Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow "ኤርትራ ጅቡቲን የሞትስላት በራሷ...
"ኤርትራ ጅቡቲን የሞትስላት በራሷ... Print E-mail
Wednesday, 30 April 2008
Image"ኤርትራ ጅቡቲን የሞትስላት በራሷ ፍላጎትና ወሰን ነው"
የጅቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሐመድ አሊ የሱፍ
በጋዜጣው ሪፖርተር

የጅቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተከበሩ መሐመድ አሊ የሱፍ ከኤርትራ ወሰን አጠገብ በምትገኘው ዱማይራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በጅቡቲና በኤርትራ መካከል የሚገኘው አወዛጋቢ የድንበር ግዛት ዱማይራ ላይ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በተመለከተ ከጊስካ አፍሪካ የዜና ወኪል ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ተርጉመን አቅርበነዋል፡፡

ጥያቄ፡- (የጅቡቲ) ፕሬዚዳንት እስማኢል ኦማር ጉሌህና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ በቅርቡ ባደረጉት የስልክ ግንኙነት ምን እንደተባባሉ ሊነግሩን ይችላሉ?

መሐመድ አሊ የሱፍ፡- እናንተን በማስታወስ ልጀምርና፣ በመግለጫዬ እንደጠቆምሁት በጅቡቲና በኤርትራ መሪዎች መካከል የተደረገው የስልክ ውይይት ለሁለቱም ወገኖች መግባባትና ወንድማማችነት ሊፈጥር የሚችል ነው፡፡

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ከጥቂት ሳምንታት በፊት አሁን አወዛጋቢ በሆነው ስፍራ ላይ ጉብኝት አድርገው ወታደሮቻቸው አንዲት ኢንችም ጥሰው እንዳይገቡ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ራሳቸው ተናግርዋል፡፡

እንደውም የተጠቀሙት ቃል ራሱ "ሺብሪ" ማለትም በዓረብኛ "አንድ ኢንች" አይገቡም የሚል ነው፡፡ ዋናው ጉዳይ ባይሆንም ኤርትራውያን በአካባቢው የኢንጂነሪንግ ሥራ ሲሰሩ በራሳቸው ግዛት ብቻ መሆን እንደነበረበት እርግጥ ነው፡፡ የሆነው ግን ከዚህ ተቃራኒ ነበር፡፡ በእርግጥ ሁሉም አገሮች በድንበር አካባቢ ላይ ተመሳሳይ የሆነ ራእይና መግባባት የላቸውም፡፡

በሁሉም የአፍሪካ አገሮች የድንበር አከላለሉ ከቅኝ አገዛዝ ጋር የተያያዘ በመሆኑ መረጃዎች የሚያረጋግጡት ሲሆን እንደዚህ ዓይነት ጉዳይ ይነሳል፡፡ እኛን በተመለከተ መብታችን ሙሉ ለሙሉ የምናስከብርበት ካርድ (ሰነድ) በእጃችን ነው ያለው፡፡

በወቅቱ የጅቡቲ ሪፐብሊክ ቅኝ ገዢ በነበረችው የፈረንሳይ ግዛት ሱልጣን ራሂይታ መጠቃለሏን የሚያመላክቱ፣ ከ1882 ዓ.ም ጀምሮ የነበሩ ዶክመንቶችና ማስረጃዎች አሉን፡፡ ራስ ዱማይራና የዱማይራ ተራራ የሚገኙት ከዚህ ጎን ለጎን ነው፡፡

ሁለቱ ሃገሮች የፈረሙት የአፍሪካ ህብረት ቻርተር፣ አንቀፅ 3 ላይ በአፍሪካ አገሮች መካከል የድንበር ወሰን በቅኝ ገዢነት የነበረው መካለል ይፀናል፡፡ በዚያ ሥፍራ ምንም ዓይነት የሚያሻማ ጉዳይ የለውም፡፡ ምክንያቱም ማስረጃዎችና ካርታዎች አሉ፡፡

ኤርትራ ከተዳፈረች ጅቡቲ ምን ርምጃ ትወስዳለች? በአሁኑ ወቅት ወሰኖቻችን እየጠበቅን ነው፡፡ የጅቡቲ የመከላከያ ሰራዊት ወሰናችን ላይ ነው፡፡

አሁን መነሳት ያለበት ጥያቄ የኤርትራ ወታደሮች ከግዛታችን ማስወጣትና ማባረር አይደለም፡፡ ቀጠናው ከታጠቀ ኃይል ነፃ በማድረግና የሁለቱም ወታደሮች በዓይነ ቁራኛ እንዳይተያዩና የከፋ ጦርነት ሊያመራ የሚችል ግጭት እንዳይፈጠር መከላከል ነው፡፡

ቢያንስ አነስተኛ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሁኔታዎች ያሉ ይመስለኛል፡፡ የሁለቱም ወገኖች የጦር ኃይሎች ከ50 ሜትር ርቀት ላይ ሆነው እንዳይተያዩ የማረጋገጥ ጉዳይ በሁለቱም መንግሥታት ላይ የተጣለ ኃላፊነት ነው፡፡

ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ፣ የሁለቱም ወገን ወታደሮች ወደካምፓቸው እንዲመለሱና ከድንበሩ እንዲርቁ ቢቻልም በመካከላቸው የ5 ኪ.ሜ ርቀት እንዲኖር ለማድረግ በዲፕሎማሲ ደረጃ እንንቀሳቀሳለን፡፡ እስከ አሁን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁና በወታደሮቹ መካከል አንዳችም ጥይት አልተተኮሰችም፡፡

ጥያቄ፡- ኤርትራ በድንበሩ ላይ ችግር ስትፈጥር እኮ ለሁለተኛ ግዜዋ ነው፣

መሐመድ አሊ የሱፍ፡- እ.ኤ.አ በ1994 ዓ.ም ኤርትራ ነፃነትዋ ያገኘችበት ጊዜ ስለነበረ አዲስ ማንነትና ጂኦግራፊያዊ ይዞታዋ የምትገነባበት ወቅት ነበር፡፡ በእርግጥ በወቅቱ በኤርትራ መንግሥት የተፈፀሙ አንዳንድ ጥፋቶች ነበሩ፡፡ በተለይ ከየመን ጋር የፈጠረችው የድንበር ውዝግብ በዓለም አቀፍ የፍትህ ተቋም ተገቢ ምላሽ ያገኘ ይመስለኛል፡፡

ወንድሞቻችን ኤርትራውያን የጅቡቲ ሰሜናዊ ክፍል ጋር ያለው ድንበር አሁን የያዝነው ብቻ እንዳልሆነ ባቀረብንላቸው ሰነድ አረጋግጠንላቸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ውዝግብ የተፈጠረበት ቦታ እ.ኤ.አ በ1994 ዓ.ም ከተፈጠረው የሚገናኝ ሳይሆን ከመንገድ የተወሰኑ ሜትሮች ራቅ ብሎ የሚገኝ ነው፡፡

ጥያቄ፡- ውዝግብ የፈጠረው ቦታ ኤርትራውያን ለድህነታቸው የሚያሰጋና ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጡት ጉዳይ መሆኑ እውነት ነው?

መሐመድ አሊ የሱፍ፡- ኤርትራ ላለፉት ሰባት ዓመታት ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት ላይ እንደሆነች ይታወቃል፡፡ እስከ አሁን የኢትዮጵያ ወታደሮች በጅቡቲ ግዛት በኩል ወደ ኤርትራ ገብተዋል የሚል ዘገባ ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? ወይስ የእኛ የፀጥታ ኃይሎች በኤርትራ ላይ ወረራ የፈፀሙበት ወቅት ኑሮ ያውቃል? የለም፡፡ በመሆኑም ይሄ ሁሉ የኤርትራ ስጋት መሠረት የሌለው ነው ማለት እችላለሁ፡፡ እዚህ ያለነው ከጎረቤት አገር ወንድማዊነትና ወዳጅነታችን ተጠብቆ እንዲኖር ነው ለዚህም ተግተን እየሰራን ነው፡፡

ጥያቄ፡- ለሐሙስ ረነገሪ የውይይት ቀጠሮ ተይዟል፡፡ ስለዚህ ግንኙነት ምን መገመት ይቻላል?

መሐመድ አሊ የሱፍ፡- ሰነዶቻችን ይዘን ቀርበን እናመሳክራለን፡፡ በድንበሩ ላይ ግልፅ የሆነ ውዝግብ ተፈጥሯል፡፡ በእኛ በኩል ድንበሩ በራሱ ዶመይራ ተራራ አልፎ የጅቡቲ ዱሜይራ ደሴት ከሆነችው ይዘልቃል ነው፡፡ በሀሓመና በሌሎች ዘመናዊ የሳተላይት ቴክኖሎጂዎች ታግዘን ትክክለኛ መስመሩን በሚሊ ሜትር ደረጃ ማወቅ እንችላለን፡፡ እንዲሁም ትክክለኛ ካርታና የካርቶግራፊ ባለሙያ የሆኑ ሰዎችን ተጠቅመን ግራ መጋባት ማስቀረትና ለወደፊቱም ምንም ዓይነት ጥርጣሬ በማያስከትል መልኩ ችግሩን መቋጨት እንችላለን፡፡ የባለሞያዎችን የካርቶግራፈሮች ሥራ ነው የሚሆነው ማለት ነው፡፡

አሁን ያለው የጅቡቲና ኤርትራ የድንበር መስመር ትክክለኛ ነው የሚል የፀና እምነት አለን፡፡
 
< Prev   Next >