| ባህሬን ከኢትዮጵያ የቁም ከብት... |
|
|
| Wednesday, 30 April 2008 | |
ባህሬን ከኢትዮጵያ የቁም ከብት መግዛት ልትጀምር ነውበባህሬን የተከሰተውን የቀይ ስጋ እጥረት ለማስወገድና በገበያ ውስጥ ያለውን ችግር ለማርገብ ከኢትዮጵያ የቁም ከብት ለመግዛት በዝግጅት ላይ እንደሆነች አስታወቀች፡፡ ከባህሬን የንግድና ኢንዱስትሪ ም/ቤት (ቻምበር) የወጣ መግለጫ እንዳመለከተው፣ በባህሬን ውስጥ የተከሰተውን የቀይ ሥጋ እጥረትን ለማስወገድ ከኢትዮጵያ የቁም ከብት መግዛት የተሻለ አማራጭ ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት ወደ ባህሬን ከሄደው የኢትዮጵያ የንግድ ልዑካን ጋር መወያየታቸውንና ለሥጋ የሚሆኑ ከብቶችን ለማግኘት የሚያስችል ስምምነት ላይ መደረሱን የንግድ ም/ቤቱ ምክትል ሊቀመንበር ኢብራሒም ዘይናው ገልፀዋል፡፡ ምክትል ሊቀመንበሩ በውይይቱ ላይ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የእንስሳት ሃብት ያላት አገር መሆኗን ለመረዳት መቻላቸውንና የሚፈልጉትን ያሀል ምርት እንደሚያገኙ እምነት እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡ ኢትዮጵያ በግምት 100 ሚሊዮን የሚደርስ የእንስሳት ሃብት አላት ብለዋል፡፡ ብዙ አገሮች የባህሬንን የቀይ ሥጋ እጥረትን ተከትሎ አማራጭ እያቀረቡ ሲሆን ኢትዮጵያ በፍጥነት በዕድሉ ተጠቃሚ መሆን እንደሚኖርባትም ተገልጿል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |