Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ኢትዮጵያ በዚምባብዌ ዓለም አቀፍ...
ኢትዮጵያ በዚምባብዌ ዓለም አቀፍ... Print E-mail
Wednesday, 30 April 2008
ኢትዮጵያ በዚምባብዌ ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ላይ ሳትካፈል ቀረች

ለአርባ ዘጠነኛ ጊዜ የተዘጋጀው የዚምባብዌ አለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ላይ ኢትዮጵያ በመጨረሻው ሰዓት እንደማትሳተፍ ማሳወቋን ጋርዲያን የተባለው የዚምባብዌ ጋዜጣ ገለፀ፡፡

እንደ ጋዜጣው ዘገባ (Trade in Zimbabwe for Africa and the world) በሚል መሪ ቃል ባለፈው አርብ የተከፈተው አለም አቀፍ ኤግዚቢሽን ላይ ማላዊ፣ ኬንያ እና ደቡብ አፍሪካ የተካፈሉ ሲሆን ይካፈላሉ ተብሎ ይጠብቁ የነበሩት ኢትዮጵያ፣ ባንግላዲሽና ፓኪስታን ግን በመጨረሻው ሰዓት እንደማይሳተፉ አስታውቀዋል፡፡

ሪፖርቱ እንደጠቆመው ሦስቱ አገሮች በንግድ ትርዒቱ ላይ ላይካፈሉ የቻሉበትን ግልጽ ምክንያት ባያስታውቁም ቀደም ብለው ግን እንደሚሳተፉና ቦታ እንዲዘጋጅላቸው  አስታውቀው እንደነበር አመልክቷል፡፡

በዚምባብዌ አለም አቀፍ የንግድ ትርዒት 565 ድርጅቶች ተካፋይ ሲሆን 21 የውጪ ኩባንያዎች ናቸው፡፡

በጠቅላላው ተሳታፊ አገሮች በማዕከሉ የያዙት ቦታ 54"471 ስኩዌር ካሬ ሜትር ነበር፡፡ ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ የተካሄደው የንግድ ትርዒት ተሳታፊዎች 53"462 ካሬ ሜትር ቦታ ይዘው እንደነበር ተጠቁሟል፡፡

በዚምባብዌ ያለው የኢኮኖሚ ቀውስ የንግድ ትርዒቱ እንደተጠበቀው በርካታ ተሣታፊዎችን ያላስተናገደ መሆኑንም ዘገባው ያመለክታል፡፡
 
< Prev   Next >