸባሪዎች ተርታ ከማስፈርዋ የተነሳ እንደሆነ ያትታል፡፡ ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያ የዕምቅ ተዋጊዎችና የሶማሊያ አክራሪዎች ትረዳለች በማለት ኳታርን የከሰሰች ሲሆን ከአገሪቱ ጋር የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማቋረጧ ይታወሳል፡፡ ኤርትራ በበኩሏ ኢትዮጵያ በሶማሊያ የአገር ውስጥ ፖለቲካ ጣልቃ መግባትዋንና የአገሪቱን ሰላም ማመሷን ትከሳለች፡፡ ባለፈው ረቡዕ የኳታር ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እርምጃውን አስመልክተው በሰጠው አስተያየት በውሳኔው መገረሙና መሠረት የሌለው ውንጀላ መሆኑን በመተቸት፣ "የአገሪቱ የተሳሳተ ፖሊሲ ነፀብራቅ ነው" ብለዋል፡፡ ኳታር ከምትረዳቸው የዕምቅ ተዋጊዎች ወይም አሸባሪዎች መካከል ኦብነግ የሚገኝበት ሲሆን ቡድኑ ኢትዮጵያ በአገሪቱ ላይ በወሰደችው እርምጃ ማዘኑንና ተቃውሞውን መግለፁ ይታወሳል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |