Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ከ100 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ...
ከ100 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ... Print E-mail
Wednesday, 30 April 2008
Imageከ100 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ምግብ መግዛት እየተሳነው ነው

ከጋዜጣው ሪፖርተር

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ባንኪሙን በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ከ100 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ምግብ መግዛት አለመቻሉን አስታወቁ፡፡ የምግብ ዋጋ ንረት በከፍተኛ ሁኔታ እየታየባቸው ከመጡ 37 አገራት ውስጥ ኢትዮጵያ አንዷ መሆንዋ ተጠቆመ፡፡

የተመድ ዋና ፀሐፊ ከትናንት ሲውዘርላንድ ላይ በተደረገ ስብሰባ ላይ እንደገለፁት ዓለም በአሁኑ ጊዜ ከምግብ ምርት መወደድ ጋር በተያያዘ ችግር ውስጥ ገብታለች፡፡

በዚህ ስብሰባ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ የዓለም ባንክ፣ የዓለም ገንዘብ ድርጅት፣ የዓለም ምግብ ድርጅትና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈዋል፡፡ የሆኑበት ሲሆን የጉዳዩ አሳሳቢነት ከእለት እለት እያደገ በመምጣቱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከሌሎች አጀንዳዎች በበለጠ ቅድሚያ በመስጠት ዋና ፀሐፊውን ጨምሮ ሌሎች የተመድ ኃላፊዎች በዚሁ ሥራ መጠመዳቸውም ተገል"ል፡፡

በጉባኤው ላይ ተሳታፊ የሆኑ የዓለም አቀፍ ድርጅት ተወካዮች ለምግብ ምርቶች መወደድ መንስኤ ሆነዋል ያሏቸውን በርካታ ምክንያቶች ያስቀመጡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የአየር ንብረት መዛባት፣ የእህል ምርቶችን ከምግብ ውጭ ለሆኑ እንደ ባዮ ፊውል ማምረቻነት መጠቀምና የመሳሰሉት መዘርዘራቸውን የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

በዚህ ስብሰባ ላይ የተገኙት የዓለም ምግብ ድርጅት ተወካይ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚደረገው የምግብ እርዳታ ተጨማሪ 750 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግና ለጋሾችም ይህንን ገንዘብ በአጭር ጊዜ እንዲያሟሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ይህ ስብሰባ ከመደረጉ ቀደም ብሎ ጂ8 በመባል የሚታወቁት የበለፀጉ አገራትና ዓለም አቀፎቹ የገንዘብ ድርጅቶች ተመሳሳይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን የምግብ እህል መወደድን ተከተሎ የተፈጠረውን ችግር ለማቃለል የራሳቸውን እርምጃ እንደሚወስዱ አስታውቀዋል፡፡

በሁለቱም ስብሰባዎች ላይ ባለሙያዎች እንዳስታወቁት የምግብ እህል መወደዱ በተለያዩ አገራት ግጭት ያስነሳ ሲሆን ችግሩን በቶሎ መቅረፍ ካልተቻለ ችግሩ ጐልቶ በሚታይባቸው አገራት ለተጨማሪ ግጭቶች መቀስቀስ ምክንያት ይሆናል በሚል ሥጋታቸውን አጠናክረው ቀጥለውበታል፡፡ የ37 አገራት ዝርዝር የተገለፀ ሲሆን ከዚህ ውስጥም አንዷ ኢትዮጵያ ናት፡፡  
 
< Prev   Next >