| "ዞሮ ገጠም" ለቤተ መጻሕፍቱ ማቋቋሚያ ተበረከተ |
|
|
| Wednesday, 30 April 2008 | |
|
በሔኖክ ያሬድ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም አዲስ ለሚያሠራው ቤተ መጻሕፍት ገቢ የሚሆን በቀድሞ የኦርኬስትራ ኢትዮጵያ አባላትና አስተባባሪዎች በአሜሪካ "ዞሮ ገጠም" በሚል ርእስ በተዘጋጀና በተሰራጨ የቀድሞ ሙዚቃ ሲዲ 10"000 ዶላር ገቢ መገኘቱን ተቋሙ አስታወቀ፡፡ ከነገ በስቲያ ዓርብ በተቋሙ ራስ መኰንን አዳራሽ "ዞሮ ገጠም" የተሰኘው የኦርኬስራ ኢትዮጵያ ባህላዊ የሙዚቃ ሥራዎች የሲዲ ምረቃና ሽያጭ ከልዩ ዝግጅት ጋር እንደሚቀርብ ዳይሬክተሯ ኤልሳቤጥ ወልደ ጊዮርጊስ ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልጸዋል፡፡ "ዞሮ ገጠም" የተሰኘውን ነባሩ የኢትዮጵያ ባህላዊ ሙዚቃ ጨዋታዎች አዲስ ቅጂ ያዘጋጁት የቀድሞ የኦርኬስትራ ኢትዮጵያ አባላት ቻርልስ ሰተን፣ ጌታ መሳይ አበበ፣ መላኩ ገላውና የሙዚቃ አቀናባሪው ተስፋዬ ለማ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ሥነ ጠበብቱ ቻርልስ፣ ጌታመሳይና መላኩ ከባህላዊው ጨዋታ መካከል የተወሰኑትን በምረቃው መድረክ ላይ የሚያቀርቡ ሲሆን፣ ከአዲሱ ሲዲ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ለኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም እንደሚበረከት ዳይሬክተሯ አመልክተዋል፡፡ ኦርኬስትራ ኢትዮጵያ የተመሠረተው በ1958 ዓ.ም ሲሆን፣ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ (የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ) በቤተ ኪነጥበባት ወቴአትር (የአሁኑ ባህል ማዕከል) ሥር ነበር፡፡ በዘመኑ ከተለያዩ አገሪቱ ክፍሎች የተሰባሰቡ 30 ባህላዊ መሣሪያ ተጫዋቾች፣ ድምፃውያንና ዳንኪራ ተጫዋቾች የተካተቱበት ሲሆን፣ ጨዋታውም በክራር፣ ማሲንቆ፣ በገና፣ ዋሽንት፣ እምቢልታ፣ መለከት፣ ከበሮና የመሳሰሉት ይካሄዱ እንደነበር በታሪክ ተመዝግቧል፡፡ "እኛም አለን ሙዚቃ መንፈስ የሚያነቃ፤ ከበሯችን ድምድም፣ ክራራችን". ማሲንቋችን". እምቢልታችን"". በሚለው ዘፈናቸውም ይታወቃሉ፡፡ ኦርኬስትራ ኢትዮጵያን ከ1958 እስከ 1968 በዳይሬክተርነት የመራው ስመ ጥር ሥነጠቢብ ተስፋዬ ለማ በአዘጋጅነትና በአቀናባሪነቱም ይታወቃል፡፡ ቡድኑ ሁለት በሪል ያስቀረጸ ሲሆን የመጀመሪያው በ1961 ዓ.ም "ዘ ብሉ ናይል ግሩፕ" ረየአባይ ልጆችሪ በሚል በቴምፖ ሪከርድስ አማካይነት ሲለቀቅ፣ ሁለተኛው በ1965 ወይም 1966 በብሉ ናይል ሪከርድስ አማካይነት ተሰራጭቷል፡፡ በቅርቡ በአሜሪካ ዋሽንግተን በናሆም ሪከርድስ አማካይነት የተለቀቀው ሲዲ በአራት የቀድሞ አባላቱ አማካይነት መሆኑ ታውቋል፡፡
|
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |